የሰኔ 1 ሰማእታት በሀገር ቤት እና በውጪ ሀገራት በልዩ ስነ-ስርዓት ታስበው ዋሉ።

ሰኔ ፪(ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-“ምርጫ 97ትን ተከትሎ  የዛሬ 9 ዓመት  ሰኔ  1 ቀን  በግፍ የተጨፈጨፉ ሰማእታት ኢትዮጵያን ጨምሮ  በበርካታ የውጪ ሀገራት  በልዩ ልዩ ፕሮግራም  ተዘክረዋል።

በኢትዮጰያ ሰማያዊ ፓርቲ፣አንድነት ፓርቲ እና መኢአድ ሰማእታቱን በተለያዩ ፕሮግራሞች አስበው የዋሉ ሲሆን፣ በተለያዩ የአውሮፓ እና አሜሪካ ከተሞች የሚኖሩ ኢትዮጰያውያንም  በደማቅ ስነ-ስርዓቶች መታሰቢያ አድርገውላቸዋል።

ሰማያዊ ፓርቲ ባሰናዳው መታስቢያ ፐሮግራም ላይ የተገኙት ፐሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም፦ “ዛሬየምናስበውቀን <<በኔላይምንግዴታይጥላል?>> ብለንመጠየቅአለብን”ብለዋል።

“ግፍንለመግፋትየሞቱሰዎችንስናስብ፤ግፍንተቀብለንለቀጣዩትውልድማስተላለፍየለብንም፡፡” ሲሉም ፕሮፌሰርመስፍንአክለዋል።

ሰኔ 1 ቀን 1997 ዓመተ ምህረት “ድምጻችን ይከበር!” በማለት ጥያቄ ባቀረቡ ወገኖች ላይ ታጣቂዎች በከፈቱት ተኩስ በርካታ ሰዎች መገደላቸው ይታወሳል።

ከሙዋቾቹ መካከል  የ15 ዓመቱ ታዳጊ ነቢይ ዓለማየሁ፣ መንታ የሆኑ ታዳጊ ወንድማማቾች፣ እናቶች እና አዛውንቶች ይገኙበታል።