(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 2011/2011) ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ አዲስ አበባ የሁሉም ሆና እያለ የአንዱ ብቻ ናት መባሉ ትክክል አይደለም ሲሉ ገለጹ ። አንደኛ ዓመት የስልጣን ጊዜያቸውን መነሻ በማድረግ በወቅታዊው የሀገሪቱ ጉዳይ ላይ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ ዶክተር አብይ እንደገለጹት በህገመንግስቱ የተቀመጠው የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ያላት የልዩ ጥቅም መብት ግን ሊረጋገጥ ይገባል። ይህንን ሀሳብ ደግሞ ኦሮሞ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ሰው ሊደግፈው ...
Read More »Author Archives: Central
ቦይንግ ኩባንያ በ737 ማክስ አውሮፕላን ላይ የነበረውን “ኤምካስ” የተሰኘው መቆጣጠሪያ መቀየሩን ገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2011) በአሜሪካ የሚገኘው አውሮፕላን አምራቹ ቦይንግ ኩባንያ በ737 ማክስ አውሮፕላን ላይ የነበረውን “ኤምካስ” የተሰኘው የመቆጣጠሪያ ሲስተም በመቀየር ችግሩን ፈትቼዋለሁ ሲል ገለጸ። እጅግ ዘመናዊ ከሚባሉት የቦይንግ 737 ማክስ ስሪቶች በኢትዮጵያና ኢንዶኔዥያ ተከስክሰው በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ካለቁ በኋላ ቦይንግ ከፍተኛ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል ። ይሕም ሆኖ ግን እንዳይበሩ የተደረጉት የቦይንግ የማክስ ስሪቶች በቅርቡ ወደ ሥራ ለመመለስ እስካሁን የወሰነ ሀገር የለም ...
Read More »ኦዴፓ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የስራ አስፈፃሚ አባል አደረገ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት19/2011) የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኦዴፓ) ማእከላዊ ኮሚቴ በዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ምትክ አቶ ኡመር ሁሴንን የስራ አስፈፃሚ አባል አድርጎ መረጠ። የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ለሶስት ቀናት ሲያካሂድ የነበረውን ስብሰባውን አጠናቋል። የኦዴፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር አለሙ ስሜ በሰጡት መግለጫ የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባው የተለያዩ ውሳኔዎችንና ምትክ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በመምረጥ መጠናቀቁን አስታውቀዋል። በዚህም መሰረት የኦዴፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከፓርቲው ስራ አስፈፃሚ ...
Read More »የ6 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ቡድን ግብረ-ሃይል በማቋቋም እየሰራ መሆኑን ገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2011) የ6 የፖለቲካ ፓርቲዎች ጥምረት ቡድን የፓርቲዎችን አባላት ውህደትና የአዲሱን አገር አቀፍ ፓርቲ ምስረታ ሂደት መርኃ-ግብር ለማውጣት ግብረ-ሃይል በማቋቋም እየሰራ እንደሚገኝ ገለጸ፡፡ ጥምረት የፈጠሩት ፓርቲዎቹ ኢዴፓ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ፣ የጋምቤላ ክልላዊ ንቅናቄ፣ አርበኞች ግንቦት 7ና የቀድሞ አንድነት ፓርቲ አመራርና አባላት ናቸው፡፡ ስድስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች በኢትዮጵያ ማህበራዊ ፍትህን የሚያሰፍንና ዜግነትን መሰረት ያደረገ የፖለቲካ ፕሮግራም እንዲሁም የምርጫ ወረዳን መሰረት አድርጎ የሚዋቀር ...
Read More »ከቀርጫ ወረዳ ተፈናቅለው በይርጋጨፌ የሚገኙት የጌዲዮ ተወላጆች ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 19/2011) ከምዕራብ ጉጂ ዞን ከቀርጫ ወረዳ ተፈናቅለው በይርጋጨፌ የሚገኙት የጌዲዮ ተወላጆች ህይወት አደጋ ውስጥ መውደቁ ተገለጸ። ኢሳት ከአካባቢው እንዳገኘው መረጃ ከሆነ የተፈናቃዮች ቁጥር 60ሺ ይደርሳል። ከነዚህ ተፈናቃዮች ከ15ሺ የሚበልጡት ደግሞ በይርጋጨፌ ስታዲየም ውስጥ ያለምንም መግብና መጠጥ ሳምንት ማስቆጠራቸው ነው የተገለጸው። ተፈናቃዮቹ ከበጎ አድራጊ ድርጅቶች እርዳታ እንዳያገኙ ከመደረጉም በላይ በመከላከያ ሃይል ወደ መጡበት እንዲመለሱ የሚደረገው ማስፈራሪያ ሁኔታዎች አስቸጋሪ እንዳደረገባቸው ...
