የእንድብር ነዋሪዎች በመብራት እና ውሀ መጥፋት ምክንያት ለከፍተኛ ችግር ተጋልጠናል ይላሉ

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በጉራጌ ዞን የእንድብር ከተማ  ነዋሪዎች እንደተናገሩት በከተማቸው ካለፉት 5 ቀናት ጀምሮ መብራት በመጥፋቱ እናቶች እህል አስፈጭተው ልጆቻቸውን መመገብ የማይችሉበት ደረጃ ላይ ደርሰዋል።

አቅሙ ያላቸው 30 ኪሎ ሜትሮችን ተጉዘው ወልቂጤ ከተማ በመሄድ እህል ለማስፈጨት መቻላቸውን የሚናገሩት ነዋሪዎች፣ አቅሙ የሌላቸው ግለሰቦች ግን ይህን ማድረግ ባለመቻላቸው ለከፍተኛ ችግር ተዳርገዋል ብለዋል።

ይህ በእንዲ እንዳለ መብራት መጥፋቱን ተከትሎም ውሀ በመጥፋቱ የከተማው ነዋሪ ምሬቱን እየገለጸ እንደሚገኝ ተያይዞ የደረሰን ዜና ያመለክታል።