Author Archives: Central

አረና ትግራይ ህወሀት ላይ ክስ ሊመሰርት ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011) አረና ትግራይ ህወሀት ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን አስታወቀ። የአረና ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ እንደገለጹት ፓርቲያቸው ህወሀት ላይ ክስ የሚመሰርተው በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ለተቋቋመው የፓርቲዎች ምክር ቤት ነው። በትግራይ የህወሀት አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል የሚለው አረና አባላቶቼ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ነው ሲል አስታውቋል። በእንደርታ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው በደል በማውገዝም ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው እንደሚያደርግ ገልጿል። ህወሀት በፓርቲዎች መሀል የተፈረመውን የቃልኪዳን ...

Read More »

የጌዲዮ ተወላጆችና የዲላ ነዋሪዎች ሰላማዊ ሰልፍ ለሁለተኛ ጊዜ ታገደ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)የጌዲዮ ተወላጆችና የዲላ ነዋሪዎች በዲላ ሊያካሂዱት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ለሁለተኛ ጊዜ ተከለከለ። በመጨረሻው  ሰአት ሰልፉ መከልከሉ እንዳሳዘናቸው አስተባባሪዎች ገለጹ።የዲላ ከተማ አስተዳደር ለሰላማዊ ሰልፉ አስተባባሪዎች በላኩት ደብዳቤ ላይ ለህዝቡ ደህንነት ሲባል ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መደረጉን ገልጸዋል። የጌዲዮ ተወላጆችና የዲላ ነዋሪዎች በዲላ ሊያካሂዱት የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ባለቀ ሰአት ሲከለከል ይሄ ለሁለተኛ ጊዜ ነው ይላሉ የሰልፉ አስተባባሪዎች።ሰላማዊ ሰልፉ እንዲሳካ የሄዱበትን ርቀት ...

Read More »

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ አመራር ተሰናበተ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ አመራር ዛሬ በይፋ ተሰናበተ። ዘጠኝ አባላት ያሉበት ጊዜያዊ የባላደራ ምክር ቤት መመስረቱንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል። ታሪካዊ በተባለው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉባዔ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ለኢትዮጵያ አንድነት ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ ገልጸዋል። ከመላ ሀገሪቱ የተወጣጡ የእምነቱ አባቶችና ምሁራን በተገኙበት እርቅ መፈጸሙንም ለማወቅ ተችሏል። የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የዘመናት ጥይቄ ...

Read More »

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን የተከሰተው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011)በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን የተከሰተው የጸጥታ ችግር በቁጥጥር ስር መዋሉን የክልሉ መንግስት አስታወቀ። ነዋሪዎች ግን አሁንም የጸጥታው ችግር እንደቀጠለ መሆኑን መግለጻቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ። የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል የሰላም ግንባታና ጸጥታ ቢሮ ሃላፊ አቶ አበራ ባየታ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት አራት ቀናት የነበረው ችግር አሁን ሙሉ በሙሉ ቆሟል። በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር የሚመራ የመንግስት ሃላፊዎች ቡድን ችግሩ ወደተከሰተበት አከባቢ ማምራቱን ...

Read More »

የቦይንግ ኩባንያ አብራሪዎቹን ተጠያቂ አደረገ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)የቦይንግ ኩባንያ በተከሰከሱት የኢንዶኔዢያና የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላኖች አብራሪዎቹን ተጠያቂ አደረገ። ከሶስት ሳምንት በፊት ኩባንያው በይፋ ሃላፊነቱን መውሰዱን ወደጎን በማድረግ አብራሪዎቹ የቦይንግን አውሮፕላኖች አጠቃቅም መስፈርት ባለሟሟላታቸው የተከሰተ አደጋ ነው ሲል አስታውቋል። የሁለቱ አየርመንገዶች ባላስልጣናት ቦይንግ አቋሙን ቀይሮ አብራሪዎቹን ተጠያቂ ባደረገበት አስተያየት ላይ እስከአሁን ምላሽ አልሰጡም። የኢትዮጵያ አየር መንገድ ስራ አስኪያጅ አቶ ተወልደ ገብረማርያም ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ የቦይንግ ...

