Author Archives: Central

የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር የዜጎችን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ማስከበር ሊሆን እንደሚገባ ተገለጸ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 11/2011)የዜጎችን መሠረታዊ ሰብዓዊ መብቶች ማስከበር የመንግሥት ተቀዳሚ ተግባር በመሆኑ ይህንኑ እንዲወጣ የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ ጠየቀ። የኢትዮጵያ ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ አመራሮች ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስና ሌሎችንም ጨምሮ መንግስት ሕግን የማስከበርን ሃላፊነት እየተወጣ አይደለም ብለዋል። የፓርቲው መግለጫ እንዳመለከተው እጅግ በርካታ ዜጎች መፈናቀል እየደረሳባቸው ነው። መንግሥት የተፈናቀሉትን ዜጎች ወደመኖሪያ ቀዬአቸውና ቤቶቻቸው ለመመለስ ከመሞከር ይልቅ ወደ ብሔር ይዞታቸው \”የጎሣ ግዛታቸው\” መልሶ ለማቋቋም ...

Read More »

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ለማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ጥሪ አቀረበ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2011) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከሀሰት ዜና እና ከጥላቻ ንግግሮች እንዲቆጠቡ ጥሪ አቀረበ። ኢትዮጵያ በማህበራዊ ሚዲያ የሀሰት ዘመቻ አትፈርስም ያለው የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ አሁን በሃገሪቱ ላለው ውጥረት ግን መነሻ ምክንያት ነው ብሏል። በዚህ የለውጥ ወቅት ግጭት በመቀስቀስና ብጥብጥ በማንገስ የህዝብ መፈናቀልና ስቃይን ለማባባስ በማህበራዊ ሚዲያ ከፍተኛ ጥረት በመደረግ ላይ እንደሚገኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አመልክቷል። ...

Read More »

በኦቢኤን ለሚሰሩ ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ ከተሰሩ ኮንዶሚኒየም ቤቶች እንዲሰጣቸው ተደረገ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 10/2011)በኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትወርክ /ኦቢኤን/ ለሚሰሩ ከ40 በላይ ጋዜጠኞች በአዲስ አበባ ከተሰሩ ኮንዶሚኒየም ቤቶች በከተማዋ ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ትዕዛዝ ያለእጣ በነጻ እንዲሰጣቸው ተደረገ ። ለኢሳት በደረሰው መረጃ መሰረት የስም ዝርዝራቸው የተካተተበት የኦቢኤን ጋዜጠኞች ኮንዲሚኒየም ቤት እንዲሰጣቸው ለከተማዋ ከንቲባ ትብብር ይደረግ ብሎ የጻፈው የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ፕሬዝዳንት ጽህፈት ቤት ነው። ጋዜጠኞቹ ስም ዝርዝራቸው ሲተላለፍ በኦቢኤን ውስጥ በከፍተኛ አመራር ላይ ...

Read More »

በምዕራብ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት አምስት ሰዎች ተገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት10/2011)በኦሮሚያ ክልል ምእራብ ወለጋ ዞን ታጣቂዎች ባደረሱት ጥቃት የአምስት ሰዎች መገደላቸው ተነገረ። የኦሮሚያ ክልል የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው ጥቃቱ የደረሰው በምእራብ ወለጋ ዞን ነጆ ወረዳ በሁምነ ዋቃዮ ቀበሌ  ውስጥ ነው። አካባቢው የኦነግ ታጣቂዎች በስፋት የሚንቀሳቀሱበት መሆኑ ይታወቃል። በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ወለጋ ዞን የተፈጸመውን ጥቃት ያደረሱት የጦር መሳሪያ ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ያልታወቁ ሃይሎች ናቸው ሲል የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ገልጿል። በጥቃቱም ...

Read More »

ሀገር አቀፍ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ላልተወሰነ ጊዜ ተራዘመ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2011)በቀጣዩ ወር ሊካሄድ የነበረው 4ኛው ሀገር ዐቀፍ የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም መወሰኑ ተነገረ። ሪፖርተር እንደዘገበው  በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የሚመራው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ  ኮሚሽን ውሳኔውን ያሳለፈው ከትናንት በስትያ  ቅዳሜ ዕለት በተጠራ ስብሰባ ብዙ ክርክር ከተካሄደበት በኋላ ነው፡፡ በዚህ መሠረት ማዕከላዊ ስታትስቲክስ ኤጀንሲ የቆጠራ ቁሶችን ወደ ክልሎች ማሰራጨቱን እንዲያቋርጥ፤ ያሰራጫቸውንም ወደ ማዕከሉ እንዲመልስ ታዟል ተብሏል ፡፡ ...

