Author Archives: Central

በሩሲያ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የእሳት አደጋ 37 ሰዎች ሞቱ

መስከረም ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ምዕራብ ሩሲያ በሚገኝ በ አንዳ ሳይካተሪክ ሆስፒታል ውስጥ በተነሳ የ እሳት አደጋ 37 ሰዎች መሞታቸውን  ባለስልጣናት ገለጹ። “ኖቭጎሮድ” ተብሎ በሚጠራው ግዛት በ”ሉካ” መንደር ውስጥ ከእንጨት በተሠራው ሆስፒታል ውስጥ ወደ 60 ሰዎች እየታከሙ ነበር። የሩሲያ ብዙሀን መገናኛ ሪፖርቶችን በመጥቀስ ቢቢሲ እንዳለው፤ ህሙማኑን ትንከባከብ የነበረች አንዲት ነርስም ከሟቾቹ መካከል ትገኝበታለች። እስካሁን ከሟቾቹ መካከል የ15ቱ  አስከሬን ...

Read More »

ጋዜጠኛ ርእዮት አለሙ በረሀብ አድማው ገፍታበታለች

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የዩኒስኮና የ’ኢንተርናሽናል ዊመንስ ሚዲያ ፋውንዴሽን’ ሽልማቶች አሸናፊ የሆነቸው ታዋቂዋ ፀሀፊና መምህር ርእዮት አለሙ በእስር ቤት የጀመረቸውን የረሀብ አድማ የቀጠለች ሲሆን፣ በእስር ቤት የሚገኙ ሌሎች እስረኞች እያሰቃዩዋት መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በግፍ የታሰረቸው ርእዮት ይቅርታ ለመጠየቅ ፈቃደኛ ባለመሆኑዋ የሚደርስባት ስቃይ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው። ሆን ተብሎ በተቀነባበረ ስልት ርእዮት ከእናትና አባቷ እንዲሁም ከነፍስ አባቷ በስተቀር ...

Read More »

ፖሊስ የፍርድ ቤት ትእዛዝ አልቀበለም በማለት በቁጫ ወረዳ ያሰራቸውን የሀገር ሽማግሌዎች ለመፍፋት ፈቃደኛ ሳይሆን ቀረ

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጋሞጎፋ ዞን በቁጫ ወረዳ በቅርቡ የተነሳውን የህዝብ ተቃውሞ መርታችሁዋል በሚል የታሰሩ የወረዳዋ አገር ሽማግሌዎች እና ነዋሪዎች ማስረጃ በመጥፋቱ እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ሀምሌ 22 እና 30 ቢወስንም ፖሊስ የፍርድ ቤትን ትእዛዝ አልቀበልም በማለት ግለሰቦቹ እስከሁን ድረስ ታስረው እንደሚገኙ ታውቋል። ፖሊስ ከፍርድ ቤት በላይ ሆኖ እስረኞችን አልፈታም ማለቱ እና  እንዲያውም ሌሎች ተጨማሪ ሰዎችን ለማሰር በዝግጅት ላይ ...

Read More »

መብራት ሀይል ለሁለት አመታት በህዶች ሊተዳደር ነው

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያን ህዝብ የመብራት ፍላጎት ማሙዋላት ያልቻለውን መብራት ሀይልን ከ300 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ክፍያ የህንድ ኩባንያ ሊያስተዳድረው ነው። ቴሌን ሲያስተዳድረው የነበረው የፈረንሳይ ኩባንያ በሺ የሚቆጠሩ ሰራተኞችን በማባረርና በቦታቸው በተለይም ከመከላከያ የመጡ ሰዎች እንዲይዙት ከማድረግ የዘለለ ነገር አልፈጸመም በሚል በሰራተኞች ሳይቀር ትችት ቢቀርብበትም፣ መንግስት መብራት ሀይልንም በተመሳሳይ መንገድ ለማስተዳደር ያወጣውን እቅድ ተግባራዊ አድርጓል። አዲሱ ኩባንያ በርካታ ...

Read More »

ሶሪያ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎቿን ለማስፈተሽ መስማማቱዋን ፕሬዚዳንት አሳድ አስታወቁ

መስከረም ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምእራባዊያን አገራት በተለይም ከአሜሪካ  ድብደባ  ለጊዜውም ቢሆን የተረፈችው ሶሪያ በአገሯ ያሉ የኬሚካል የጦር መሳሪያዎችን በሙሉ ለማውደም ፈቃደኛ መሆኑዋን ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ተናግረዋል። ከሩሲያ የቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ቃለ ምልልስ ያደረጉት አላሳድ፣ አገራቸው ስምምነቱን የምትፈርመው ሩሲያ ስላግባባቻች እንጅ የአሜሪካን ጥቃት ፈርታ አይደለም። የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሜር ፑቲን በኒውዮርክ ታይምስ ላይ ለአሜሪካ ህዝብ እንዲደርስ በማለት ባሰፈሩት ጽሁፍ አሜሪካ ...