Read More »ኢትዮጵያ አንድ የመረጃ አገልግሎት የሚሰጥ ሳተላይት ልታመጥቅ ነው
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2011)ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ አንድ የመረጃ አገልግሎት የሚሰጥ ሳተላይት እንደምታመጥቅ ተገለጸ። የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሪፖርት ሲያቀርቡ እንደገለጹት ኢትዮጵያ በሚቀጥለው ዓመት መጀመሪያ ላይ አንድ ሳተላይት ከሌላ ሀገር ወደ ህዋ ለማምጠቅ ዝግጅት እያደረገች ትገኛለች። የኮሚዩኒኬሽን ሳተላይት ወደ ህዋ የማምጠቅ ሙከራ ለማድረግ የሳተላይት ግብዓቶችን ከማሟላት ጀምሮ ፣ የተለያዩ ቅድመ ዝግጅቶችን በመከናወን ላይ እንደሚገኝ ...
Read More »የኢህአዴግ ምክር ቤት በኢትዮጵያ ጽንፍ የያዘ ብሄርተኝነት ካጋጠሙ ችግሮች አንደኛው ነው አለ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2011)በኢትዮጵያ አሁን ካጋጠሙ ችግሮች መካከል ጽንፍ የያዘ ብሄርተኝነት አንደኛው ነው ሲሉ የኢህአዴግ ምክር ቤት ፅህፈት ቤት ምክትል ሃላፊ አቶ መለሰ አለሙ ገለጹ። እናም በኢህአዴግ አባልና አጋር ድርጅቶች መካከል ሊደረግ የታሰበው ውህደት ይሕን ችግር ለመፍታት ያስችላል ብለዋል። ወሕደቱ ራስን በራስ ከማስተዳደር መብት ጋር ፣ ከፌዴራል ስርዓቱና በህገ መንግስቱ ከተቀመጡ የመንግስት አስተዳደር ጉዳዮች ጋር እንደማይጣረስም ኣአቶ መለሰ አለሙ ገልጸዋል። የኢህአዴግ ...
Read More »በጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ላይ የሚካሄደው ማስፈራራትና ዛቻ በአስቸኳይ እንዲቆም ተጠየቀ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2011)በጋዜጠኛና የሰብዓዊ መብት ተሟጋቹ እስክንድር ነጋ ላይ የሚካሄደው ማስፈራራትና ዛቻ በአስቸኳይ እንዲቆም ከ40 በላይ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ምሁራን እና ታዋቂ ሰዎች ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ደብዳቤ ጻፉ። ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ እና ዶክተር አክሎግ ቢራራን ጨምሮ ከ40 በላይ ምሁራን ለዶክተር አብይ በጻፉት ግልጽ ደብዳቤ ጋዜጠኛና የሰብአዊ መብት ታጋዩ እስክንድር ነጋ የራሱን የግል ሕይወት ትቶ ለሃገሩ ዋጋ የከፈለና አሁንም በሰላሚዊ መንገድ ...
Read More »በጎፋ ዞን አላግባብ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱ ተገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2011)በጎፋ ዞን አላግባብ የሚታሰሩ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገለጹ። ባለፉት ሶስት ቀናት ብቻ በአካባቢው ፖሊስና በዞኑ አስተዳደር የማንነት ጥያቄ አንስታችኋል በሚል የታሰሩ ዜጎች ቁጥር ከ30 በላይ መድረሱን ለኢሳት የደረሰው መረጃ ያመለክታል። ኢሳት በጉዳዩ ላይ የዞኑን አስተዳዳሪ ለማነጋገር ሙከራ አድርጎ ነበር አስተዳዳሪው ስብሰባ ላይ ነኝ የሚል መልስ በመስጠታቸው ይሄ ዜና እስከተጠናከረበት ጊዜ ድረስ አስተዳዳሪውን አግኝቶ ማነጋገር ...
Read More »አርበኞች ግንቦት ሰባት የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምስረታ ጥረታችን በእብሪተኞች ድርጊት አይገታም ሲል ገለጸ
(ኢሳት ዲሲ–መጋቢት 18/2011) የዲሞክራሲያዊ ሥርዓት ምስረታ ጥረታችን በአመጸኞችና በዕብሪተኞች ድርጊት አይገታም ሲል አርበኞች ግንቦት ሰባት ንቅናቄ ባወጣው መግለጫ አመለከተ። አርበኞች ግንቦት 7 ባወጣው መግለጫ ለረጅም ዓመታት ከታገለላቸዉ መብቶች ዉስጥ አንዱ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ባልተስማማበት ሀሳብ፥ፖሊሲና ፕሮግራም ላይ ህግና ደንብን እስካከበረ ድረስ ያለምንም መከልከል በፈለገዉ መን ገድ ተቃዉሞዉን መግለጽ እንዲችል ነዉ ብሏል። ነገር ግን ዛሬ አገራችን ዉስጥ በግልጽ የሚታየዉ የዜጎች መብትና ነጻነት ...
Read More »