ህዳር ፲፫(አስራ ሦስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዩኒሴፍ ባወጣው ሪፖርት እንደማለከተው ይህን ችግር ለመቅረፍ የኮሚኒቲ አስተባባሪዎች ከፍተኛ ሚና መጫወት አለባቸው። ኤርትራ ውጭ ላይ መጸዳዳትን በማስቀረት ከፍተኛ ድል ማስመዝገቡዋን ዩኒሴፍ ጠቅሷል። በመላው ኤርትራ ውጤታማ ስራ በመሰራቱ አገሪቱ ውጭ ላይ መጸዳዳትን ያስቆመች አገር የሚል ሰርተፊኬት እንደሚሰጣት ድርጅቱ ገልጿል። በአለም ላይ 34 በመቶ የሚሆኑ ዜጎች ንጹህ የመጸዳጃ ቦታ የላቸውም።
Read More »Author Archives: Central
በአቶ መለስ ትእዛዝ በሳውድ አረቢያ የኢትዮጵያውያን ኮሚኒቲ ንብረት ተወርሶ ኢምባሲና የአምባሰደሩ መኖሪያ ቤት እንደተሰራበት ታወቀ
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት በደረሰው አስተማማኝ መረጃ መሰረት በሳውድ አረቢያ ይኖሩ የነበሩ ኢትዮጵያውያን ለትምህርት ቤት መገንቢያ እና ለችግር ግዜ ይሆነናል በማለት ከግል ኪሳቸው እያወጡ በደረግ ዘመን ሲያጠራቅሙት የነበረውን ገንዘብ የቀድሞው ጠ/ሚ መለስ ዜናዊ በሰጡት ትእዛዝ ገንዘቡ ተወርሶ በሪያድ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኢምባሲና የአምባሳደሩ መኖሪያ እንዲሁም ጅዳ የሚገኘው የቆንስላ ጽህፈት ቤት እንዲሰራበት ተድርጓል። ኮሚኒቲው በወቅቱ 50 ሚሊዮን ...
Read More »ከሳውድ አረቢያ የሚመለሱ ኢትዮጵያውያንን ቁጥር በተመለከተ የመንግስት ባለስልጣናት የሚሰጡት መግለጫ ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ ጥሎታል
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዘግይቶም ቢሆን ችግረኛ ኢትዮጵያውያንን ከሳውድ አረቢያ ማስወጣት የጀመረው የኢትዮጵያ መንግስት፣ እስካሁን ድረስ የተመላሾችን አሀዝ በተመለከተ የሚሰጠው መግለጫ ግን ህዝቡን ጥርጣሬ ላይ መጣሉን የኢትዮጵያው ዘጋቢያችን ገልጿል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስተሩ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሀኖም በቲውተር ወደ አገር ቤት የተመለሱት ኢትዮጵያውያን ቁጥር 10 ሺ 707 ነው በማለት ገልጸዋል። ይሁን እንጅ የእርሳቸው ቃል አቀባይ የሆኑት አምባሳደር ዲና ...
Read More »በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የተፈጸመውን የመብት ጥሰት ለመቃወም የሚደረጉ ሰልፎች እንደቀጠሉ ነው
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በሰኞ ኖቬምበር 25፤ 2013 ከ ጠዋቱ 8:30 ጀምሮ ሚድራንድ በሚገኘው ፓን አፍሪካ ፓርላማ ፊት ለፊት ታላቅ የተቃውሞ ሰልፍ እንደሚያዘጋጁ ለኢሳት ተናግረዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በተዘጋጀው ሰላማዊ ሰልፍ ላይ በመገኘት ድምጻቸውን እንዲያሰሙ ተማጽነዋል።
Read More »በሚኒስትር ማእረግ የሚለው ሹመት ውዝግብ እያስነሳ ነው
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት 15ኛ ወንጀል ችሎት አቶ መላኩ ፈንታ ክሳቸው በየትኛው ፍርድቤት ይታይ የሚለውን ጉዳይ ፥ የህገመንግስት ትርጉም ያስፈልገዋል በሚል ለሕገመንግስት አጣሪ ጉባኤ መምራቱ አንዳንድ ከፍተኛ የኢህአዴግ ሹማምንትን እንዳላስደሰተ ታውቋል። ሰኞ ህዳር 10 ቀን 2006 ዓ.ም በነበረው የችሎት ውሎ አቶ መላኩ ፈንታበሚኒስትር ማዕረግ ተሸመው ሲያገለግሉ እንደነበሩና በወቅቱም የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባል ...
