ቴዎድሮስ አድሃኖም አል ሲሲ ኢትዮጵያን እንዲጎበኙ ጠየቁ

ሰኔ ፫(ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከአባይ ግድብ ጋር ተያይዞ በአገር ውስጥ ግብጽን የማጥላላቱ ዘመቻ በስፋት የቀጠለ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴዎድሮስ አድሃኖም ለአዲሱ የግብጽ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አል ሲሲ የጉብኝት ጥያቄ አቅርበዋል።

ኢትዮጵያ ግብጽን የመጉዳት ፍላጎት እንደሌላት ውጭ ጉዳይ ሚኒሰትሩ ሲገልጹ፣ አል ሲሲም ከኢትዮጵያ ጋር የመተባባር ፍላጎት እንዳላቸው ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት የፖሊቲካ ተቃዋሚዎችን ከግብጽ ጋር ይሰራሉ በማለት በመገናኛ ብዙሃን እያወገዛቸው ሲሆን፣ በሌላ በኩል ግን  ባለስልጣኖች ከግብጽ ጋር ያላቸውን ግንኙነት ለማሳደግ ከፍተኛ የዲፐሎማቲክ ዘመቻ እያደረጉ ነው።