Read More »

በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ  አካባቢ ግጭት ተቀሰቀሰ

 (ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2011)በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ  አካባቢ ግጭት መከሰቱ ተነገረ። የግጭቱ መንስኤ ረዥም ጊዜ የቆየና በዘላቂነት ለመፍታት ሂደት ላይ የነበረ የወሰን አለመግባባት ነው ተብሏል፡፡ በግጭቱ ሰዎች ሞተዋል ከመባሉ ውጭ ስለደረሰው የጉዳት መጠን የተገለጸ ነገር የለም። የምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ከኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ወረዳዎች የሚዋሰን ነው። ግጭቱ ያጋጠመው በምንጃራ ሸንኮራ ወረዳ አሞራቢት ቀበሌ ከሚዋሰኑት ፈንታሌና ቦሰት ወረዳዎች አዋሳኝ ...

Read More »

በጉፋ ዞን ሁለት ወረዳዎች የተፈናቀሉ 37ሺ የሚሆኑ ዜጎች ለከፋ ችግር መጋለጣቸው ታወቀ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2011) በጉፋ ዞን በባስኬቶ ልዩ ወረዳና በመሎ ወረዳ የተፈናቀሉ 37ሺ የሚሆኑ ዜጎች ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገለጹ። እነሱ እንደሚሉት ከሆነ በሁለቱ ወረዳዎች አመራሮች መካከል በቀበሌ ይገባኛል ጥያቄ የተነሳው ግጭት በአስር ሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች መፈናቀል ምክንያት ሆኗል። በዚህ ግጭት የ11 ቀበሌዎች ነዋሪዎች የተፈናቀሉ ሲሆን ማንም የሚደርስላቸው አካል ባለማግኘታቸው በረሃብ እየሞቱ መሆናቸውንም ነዋሪዎቹ ለኢሳት ያደረሱት መረጃ ያመለክታል። ስምንት ወራት ...

Read More »

ግሎባል አልያንስ ለጌዲዮ ተፈናቃዮች በሶስት ቀን ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ ሰበሰበ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2011)ለጌዲዮ ተፈናቃዮች እርዳታ በግሎባል አልያንስ ዋና ዳይሬክተር ታማኝ በየነ አስተባባሪነት የተጀመረው የገንዘብ ማሳባሰብ ሂደት በሁለት ቀን ወስጥ ብቻ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ መገኘቱ ኢትዮጵያዊያን ችግር ሲደርስባቸው በሕብረት እንደሚቆሙ ያሳየ መሆኑ ተገለጸ። የግሎባል አልያንስ ዋና ዳይሬክተር ታማኝ በየነ በበኩሉ ኢትዮጵያዊያንን በማመስገን በጌዲዮ ያሳየነው የትብብርና የአንድነት መንፈስ በሌሎችም ጉዳዮች ላይ እንዲቀጥል ጥሪ አቅርቧል። ይሕ በእንዲህ እንዳለም የአዲስ አበባ አስተዳደር ለጌዲዮ ...

Read More »

አቶ ነዓምን ዘለቀ በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ከድርጀቱ አገለሉ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 9/2011)የአርበኞች ግንቦት 7 የስራ አስፈጻሚ ኮሜቴ አባልና የንቅናቄው የውጭ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ነዓምን ዘለቀ በገዛ ፈቃዳቸው ራሳቸውን ከድርጀቱ ማግለላቸውን አስታወቁ። አቶ ነአምን ዘለቀ ለኢሳት በላኩት መግለጫ እራሳቸውን በገዛ ፈቃዳቸው ከንቅናቄው ያገለሉት ከኤርትራ በረሃ ወደ አገር ቤት እንዲገቡ የተደረጉትን የአርበኞች ግንቦት 7 የቀድሞ ታጣቂዎች በተገባላቸው ቃል መሰረት ምንም አለመደረጉና ሂደቱ መጓተቱ  እንቅልፍ ስለነሳኝ ነው ብለዋል። እናም ከካምፕ ውጭ  በዘርፈ ...

Read More »

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከካራማራ ጦርነት ተሳታፊዎች ጋር ተወያዩ

(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 6/2011) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን በካራማራ ጦርነት የተሳተፉ ከቀድሞ የሰራዊቱ ተወካይ አባላት ጋር መወያየታቸው ተነገረ። የሰራዊት አባላቱ የካራማራ ድልመንግስት ተገቢውን የታሪክ ትኩረት እና ክብደት እንዲሰጠው ጠይቀዋል። የሃገርን ታሪክ አጥርቶ ለትውልድ ለማስጨበጥ እና ጠቃሚ ትምህርት ለመውሰድ ቅብብሎሹ በይዘቱ የተሟላ መሆን እንደሚገባው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ተናግረዋል። ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ለካራማራ ድል መንግስት ተገቢውን ...

Read More »