Read More »በቡራዩ ከ500 በላይ ቤቶች ፈረሱ
ህዳር ፲፪(አስራ ሁለት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በዛሬው እለት የአዲስ አበባ መስተዳድር በቡራዩ አካባቢ በወሰደው እርምጃ፣ ከ500 በላይ ቤቶችን ያፈረሰ ሲሆን በርካታ ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል። አመዲና ጎጥ በተባለ አካባቢ የሚኖር አንድ መስፍን የተባለ ወጣት ወላጆቼ በሰሩት ቤት መኖር ካልቻልኩ ምን ህይወት አለኝ በሚል ራሱን ማጥፋቱም ታውቋል። የቀበሌው ሊቀመንበር ህዝቡን ሰብስቦ ለማነጋገር ቢመክሩም ህዝቡ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር ...
Read More »በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ የደረሰውን ጥቃት የሚቃወሙ ሰልፎች እንደቀጠሉ ነው
ህዳር ፲፩(አስራ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ ህጋዊ የመኖሪያ ፈቃድ የላቸውም በሚል የሳውዲ ፖሊሶች እና ወጣቶች በኢትዮጵያውያን ሴቶች፣ ህጻናትና ወንዶች ላይ የፈጸሙትን የሰብአዊ መብት ጥሰት በመቃወም በተለያዩ የውጭ አገራት የሚካሄዱት የተቃውሞ ሰልፎች እንደቀጠሉ ሲሆን ፣ በዛሬው እለት በስዊዘርላንድ በርን በተካሄደው ተቃውሞ ኢትዮጵያውያኑ ስሜታቸውን ለመቆጣጠር ተስኖአቸው ታይተዋል። ኢትዮጵያውያኑ የሳውዲን መንግስትና የኢትዮጵያን መንግስት የሚያወግዙ መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ሳውዲ ኢምባሲ ...
Read More »የስዊድን የጦር ፍርድ-ቤት አቃቢ-ህግ በኢትዮጵያ መንግስት ባለስልጣናት ላይ ምርመራ እንዲካሄድ ወሰነ፡፡
ህዳር ፲፩(አስራ አንድ )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የጦር ፍርድ ቤቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው በቅርቡ በኦጋዴን የተፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰት በተመለከተ፣ የክልሉ የወጣቶች ሊቀመንበርና የፕሬዚዳንቱ የግል ዌብሳት ማኔጀር እና አማካሪ የነበረው ወጣት አብዱላሂ ሁሴን በኦጋዴን የጦር ወንጀልና የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መፈጸሙን የሚያሳይ ማስረጃ ለፍርድ ቤቱ አቃቢ ህግ ማቅረቡን ተከትሎ ነው። የጦር ፍርድ ቤቱ ዋና አቃቢ ህግ ክሪስተር ፒተርሰን በ10 ...
Read More »የፌደራል ፖሊሶች በሳውድ አረቢያ የሚፈጸመውን ግፍ ለመቃወም አደባባይ በወጡ ኢትዮጵያውያን ላይ ጥቃት ሰነዘሩ
ህዳር ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሳውድ አረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈጸመ ያለው ግፍ ተባብሶ በቀጠለበት በዚህ ወቅት፣ የሳውዲን መንግስት ለመቃወም በሳውድ አረቢያ ኢምባሲ ፊት ለፊት ተቃውሞዋቸውን ለመግለጽ የወጡ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ተደብድበዋል። ከ100 በላይ ሰዎች ታስረው የነበረ ሲሆን እስከ ምሽት ድረስ 40 የሚሆኑት ተለቀዋል። ሰልፉን ያዘጋጀው የሰማያዊ ፓርቲ 15 የአመራር አካላትም በእስር ላይ እንደሚገኙና ይህን ዜና እስካጠናከርንበት ጊዜ ...
Read More »በሰዑዲ አረቢያ ሚገኙ ኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ተባብሶ ቀጥሏል።
ህዳር ፭(አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአውሮፓና አሜሪካ የሚገኙ ኢትዮያውያን በሰልፍ ተቃውሟቸውን ሲገልፁ ውለዋል። በሳዑዲ ዐረቢያ በኢትዮጵያውያን ላይ እየተፈፀመ ያለው ግፍ ተባብሶ መቀጠሉን ተጠቂዎቹ ለኢሳት ገለፁ። በሪያድ ወደማጎሪያ ካምፕ ውስጥ የተወሰዱ ኢትዮጵያውያን ካሉበት ስፍራ ሆነው ለ ኢሳት በስልክ እንደገለፁት፤ በትናንትናው ዕለት ብቻ በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በከባድ መኪናዎች እየተጫኑ ወዳልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። ስደተኞቹ-ለሳዑዲ ፖሊሶች፦” ወደ ሦስተኛ አገር የማታሻግሩን ከሆነ ወደ ...
Read More »