(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት3/2011) በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በማንኛውም ብሔር ላይ የማፈናቀል ሙከራም ይሁን ሌላ ጉዳት አልደረሰም ሲል የኦሮሚያ ክልል መንግስት ገላጻ። የክልሉ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ሃላፊ አቶ አድማሱ እንደገለጹት በኦሮሚያ ክልል ውስጥ በተለይም በቄለም ወለጋ ዞን በሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆች ላይ ምንም አይነት ጉዳት አልደረሰም። ቢሮ ሃላፊው ይሕንን መግለጫ ለመስጠት የተገደዱት “በቄለም ወለጋ ዞን የሚገኙ የአማራ ብሄር ተወላጆች አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ ...
Read More »Author Archives: Central
የተለያዩ አካላት በአውሮፕላን አደጋው በጠፋው የሰው ህይወት ማዘናቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት1/2011ፕሬዝዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴን ጨምሮ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች እና ክልላዊ መንግስታት እንዲሁም የዓለም ሀገራትና ዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች በኢትዮጵያ ዓየር መንገድ የአውሮፕላን አደጋ በጠፋው የሰው ህይወት ማዘናቸውን ገለጹ’። የአውሮፕላን አደጋው መድረሱን ተከትሎም በርከታ የዓለም ሀገራት ህዝቦች፣ የሀገራት መሪዎች እና የዓለም አቀፍ ተቋማት መሪዎች የተሰማቸውን ሀዘን እየገለጹ ይገኛሉ። ፕሬዝዳንት ሳህለወረቅ ዘውዴና ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን ጨምሮ የፌዴራል መስሪያ ቤቶች እና ...
Read More »በቄለም ወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች አካባቢውን ለቀው ውጡ መባላቸውን ገለጹ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 2/2011)በቄለም ወለጋ የሚኖሩ የአማራ ተወላጆች አካባቢውን ለቃችሁ ውጡ በሚሉ ሃይሎች እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገለጹ። የሚመለከተው አካል አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጠ ችግሩ የሕይወት መስዋዕትነት የሚያስከፍል መሆኑንም ተናግረዋል። በአካባቢው ያለው መከላከያም ሆነ የጸጥታ ሃይሉ እንዲሁም የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ ምንም አይነት ምላሽ መስጠት እንዳልቻሉ ነው የተገለጸው። በቄለም ወለጋ ዛሬ ላይ ችግር የገጠማቸው ዜጎች በ1977ቱ የሰፈራ ፕሮግራም ከወሎ ተነስተው በቄለም ወለጋ እንዲሰፍሩ የተደረጉ የአማራ ...
Read More »የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብሔራዊ የሐዘን ቀን አወጀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 1/2011)የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተከሰከው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ለሞቱት 157 ሰዎች የዛሬው ቀን መጋቢት 2/ 2011 ዓ.ም ብሔራዊ የሐዘን ቀን እንዲሆን አወጀ። እናም የሪፐብሊኩ ሰንደቅ አላማ በዛሬው እለት በመላው የአገሪቱ ግዛቶች፣ በኢትዮጵያ መርከቦች ፥ በውጭ ሐገር ባሉ ኤምባሲዋችና የቆንስላ ጽህፈት ቤቶች ዝቅ ብሎ ይውለበለባል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የደረሰበትን አይነት ቦይንግ 737 አውሮፕላን ተጨማሪ መመሪያ እስኪስጥ ድረስ ...
Read More »የጌዲዮ ተፈናቃዮች ሰቆቃ እየከፋ መምጣቱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 2/2011)ከጌዲዮ የተፈናቀሉ ዜጎች ሞትና ሰቆቃ እየከፋ መምጣቱን ተፈናቃዮቹ ገለጹ። ተፈናቃዮቹ እንደሚሉት በየቀኑ 4ና 5 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው እያለፈ ነው። ከችግሩ አስከፊነት የተነሳ የሞቱትን ሰዎች የመቅበር አቅም ስለሌለ የከተማዋ ማዘጋጃ ቤት ነው አስከሬኖቹን እየሰበሰበ የሚቀብረው ብለዋል ተፈናቃዮቹ። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣የኦሮሚያ ፕሬዝዳንትና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ተፈናቃዮቹን ጎብኝተው በ6 ወር ውስጥ ድጋፍ ይደረጋል ቢሉም የተባለውን ድጋፍ ግን ማየት አለመቻላቸውን ነው ...
