የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ አመራር ተሰናበተ

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011) የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጅሊስ አመራር ዛሬ በይፋ ተሰናበተ።

ዘጠኝ አባላት ያሉበት ጊዜያዊ የባላደራ ምክር ቤት መመስረቱንም የደረሰን መረጃ አመልክቷል።

ታሪካዊ በተባለው የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጉባዔ ላይ የተገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች አንድነት ለኢትዮጵያ አንድነት ወሳኝ ሚና አለው ሲሉ ገልጸዋል።

ከመላ ሀገሪቱ የተወጣጡ የእምነቱ አባቶችና ምሁራን በተገኙበት እርቅ መፈጸሙንም ለማወቅ ተችሏል።

የኢትዮጵያ ሙስሊሞችን የዘመናት ጥይቄ በሚመልስ መልኩ የተጠናቀቀ ጉባዔ ነው ሲሉ አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።

አፈጻጸሙ ትኩረት ከተሰጠው የዛሬው ጉባዔ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ታላቅ ድል ነው ተብሏል።