ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በሶማሊ ክልል ዋና ከተማ ጅጅጋ የሚታየው ሁኔታ እስከ ዛሬ ከታዩት ሁሉ የተለየ ነው ይላሉ ነዋሪዎች። ከሌሎች አካባቢዎች በመሄድ ወደ ከተማው መግባት ወይም ከከተማው በመውጣት ወደ ሌሎች አካባቢዎች መሄድ የተከለከለ ነው ይላሉ። የመከላከያ ሰራዊት አባላት በከተማው በብዛት በመገኘት ቤት ለቤት የሚያካሂዱት ፍተሻ ለነዋሪዎች ጭንቀትን ፈጥሮባቸዋል። በክልሉ ፕሬዚዳንት ትእዛዝ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ላፕቶፕ ኮምፒዩተራቸውን ...
Read More »Author Archives: Central
በየካ ክፍለከተማ አንድ ጤና ጣቢያ ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀየረ
ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራሩ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 18 ለህዝብ አገልግሎት በሚል የተሰራው ጤና ጣቢያ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የእስረኞች ማጎሪያ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሆን መደረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል። የአካባቢው ነዋሪ በቂ የህክምና ቦታ አጥቶ በሚቸገርበት ጊዜ ፣ መንግስት ጤና ጣቢያውን ፖሊስ ጣቢያ ማድረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በጉዳዩ ዙሪያ የክፍለ-ከተማውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ...
Read More »በቁጫ ወረዳ ከተነሳው ተቃውሞ ጋር በተያያዘ በርካታ ትምህርት ቤቶች ተዘጉ
ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በቁጫ ወረዳ የሚማሩ ተማሪዎች ከማንነት እና መብት መከበር ጋር በተያያዘ ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ የአንደኛ እና መለስተኛ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ትምህርት ማቆማቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ተማሪዎቹ በቋንቋችን እንማር፣ በአካባቢያችን የሚታየው የመብት ረገጣ ይቁም የሚሉ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ የፌደራል ፖሊስ አካባቢውን ከተቆጣጠረው በሁዋላ ቁጥራቸው ከ25 እስከ 40 የሚደርሱ ተማሪዎችን ይዞ ...
Read More »ከመሬት፣ እንዱ ስትሪና ከተማ ፤ልማት ጋር በተያያዘ ከ990 ሺ በላይ አቤቱታዎች መፍትሄ ማጣታቸው ተመለከተ።
ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመሬት፣ ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት እንደተሳነው መረጃዎች አመልክተዋል። የመልካም አስተዳደር ኮማንድ ፖስት ሴክሬታርያት ፅ/ቤት የ2005 የ6 ወራት የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት እንደሚያሳየው ከመሬት፣ ከኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ጋር በተያያዘ በመላ አገሪቱ ለቀረቡ 990 ሺ 627 አቤቱታዎች መንግስት መልስ ለመስጠት ተስኖታል። የመልካም ...
Read More »አርሶደአሮች አሸባሪዎችን ነቅታችሁ ጠብቁ መባላቸውን ገለፁ፡፡
ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሎ ዞን በእያንዳንዱ ቀበሌ 10 ሰዎች እየተመለመሉ አሸባሪዎችን ነቅተው እንዲጠብቁ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል። በስልጠናው የተነሳ አዝመራችንን እንኳ በወቅቱ ለመሰብሰብ አልቻልንም የሚሉት አርሶደአሮች፣ በአካባቢያቸው ጸረ ሰላም ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ ከተመለከቱ ወይም ጸጉረ ልውጦችን ከተመለከቱ ለመንግስት አካላት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል። ለሁለት ሳምንት በሚቆየው በዚህ ስልጠና አርሶአደሮቹ ስለመጪው ምርጫ እና ስለኢህአዴግ እቅድ ...