Read More »ሰላም ወዳድ ዜጋ ሁሉ ጦርነት ሊነሳ ይችላል ብሎ ስጋት ሊገባዉ አይገባም
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011)የትግራይ ሕዝብና መንግስት ጦርነታቸዉ ከድህነት ጋር በመሆኑ ማንኛውም ሰላም ወዳድ ዜጋ ሁሉ ጦርነት ሊነሳ ይችላል ብሎ ስጋት ሊገባዉ አይገባም ሲል ይክልሉ ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ገለጸ። የአማራ ክልል ምክር ቤት ከትግራይ በኩል በመቀሌ የመሸገ ቡድን ትንኮሳ እየተፈጸመብኝ ነው በሚል የተለያዩ ውሳኔዎች ማስተላለፉን አስመልክቶ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት መግለጫ አውጥቷል፡፡ የአማራ ክልል ምክር ቤት አስተላለፉዋቸው ከተባሉት ጉዳዮች መካከል ...
Read More »ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ አበባ ሁሉን መሰብሰብ የምትችል ተደርጋ ልትገነባ ይገባል አሉ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011) ጠቅላይ ሚንስትር አቢይ አሕመድ አዲስ አበባን ነዋሪዎቿን ብቻ ሳይሆን ሁሉን መሰብሰብ የምትችል ተደርጋ ልትገነባ ይገባል ሲሉ ገለጹ፡፡ ዶክተር አብይ አሕመድ የዓለም ዐቀፍ ሴቶች ቀንነ ለማበር በተዘጋጀ ስብሰባ ላይ ባሰሙት ንግግር አዲስ አበባን ለመከፋፈልና የእኔ ለማለት ከመቸኮል ይልቅ የማያግባቡ ጉዳዮችን በመነጋገር መፍታትና መጓዝ ያስፈልጋል ብለዋል። ጠቅላይ ሚንስትሩ አዲስ አበባን ብተመለከተ የተናገሩት ሀሳብ የኦሮሚያ መንግስት የአዲስ አበባ ባለቤትነታችን ሳይረጋገጥ ...
Read More »ኦዴፓ የአዲስ አበባ የኦሮሞ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ይሰራል
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011)የአዲስ አበባ የኦሮሞ ባለቤትነትን ለማረጋገጥ የተጀመሩ ስራዎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ገለጸ። በአዲስ አበባና ኦሮሚያ መካከል ያለው የአስተዳደር የወሰን ጉዳይ እልባት ሳይሰጠው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ መተላለፋቸው ተገቢ አይደለም ሲልም ተቃውሞውን አሰምቷል። የክልሉ መንግስት በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ባወጣው መግለጫ የኦሮሚያ ክልል ጥያቄ እያነሳባቸው ባሉና የክልሉን ወሰን አልፈው የተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች በእጣ ለተጠቃሚዎች የማስተላለፍ ሂደት እንዳይተገበርም ...
Read More »አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ስልጣናቸው ለቀቁ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 27/2011) አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከአማራ ክልል ፕሬዝዳንትነት ስልጣናቸው በገዛ ፈቃዳቸው ለቀቁ። በምትካቸው ዶክተር አምባቸው መኮንን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሹመዋል። የአማራ ክልል ርእሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ቃለ መሀላ ከፈጸሙ በኋላ ፖለቲካውን ከክረት በማላቀቅና ሀገሪቱን ከውጥረት በማውጣት አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባት ለማድረግ የበኩሌን እወጣለሁ ብለዋል። የአማራ ክልልን በርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በዛሬው እለት መልቀቂያ አስገብተው ...
Read More »የነ አቶ ኤርሚያስ አመልጋ የክስ መቃወሚያ ውድቅ ሆነ
(ኢሳት ዲሲ–የካቲት 26/2011)ከኢምፔሪያል ሆቴል ሽያጭ ጋር በተያያዘ በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሠረተባቸው አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ 11 ተከሳሾች አቅርበውት የነበረው የክስ መቃወሚያ ውድቅ ተደረገ። በዚሁም መሰረት አቶ ኤርሚያስ አመልጋን ጨምሮ 11 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃላቸውን እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡ በሜቴክ የቀድሞ ዋና ዳይሬክተር ሜጀር ጄኔራል ክንፈ ዳኘው የክስ መዝገብ የተካተቱት ተከሳሾች አቶ ኤርሚያስ አመልጋ፣ የሪቬራ ኢንተርናሽናል ሆቴልና የፒቪሲ ፕሮፋይል ፋብሪካ ባለቤት አቶ ...
Read More »