በቤንሻንጉል ጉምዝ የአማራ ተወላጆች መንግስት ይድረስልን አሉ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 22/2011)በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ዳንጉራ ወረዳ 4 ሺህ የሚጠጉ የአማራ ተወላጆች መንግስት እንዲደርስላቸው ጥሪ አቀረቡ።

ፋይል

ልዩ ቦታው ቆታ መገንጠያ በሚባለው አካባቢ የሚገኙት የአማራ ተወላጆቹ ለህይወታቸው አስጊ ሁኔታዎች እየተከሰቱ መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ በማንዱራ ወረዳ ባለው የጸጥታ ችግር ህይወታቸው አደጋ ውስጥ መውደቁን በወረዳው በተለያዩ ቀበሌዎች ነዋሪ የሆኑ የአማራና የሌሎች ብሄር ተወላጆች መግለጻቸውን የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

መንገድ ተዘግቷል ያሉት ነዋሪዎች ለእርሻ የወጡ ሰዎች አልተመለሱም ሲሉ ስጋታቸውን ገልጸዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለም በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና በኤታማዦር ሹሙ ጄነራል ሰዓረ መኮንን የሚመራ ልዩ የጸጥታና ደህንነት ምክክር በባህር ዳር ተካሂዷል።