ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 4 ቀን 2006 ዓም ከንጋት ጀምረው አድማ መተው ያረፈዱት የባህር ዳር ከተማ ባጃጅ አሺከርካሪዎች ፤ መንግስት ለጥያቂያችን ምላሺ እስካልሰጠ ድርስ የስራ ማቆም አድማው ይቀጥላል ብለዋል፡፡ ከሶስት ሺህ በላይ ባጃጆች የሚርመሰመሱባት ባህርዳር ከጎዳናዋ የተሰወሩባት ከንጋቱ ጀምሮ ከከተማዋ ተሰውረው ህብረተሰቡ እና መንግስት ሰራተኛው በትራንስፖርት ችግር ውስጥ ወድቆ አርፍዷል፡፡ የባጃጅ አሺከርካሪ ማህበራትሃላፊነቱን በወሰዱበት በዚህ አድማ ፣ ...
Read More »Author Archives: Central
ፖሊስ በሲኤም ሲ የቤት ለቤት ፍተሻ አካሄደ
ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢሳት የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ፖሊስ በእያንዳንዱ ነዋሪ ቤት እየገባ መታወቂያ የጠየቀ ሲሆን የውጭ አገር ዜጎች ደግሞ ፓስፖርት፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡበት ቀን ፣ የቀጣሪ ድርጅታቸውን ስምና አድራሻ፣ መታወቂያና ሌሎችንም ጥያቄዎች ተጠይቀዋል። ተመሳሳይ ፍተሻዎች በሌሎች አካባቢዎች ሊኖር እንደሚችል መረጃዎች ያመለክታሉ። በቅርቡ የምእራብ መንግስታት አልሸባብ በኢትዮጵያ የሽብር ጥቃት ሊፈጽም እንደሚችል አስጠንቅቀው ነበር። መንግስትም 2 የአልሸባብ አሸባሪዎችን ...
Read More »ኦርኪድ 42 ሚሊዮን ብር እንዲከፍል ተወሰነበት
ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የወ/ሮ አዜብ መስፍን የእህት ልጅ የሆኑት የወ/ሮ አኪኮ ስዩም ንብረት የሆነው ኦርኪድ ቢዝነስ ግሩፕ 42 ሚሊዮን ብር ወይም 1 ሚሊዮን 700 ሺዩሮ ለ አቶ ዮናስ ካሳሁን እንዲከፍል ፍርድ ቤት መወሰኑን ሪፖርተር ዘግቧል። የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ውሳኔውን ያስተላለፈው ሁለቱተከራካሪወገኖችእ.ኤ.አ. ጁላይ 9 ቀን 2011 ለመጀመርያጊዜከተከበረውየደቡብሱዳንየነፃነትቀንላይበተፈጸመየሥራግንኙነትጋርበተገናኘ ነው። አቶዮናስ ካሣሁን፣ የተለያዩ መሣሪያዎችንና ማሽኖች ከጀርመን በማምጣት ለኦርኪድ በማከራየት ...
Read More »ሁለቱ የሱዳን ተፋላሚ ሃይሎች በ2 ወራት ውስጥ የሽግግር መንግስት ለመመስረት ተስማሙ
ሰኔ ፬(አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሰልቫኪር እና የተቃዋሚው መሪ ሪክ ማቻር ቀደም ብሎ የተፈረመውን የሰላም ስምምነት በማክበር በ60 ቀናት ውስጥ የሽግግር መንግስት ይመሰርታሉ። ተፋላሚ ሃይሎች ስምምነቱን የማይፈርሙ ከሆነ የኢጋድ አባል አገራት ማእቀብ እንደሚጥሉ ጠ/ሚ ሃይለማርያም ደሳለኝ ገልጸዋል።
Read More »በሃረር በጅምላ የተቀበሩ ሰዎች መቃብር መገኘቱን ተከትሎ ግጭት ተነሳ
ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቀበሌ 19 ልዩ ስሙ ሃመሬሳ ወይም መድፈኛ ጀርባ በሚባለው አካባቢ ሰኔ 2 ቀን 2006 ዓም በቁፋሮ ላይ የነበረ አንድ የግሪደር ሹፌር የተከማቹ አስከሬኖችን አግኝቷል። የ2ቱ አስከሬን ምንም አይነት የመበስበስ ምልክት አለማሳየቱን የገለጸው ወኪላችን፣ ግለሰቦቹ በቅርቡ የተገደሉ መሆናቸውን ያሳያል ብሎአል። አንደኛው ሟች እጆጁን ወደ ሁዋላ ለፊጥኝ ታስሮ የተገኘ ሲሆን ሌላው ደግሞ አይኖቹ በጨርቅ ተሸፍነዋል። የአራት ...
