አረና ትግራይ ህወሀት ላይ ክስ ሊመሰርት ነው

(ኢሳት ዲሲ–ሚያዚያ 23/2011) አረና ትግራይ ህወሀት ላይ ክስ ሊመሰርት መሆኑን አስታወቀ።

የአረና ሊቀመንበር አቶ አብረሃ ደስታ እንደገለጹት ፓርቲያቸው ህወሀት ላይ ክስ የሚመሰርተው በምርጫ ቦርድ አማካኝነት ለተቋቋመው የፓርቲዎች ምክር ቤት ነው።

በትግራይ የህወሀት አፈና ተጠናክሮ ቀጥሏል የሚለው አረና አባላቶቼ በእስር ላይ እየተሰቃዩ ነው ሲል አስታውቋል። በእንደርታ ህዝብ ላይ የሚፈጸመው በደል በማውገዝም ጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው እንደሚያደርግ ገልጿል።

ህወሀት በፓርቲዎች መሀል የተፈረመውን የቃልኪዳን ሰነድ ጥሷል ሲልም አረና ትግራይ ክስ አቅርቧል።