Read More »

ኢሳት የቶምቦላ እጣ ማውጣቱን ስነስርአት ለአንድ ወር ማራዘሙን አስታወቀ

ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ለኢትዮጵያውያን አዲስ አመት የመኪና የቶምቦላ ትኬት ማዘጋጀቱ ይታወቃል። ይሁን እንጅ በተለያዩ አገራት የሚገኙ የሽያጭ ወኪሎቻችን፣ በርካታ ኢትዮጵያን የሽያጭ ጊዜው በአንድ ወር እንዲራዘም መጠየቃቸውን ተከትሎ ሽያጩን ለመጨረሻ ጊዜ ለአንድ ወር ለማራዘም መወሰኑን የድርጅቱ የገቢ አሰባሳቢ ግበረሀይል ገልጿል። ተቋሙ እጣውን አስቀድሞ በተያዘለት መረሀ ግብር ለማውጣት ባለመቻሉም ይቅርታ ጠይቋል። በተለያዩ አገራት የሚገኙ የኢሳት የሽያጭ ወኪሎች፣ በእጃችው ...

Read More »

በጉዲፈቻ የወሰዱዋቸውን ኢትዮጵያውያን ልጆች የገደሉት አሜሪካውያን ጥፋተኞች ተባሉ

ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላሪ እና ካሪ ዊሊያምስ የተባሉ አሜሪካውያን ባልና ሚስቶች ሃና ዊሊያምስ የተባለቸውን የ13 አመት ታዳጊ ህጻን፣ ደብድበው፣ አስርበውና አሰቃይተው ገድለዋታል። ግለሰቦቹ በተመሳሳይ መንገድ አንድ ታዳጊ ወጣት በመግደላቸው በአንደኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል። ባልና ሚስቱ ለታዳጊዎቹ ሞት እርስበርሳቸው በፍርድ ቤት መወቃቀሳቸው ታውቋል። ሁለቱም ግለሰቦች በእድሜ ልክ እስራት ሊቀጡ ይችላሉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

Read More »

የኢትዩጵያ ሬዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ፊደራሊዝምን ባላከበረ መልኩ ያለ አግባብ ከክልሎች እንደሚሰበስብ ታወቀ

ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ኤጀንሲ በቴሌቪዥን ቻናል አንድ እና ሁለት የአየር ሰዓት ድልድል ወጥቶላቸው በቀን የአንድ ስዓት ስርጭት የክልሎችን ተደማጭነት እና የልማት ዘገባ ለህዝቡ ለማድረስ ፣ እያንዳንዱ ክልል ለኢቲቪ በአመት አምስት ሚሊየን ብር በነፍስ ወከፍ ይከፍላል፡፡  የኢትዩጵያ ሬዲዩና ቴሌቪዥን በእየአመቱ ከክልሎች ብቻ 55 ሚሊየን ብር ገቢ ያገኛል፡፡ ክልሎች በራሳቸው ሳተለይት ተከራይተው ዝግጀቶቻቸውን ለማቅረብ ጥያቄ ቢያቀርቡም ...

Read More »

በኢትዩጵያ 66 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች መፀዳጃ ቤት አልባ ናቸው

ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የኢትዮጵያ ዌልፌር ሞኒተሪንግ ሰርቬይ ሪፖርት እንደሚያሳየው፣ በኢትዮጵያ 66 በመቶ የሚሆኑ ቤቶች መፀዳጃ ቤት የላቸውም፡፡ መጸዳጃዎች ካሏቸው ውስጥ 2.2 በመቶ በውኃ የሚለቀቅ፣ 63.8 በመቶ ያህሉ በጉድጓድ የሚጠቀሙ ናቸው፡፡ በሜዳ ወይም በጫካ የሚጠቀሙት 33.7 በመቶ ያህሉን ይሸፍናሉ፡፡ በጫካ ወይም በሜዳ ከሚጠቀሙት 12.5 በመቶ ያህሉ በከተማ ሲሆን 39.5 በመቶው በገጠር አካባቢ ነው፡፡ ወተር ኤይድ ...

Read More »

አንድነት ፓርቲ በአዳማ/ናዝሬት የተሰካ የተቃውሞ ሰልፍ አደረገ

ጳግሜ ፬(አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት ገዢው ፓርቲ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ እየፈጸመ ያለውን የሰብአዊ መብቶች ጥሰት ከማውገዝ በተጨማሪ ህዝቡ ለእውነተኛ ለውጥ እንዲነሳ ጥሪ አድርጓል። ሰልፈኛው ሲያሰማቸው ከነበሩት መፈክሮች መካከል ጥያቄያችን ህገመንግስታዊ ነው፣ ውሸት ሰልችቶናል፣ ስራ መግኘት መብታችን ነው፣ ጸረ ሽብር ህጉ በራሱ አሸባሪ ነው፣ መንግስት፣ የኑሮ ድጎማ ያድርግልን፣  ድህነት በወሬ አይጠፋም፣ ርእዮት አለሙ አሸባሪ አይደለችም፣ ...

Read More »