አርሶደአሮች አሸባሪዎችን ነቅታችሁ ጠብቁ መባላቸውን ገለፁ፡፡

ጥቅምት ፳፰(ሃያ ስምንት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በሰሜን ወሎ ዞን በእያንዳንዱ ቀበሌ  10 ሰዎች እየተመለመሉ አሸባሪዎችን ነቅተው እንዲጠብቁ ስልጠና እየተሰጣቸው መሆኑን አርሶ አደሮች ተናግረዋል።

በስልጠናው የተነሳ አዝመራችንን እንኳ በወቅቱ ለመሰብሰብ አልቻልንም የሚሉት አርሶደአሮች፣ በአካባቢያቸው ጸረ ሰላም ሀይሎች ሲንቀሳቀሱ ከተመለከቱ ወይም ጸጉረ ልውጦችን ከተመለከቱ ለመንግስት አካላት ሪፖርት እንዲያደርጉ ተነግሮአቸዋል።

ለሁለት ሳምንት በሚቆየው በዚህ ስልጠና አርሶአደሮቹ ስለመጪው ምርጫ እና ስለኢህአዴግ እቅድ ስልጠና ይሰጣቸዋል።