Read More »

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ ስራ አመራር ሃላፊነቱን ሊያስረክብ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ ስራ አመራር ሃላፊነቱን ሊያስረክብ መሆኑን አስታወቀ። የመጅሊስ አመራር ስልጣኑን እንደሚለቅ ያስታወቀው እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ ነው። የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አይወክለንም በሚል ለአራት አመታት ሲቃወሙት የነበረው የመጅሊስ አመራር ስልጣኑን በነገው እለት እንደሚያስረክብ ፕሬዝዳንቱ ማስታወቃቸውን ሬዲዮ ፋና ዘግቧል። በትላንትናው ዕለት በገዛ ፈቃዳቸው ስልጣን ለመልቀቅ ጥያቄ ያቀረቡት የመጀሊሱ ፕሬዝዳንት ሼህ መሀመድ ...

Read More »

በአፋር ክልል ያለው ውጥረት እየተባባሰ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)በአፋር ክልል ያለው ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱ ተገለጸ። በተለይ ከውጭ እየገባ በክልሉ ላይ ጥቃት የሚያደርሰው የታጠቀ ሃይል እየተጠናከረ መምጣቱንም የአፋር የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ሊቀመንበር አቶ ጋአስ አህመድ ለኢሳት ገልጸዋል። እንደ እሳቸው አባባል የክልሉ መንግስትም ሆነ የፌደራል መንግስቱ በክልሉ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል ምንም እየሰሩ አይደሉም ብለዋል። በኢትዮ-ጅቡቲ መስመር የክልሉ ልዩ ሃይል ሲነሳ መከላከያ የአካባቢውን ሰላም ይጠብቃል በሚል ነበር ነገር ...

Read More »

በጋምቤላ በድብቅ ተገንብተው የተገኙት ካምፖች የማን እንደሆኑ ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)በጋምቤላ በድብቅ የተገኙትና በመከላከያ እየፈረሱ ያሉት ካምፖች በደቡብ ሱዳኑ ተቀናቃኝ ሬክ ማቻር ቡድን የሚመራ ሃይል የገነባው መሆኑን ለኢሳት የደረሰው መረጃ አመለከተ። እንደመረጃው ከሆነም በካምፑ የተገኙትና በጥቃቱ ህይወታቸው ያለፈው ታጣቂዎች ዜግነታቸው ኢትዮጵያዊ ነው የሚል መታወቂያ በኪሳቸው መገኘቱም ታውቋል። ይህን ተከትሎም በጋምቤላ ያለው አለመረጋጋት መቀጠሉ ነው የታወቀው። የአኝዋክ ሬዲዮ አዘጋጁ አግዋ ጊሎ ይህ ሁሉ ችግር ባለበት ሁኔታ ውስጥ የክልሉም ሆነ ...

Read More »

በቤንሻንጉል ጉምዝ የአማራ ተወላጆች መንግስት ይድረስልን አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉራ ወረዳ 4 ሺህ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቀረቡ። ልዩ ቦታው ቆታ መገንጠያ በሚባለው አካባቢ የሚገኙት የአማራ ተወላጆቹ ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች እየተከሰቱ መሆኑን ገልጸዋል። በተመሳሳይ በማንዱራ ወረዳ ባለው የጸጥታ ችግር ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ የአማራና የሌሎች ብሄር ተወላጆች መግለጻቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል። መንገድ ተዘግቷል ያሉት ነዋሪዎች ...

Read More »

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ ፕሬዝዳንት ስልጣን ለቀቁ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 21/2011)በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ህገወጥ ነው በሚል ሲወገዝ የነበረው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ ፕሬዝዳንት ከስልጣን መልቀቃቸው ተገለጸ። ፕሬዝዳንቱ ሼህ መሀመድ አሚን ጀማል እየተካሄደ ባለው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት ጉባዔ ላይ መልቀቂያ በማስገባት ከስልጣን በገዛ ፈቃዳቸው መነሳታቸው ታውቋል። ምክር ቤቱ እንዳስታወቀው ሼህ መሀመድ በጤና ችግር ምክንያት መቀጠል አልቻሉም። ለአራት ዓመታት በዘለቀው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቃውሞ መነሻ ከሆኑ ጉዳዮች አንዱ ...

Read More »