(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) በሜክሲኮ በደረሰው ርዕደ መሬት ፍርስራሽ ስር የተቀበሩ ሕጻናትን ለማትረፍ የነፍስ አድን ሰራተኞች እየተሯሯጡ መሆናቸው ተነገረ። ሕጻናትና ታዳጊ ልጆች ከርእደ መሬቱ ጋር በተያያዘ ከተደረመሰው ትምህርት ቤት ሕንጻ ስር ሆነው የአድኑን ጥሪ እያሰሙ መሆናቸው ተነግሯል። በሬክተር ስኬል 7 ነጥብ 1 በተመዘገበው ርእደ መሬት እስካሁን ከ250 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። የሜክሲኮው ርዕደ መሬት ያልተጠበቀና ድንገተኛ ነው።በሜክሲኮ መናገሻ ከተማ የደረሰውን የመሬት ...
Read More »Author Archives: Central
የኢጋድ አባል ሀገራት የደቡብ ሱዳንን ችግር ከመፍታት ይልቅ ብሔራዊ ጥቅማቸውን እያስቀደሙ ነው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) የደቡብ ሱዳን አማጽያን መሪና የቀድሞው ምክትል ፕሬዝዳንት የኢጋድ አባል ሀገራት የደቡብ ሱዳንን ችግር ከመፍታት ይልቅ ብሔራዊ ጥቅማቸውን እያስቀደሙ ችግር መፍጠራቸውን ገለጹ። ሬክ ማቻር በኢጋድ አባል ሀገራት ላይ ተስፋ መቁረጣቸውን ያስታወቁት ባለፈው ሀሙስ ለተባበሩት መንግስታት ዋና ጸሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በጻፉት ደብዳቤ መሆኑን መረዳት ተችሏል። የአማጽያኑ መሪ ዶክተር ሬክ ማቻር እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር መስከረም 14/2017 የጻፉትና በሱዳን ትሪቡን በኩል ...
Read More »ሀገራት ከአምባገነኑ የህወሃት አገዛዝ ጋር ያላቸውን ግንኙነት እንዲመረምሩ ኢትዮጵያን ጠየቁ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010)ካናዳ ከአምባገነኑ የህወሃት አገዛዝ ጋር ያላትን ግንኙነት እንድትመረምር በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮጵያን ጠየቁ። በጀርመን የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ደግሞ አሜሪካ ለህወሀት መንግስት የምታደርገውን ድጋፍ እንድታቆም ጠይቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ ጥያቄውን ያቀረቡት በካናዳ ቶሮንቶና በጀርመን ፍራንክፈርት ባካሄዱት የተቃውሞ ትዕይንት ነው። እነዚህ የተቃውሞ ትዕይንቶች በዓለም ዓቀፍ ደረጃ በኢትዮጵያውያን ግብረ ሃይል የተዘጋጁ ሲሆን ባለፈው ሰኞ በዋሽንግተን ዲሲም መካሄዱ የሚታወስ ነው። በዓለም ዓቀፍ የነጻነት ትግል ድጋፍ ጥሪ ...
Read More »በቢልና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን እንዲሁም በሌሎች ለጋሾች የሚሰጠው ድጋፍ ለአማካሪ ድርጅት በሚደረግ ክፍያ እየባከነ መሆኑ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) የኢትዮጵያን የግብርና ስርአት ለማሻሻልና አርሶአደሮችን ተጠቃሚ ለማድረግ በቢልና ሚሊንዳ ጌት ፋውንዴሽን እንዲሁም በሌሎች ለጋሾች የሚሰጠው ድጋፍ ከተግባራዊ ስራ ይልቅ ለአማካሪ ድርጅት በሚደረግ ክፍያ እየባከነ መሆኑን ምንጮች ገለጹ። የኢትዮጵያ ግብርና ማበልጸጊያ ማእከል ዋና ዳይሬክተር አቶ ካሊድ ቦምባ የዘመዶቻቸው ንብረት ለሆነውና ፈርስት ኮልሰንታሲ ለተባለው ድርጅት በእርዳታ የሚመጣውን ገንዘብ እያሻገሩ እንደሆነም ተመልክቷል። የጉዳዩን አሳሳቢነት በተመልከተ የሚመለከታቸው አካላት ለጸረ ሙስና ኮሚሽን ...
Read More »የኢትዮጵያ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ይዘቶች ብሔሮችን ከብሔሮች ጋር የሚያጋጩና ጦርነት ቀስቃሽ ናቸው ተባለ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010) የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣን ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የሚሰራጩ የመገናኛ ብዙሃን ይዘቶች ብሔሮችን ከብሔሮች ጋር የሚያጋጩና ጦርነት ቀስቃሽ ናቸው በማለት አስጠነቀቀ። በህወሃቱ ነባር ካድሬ አቶ ዘርአይ አስገዶም ፊርማ የወጣው ማሳሰቢያ በጥቅል የተቀመጠና ዝርዝር ይዘት የሌለው በመሆኑ ሆነ ብሎ ጋዜጠኞችን ለማሸማቀቅና ለማስፈራራት የወጣ ሊሆን እንደሚችል ባለሙያዎች ይገልጻሉ። በኦሪገን ዩኒቨርስቲ የሚዲያና ኮሚኒኬሽን ዕጩ ዶክተርና መምህር አቶ እንዳልካቸው ሃይለሚካኤል ለኢሳት እንደገለጹት ከዚህ ...
