በጉዲፈቻ የወሰዱዋቸውን ኢትዮጵያውያን ልጆች የገደሉት አሜሪካውያን ጥፋተኞች ተባሉ

ጳግሜ ፭(አምስት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ላሪ እና ካሪ ዊሊያምስ የተባሉ አሜሪካውያን ባልና ሚስቶች ሃና ዊሊያምስ የተባለቸውን የ13 አመት ታዳጊ ህጻን፣ ደብድበው፣ አስርበውና አሰቃይተው ገድለዋታል።

ግለሰቦቹ በተመሳሳይ መንገድ አንድ ታዳጊ ወጣት በመግደላቸው በአንደኛ ደረጃ የግድያ ወንጀል ጥፋተኛ ተብለዋል።

ባልና ሚስቱ ለታዳጊዎቹ ሞት እርስበርሳቸው በፍርድ ቤት መወቃቀሳቸው ታውቋል። ሁለቱም ግለሰቦች በእድሜ ልክ እስራት ሊቀጡ ይችላሉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።