Read More »በዲላ በግብር የተማረሩ ነጋዴዎች ስራ አቆሙ
ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በበግምብ ገበያ አዳራሽ ውስጥ በጨርቃጨርቅ የንግድ ስራ ላይ የተሰማሩ ከ100 በላይ የሚሆኑ ነጋዴዎች ስራ ያቆሙት ፍትሃዊ ባልሆነ መንገድ ግብር እንድንከፍል ተጠይቀናል በሚል ምክንያት ነው። ነጋዴዎቹ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከደረጃ ሐ ወደ ደረጃ ለ እንዲሸጋገሩ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ወይም ቫት እንዲከፍሉ መታዘዛቸውን ለመቃወም ነጋዴዎቹ ወደ አዋሳ አምርተዋል። የክልሉ ባለስልጣናት ለነጋዴዎቹ ጥያቄ የሰጡት መልስ አልታወቀም። ...
Read More »በአዳማ በርካታ የንግድ ማስታወቂያዎች የአጻጻፍ መመሪያ አልተከተሉም በሚል ተሰረዙ
ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኦሮምያ ክልል መስተዳድር የክልሉን የማስታወቂያ አጻጻፍ መመሪያ አልተከተሉም ያላቸውን የበርካታ ድርጅቶች ማስታወቂያዎች መሰረዙ ታውቋል። የንግድ ማስታወቂያቸውን በአማርኛ ወይም በእንግሊዝኛ የጻፉ የንግድ ድርጅቶች ማስታወቂያቸውን እንዲለውጡና በኦሮምኛ እንዲጽፉ ሲታዘዙ ፣ ከማስታወቂያ ሰሌዳው ላይ በተጨማሪ ቋንቋ ለመጻፍ የሚፈልጉ ድርጅቶች ደግሞ በኦሮምኛ የተጻፈውን በጉልህ ሁኔታ ከላይ ካስቀመጡ በሁዋላ በተጨማሪ ቋንቋ የተጻፈውን በትንሹ ከታች እንዲያስቀምጡ ታዘዋል። የመስተዳድሩ ባለስልጣናት በአማርኛ ...
Read More »በሚቀጥለው የበጀት አመት የ21 ቢሊዮን ብር ጉድለት እንደሚኖር ተገለጸ
ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰኔ 30/2006 በሚጠናቀቀውየዘንድሮውበጀትዓመትከተያዘው 155 ነጥብ 9 ቢሊየንብር ውስጥ 16 ነጥብ 6 ቢሊየንብርየበጀትጉድለትየነበረሲሆን፣ በ2007 የበጀት ጉድለቱ አድጎ 21 ነጥብ 2 ቢሊየን ብርእንደሚደርስ ታውቋል። ከ2007 አጠቃላይበጀትማለትም 178 ቢሊየን 565 ሚሊየን 906 ሺህ 571 ብርውስጥከሃገርውስጥ፣ከውጭአገርዕርዳታናብድርበድምሩብር 157 ቢሊየን 357 ሚሊየን 947 ሺህ 657 ያህልገንዘብለመደጎምየታቀደመሆኑንምየገንዘብናኢኮኖሚልማትሚኒስትሩአቶሶፊያንአህመድለፓርላማው ካቀረቡትሪፖርትለመረዳትይቻላል፡፡ የቀጣዩዓመትበጀትውስጥ 34 ቢሊየን 304 ሚሊየን 872 ሺህ 764 ብርበብድርናዕርዳታማለትም 17 ነጥብ 5 ቢሊየንብርበብድር፣ ...
Read More »ቴዎድሮስ አድሃኖም አል ሲሲ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጠየቁ
ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአባይ ግድብ ጋር ተያይዞ በአገር ውስጥ ግብጽን የማጥላላቱ ዘመቻ በስፋት የቀጠለ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአዲሱ የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ የጉብኝት ጥያቄ አቅርበዋል። ኢትዮጵያ ግብጽን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ሲገልጹ፣ አል ሲሲም ከኢትዮጵያ ጋር የመተባባር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል። የኢትዮጵያ መንግስት የፖሊቲካ ተቃዋሚዎችን ከግብጽ ጋር ይሰራሉ በማለት በመገናኛ ...
Read More »የሰኔ 1 ሰማእታት በሀገር ቤት እና በውጪ ሀገራት በልዩ ስነ-ስርዓት ታስበው ዋሉ።
ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ምርጫ 97ትን ተከትሎ የዛሬ 9 ዓመት ሰኔ 1 ቀን በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማእታት ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የውጪ ሀገራት በልዩ ልዩ ፕሮግራም ተዘክረዋል። በኢትዮጰያ ሰማያዊ ፓርቲ፣አንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ሰማእታቱን በተለያዩ ፕሮግራሞች አስበው የዋሉ ሲሆን፣ በተለያዩ የአውሮፓ እና አሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጰያውያንም በደማቅ ስነ-ስርዓቶች መታሰቢያ አድርገውላቸዋል። ሰማያዊ ፓርቲ ባሰናዳው መታስቢያ ፐሮግራም ላይ የተገኙት ፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፦ ...
Read More »