በየካ ክፍለከተማ አንድ ጤና ጣቢያ ወደ ፖሊስ ጣቢያነት ተቀየረ

ጥቅምት ፳፱(ሃያ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በየካ ክፍለ ከተማ በቀድሞ አጠራሩ ከፍተኛ 12 ቀበሌ 18 ለህዝብ አገልግሎት በሚል የተሰራው ጤና ጣቢያ ካለፉት 6 ወራት ጀምሮ የእስረኞች ማጎሪያ ፖሊስ ጣቢያ እንዲሆን መደረጉን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የአካባቢው ነዋሪ በቂ የህክምና ቦታ አጥቶ በሚቸገርበት ጊዜ ፣ መንግስት ጤና ጣቢያውን ፖሊስ ጣቢያ ማድረጉ በእጅጉ እንዳሳዘናቸው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የክፍለ-ከተማውን ባለስልጣናት ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።