በቡራዩ ከ500 በላይ ቤቶች ፈረሱ

ህዳር ፲፪(አስ ሁለት )ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በዛሬው እለት የአዲስ አበባ መስተዳድር በቡራዩ አካባቢ በወሰደው እርምጃ፣ ከ500 በላይ ቤቶችን ያፈረሰ ሲሆን በርካታ ቤተሰቦች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ለኢሳት ገልጸዋል።

አመዲና ጎጥ በተባለ አካባቢ የሚኖር አንድ መስፍን የተባለ ወጣት ወላጆቼ በሰሩት ቤት መኖር ካልቻልኩ ምን ህይወት አለኝ በሚል ራሱን ማጥፋቱም ታውቋል።

የቀበሌው ሊቀመንበር ህዝቡን ሰብስቦ ለማነጋገር ቢመክሩም ህዝቡ ከእናንተ ጋር ለመነጋገር አንፈልግም በሚል ሳይሳካ ቀርቷል።