Read More »በኬንያ ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትዕዛዝ በርካታ ስቃይና በደል እየደረሰባቸው መሆኑ ታወቀ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 11/2010)በኬንያ ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን በኢትዮጵያ ባለስልጣናት ትዕዛዝ በርካታ ስቃይና በደል እየደረሰባቸው መሆኑን ሂዩማን ራይትስ ዎች አጋለጠ። የሂዩማን ራይትስ ዎች ከፍተኛ ተመራማሪ ፍሌክስ ሆርን እንደገለጹት ኢትዮጵያውያኑ ስደተኞች ረጅም እጅ ባላቸው የኢትዮጵያ ባለስልጣናት አማካኝነት በኬንያም እየኖሩ ይገረፋሉ፣ከፍተኛ ስቃይም እየደረሰባቸው ይገኛል። በተለይ በናይሮቢ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የኬንያ ፖሊሶችን በገንዘብ እየደለለ ስደተኞቹን አሳስሮ ወደ ሀገር ቤት በግዴታ እንዲመለሱ እያደረገ መሆኑንም ሂዩማን ራይትስ ...
Read More »በሰርባ መስኖ ተፋሰስ ፕሮጀክት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በተባሉ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ላይ ክስ ተመሰረተ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010) የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ በሰርባ መስኖ ተፋሰስ ፕሮጀክት ላይ ጥቃት ፈጽመዋል ባላቸው የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ላይ ክስ መሰረተ። በክስ መዝገቡ ላይ እንደተብራራው ታጣቂዎቹ በፈጸሙት ጥቃት ሁለት ሰዎች ሲገደሉ አምስት ቆስለዋል። ባለፈው ዓመት መጋቢት 25/2009 ተፈጸመ የተባለውን ጥቃት በወቅቱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ሃላፊነት እንደሚወስድ መግለጹን መዘገባችን ይታወሳል። መጋቢት 25 2009 የአርበኞች ግንቦት ሰባት ታጣቂዎች ...
Read More »ተላልፈው የተሰጡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከፍተኛ አመራርን በተመለከተ የሶማሊያ ፓርላማ መርማሪ ቡድን አቋቋመ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010) ሶማሊያ ውስጥ ታፍነው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው የተሰጡት የኦጋዴን ብሔራዊ ነጻ አውጭ ግንባር ከፍተኛ አመራርን በተመለከተ የሶማሊያ ፓርላማ መርማሪ ቡድን አቋቋመ። ድርጊቱ የተፈጸመው የብዙዎቹ የሶማሊያ ፓርላማ አባላት ለሃይማኖታዊ ጉዳይ ሳውዲ አረቢያ በነበሩበት ወቅት እንደሆነም ተመልክቷል። የኦጋዴን ነጻ አውጭ ግንባር/ኦብነግ ከፍተኛ አመራር አባል የሆኑት አቶ አብዲካሪን ሼህ ሙሴ ከወር በፊት በነሀሴ 2009 በደቡብ ሶማሊያ የወደብ ከተማ ኪስማዩ ላይ ...
Read More »የአባይ ወንዝ ከ25 ሔክታር በላይ በእምቦጭ አረም መወረሩ ተገለጸ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010) የአባይ ወንዝ ከ25 ሔክታር በላይ በእምቦጭ አረም መወረሩ አስደንጋጭ እንደሆነባቸው የባህርዳር ነዋሪዎች ገለጹ። አረሙን ለመከራከል ደግሞ የፌደራል መንግስቱ የሚጠበቀውን ያህል ምላሽ አለመስጠቱ ችግሩ እየተባባሰ እንዲመጣ አድርጎታል ይላሉ። ከጣና ሃይቅ አልፎ በመሄድ የአባይ ወንዝን እየወረረ ያለውን የእምቦጭ አረም ለመከላከል የፌደራል መንግስቱ የሚጠበቅበትን እንዳልሰራ በአማራ ክልላዊ መንግስት ባለስልጣናት የቀረበውን ቅሬታ ተከትሎ የኢሳት ወኪሎች ያናገሯቸው የባህርዳር ነዋሪዎች የተሰማቸውን ሀዘን ገልጸዋል። ...
Read More »አቶ አባይ ጸሀዬ ለሕክምና ከሀገር መውጣታቸው ተሰማ
(ኢሳት ዜና–መስከረም 10/2010) በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ሌብነት በግንባር ቀደምትነት ሲጠቀሱ የነበሩትና ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ ተጥሎባቸው የቆየው አቶ አባይ ጸሀዬ ለሕክምና ከሀገር መውጣታቸውን ምንጮች ለኢሳት ገለጹ። ይህ በእንዲህ እንዳለ ራሳቸውን በኮሚቴ ያደራጁ የትግራይ ምሁራንና የሀገር ሽማግሌዎች በሌብነት ላይ የተጀመረው ዘመቻ እንዲቆምና የታሰሩትም እንዲፈቱ መጠየቃቸው ተሰምቷል። በኢትዮጵያ ውስጥ በሚካሄደው ሌብነት በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሱት አቶ አባይ ጸሃዬ ናቸው። ይህን ተከትሎም ከሀገር እንዳይወጡ እገዳ ...
Read More »