Read More »የእንድብር ነዋሪዎች በመብራት እና ውሀ መጥፋት ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል ይላሉ
ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጉራጌ ዞን የእንድብር ከተማ ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማቸው ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ መብራት በመጥፋቱ እናቶች እህል አስፈጭተው ልጆቻቸውን መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል። አቅሙ ያላቸው 30 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ወልቂጤ ከተማ በመሄድ እህል ለማስፈጨት መቻላቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አቅሙ የሌላቸው ግለሰቦች ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል። ይህ በእንዲ እንዳለ መብራት መጥፋቱን ...
Read More »የቀድሞው የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት የሞቱት ፖሎኒየም በተሰኘ ንጥረ ነገር ተመርዘው እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ መውጣቱን አልጀዚራ ዘገበ።
ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የስዊዝ ሳይንቲስቶችን የምርመራ ውጤት በመጥቀስ አልጀዚራ እንደዘገበው፤ በያሲር አራፋት ሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፖሎኒየም የተሰኘ የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር ክምችት ተገኝቷል። ይሁንና እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ለሞት የተዳረጉት ያሲር አራፋት በፖሎኒየም የተመረዙት መቼ እንደሆነ የሳይንቲስቶቹ ጥናት አያመለክትም። የምርመራ ጥናቱ ውጤት በያሲር አራፋት አስከሬን ውስጥ ከትክክለኛው መጠን የ 18 ጊዜ ያህል ብልጫ ያለው ...
Read More »ቁጫ ዛሬ በተቃውሞ ሰልፍ ስትናወጥ ዋለች
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከማንነት ጋር በተያያዘ አንዴ ሲሞቅ ሌላ ጊዜ ሲቀዘቅዝ የነበረው የቁጫ ተቃውሞ በዛሬው እለት በሰላም በር ከተማ ተጠናክሮ መካሄዱን ከአካባቢው ያገኘነው መረጃ ያመልክታል። ዛሬ ተቃውሞውን ያካሄዱት ተማሪዎች ሲሆኑ ፣ ተማሪዎችም ላቀረብነው ጥያቄ መልስ የማይሰጠን ከሆነ ትምህርት አንማርም ብለዋል። ተቃውሞውን አስተባብረዋል የተባሉ መምህራንም በአስቸኳይ ስብሰባ ተጠርተው ተቃውሞን የመሩትን እንዲያጋልጡ ተጠይቀዋል። ልዩ ሀይል ከተማዋን ተቆጣጥሮ በተማሪዎች ...
Read More »መንግስት አገሪቱ በሽብር ጥቃት ኢላማ ውስጥ ገብታለች አለ
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጸረ ሽብር ግብረሀይል ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ባስተላላፈው መልእክት አልሸባብና በኤርትራ የሚደገፉ ሀይሎች በመላው አገሪቱ ጥቃት ለመፈጸም እየተዘጋጁ መሆኑን አስተማማኝ መረጃ ደርሶኛል ብሎአል። ዜጎች እራሳቸውን ለመከላከል አስፈላጊውን ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለባቸውም ገልጿል። ሰሞኑን በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ፍተሻዎች ሲደረጉ የሰነበቱ ሲሆን፣ የትናንቱ ማስጠንቀቂያም ይህን ተከትሎ የተሰጠ ነው። መንግስት በኤርትራ የሚደገፉ የሽብር ሀይሎች ጥቃት ለመሰንዘር ተዘጋጅተዋል ቢልም ...
Read More »የኢንተርኔት አፈናንና ስለላን የሚፈቅደው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የሚኒስትሮች ምክር ቤትን ደንብ ቁጥር 250/2003 ሽሮ እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀ ፤ ተጠሪነቱ ለጠ/ሚኒስትሩ የሆነ የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲን ለማቋቋሚያ የወጣው አዋጅ ሀሙስ ይጸድቃል።በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ተዘጋጅቶ በካቢኔ ፀድቆ ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉ የትራንሰፖርት እና የኢንዱስትሪ የቁጥጥር ስርዓቶች ደህንነት ኮምፒዩተርን መሰረት ያደረጉት የኢነርጂ፣ የባቡር ኔትዎርክ፣ የአቬሽን፣ ...
Read More »