የቀድሞው የፍልስጥኤም መሪ ያሲር አራፋት የሞቱት ፖሎኒየም በተሰኘ ንጥረ ነገር ተመርዘው እንደሆነ የሚያረጋግጥ መረጃ መውጣቱን አልጀዚራ ዘገበ።

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-የስዊዝ ሳይንቲስቶችን የምርመራ ውጤት በመጥቀስ አልጀዚራ  እንደዘገበው፤ በያሲር አራፋት ሰውነት ውስጥ ከመጠን ያለፈ ፖሎኒየም የተሰኘ የራዲዮ አክቲቭ ንጥረ ነገር ክምችት ተገኝቷል።

ይሁንና እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2004 ለሞት የተዳረጉት ያሲር አራፋት በፖሎኒየም የተመረዙት መቼ እንደሆነ የሳይንቲስቶቹ ጥናት አያመለክትም።

የምርመራ ጥናቱ ውጤት በያሲር አራፋት አስከሬን ውስጥ ከትክክለኛው መጠን   የ 18  ጊዜ  ያህል ብልጫ ያለው የፖሎኒየም  ንጥረ ነገር ነው መገኘቱን ነው የሚያመለክተው።