(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010) በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የተቀሰቀሰው የኢቦላ ቫይረስ ወደ ሌሎች የሃገሪቱ የገጠር ከተሞች እየተስፋፋ መሆኑ ተሰማ። እስካሁን በቫይረሱ 45 ሰዎች መጠቃታቸው ታውቋል።የሌሎች 25 ሰዎች አሟሟትም ምናልባት ከቫይረሱ ጋር ሳይያያዝ አይቀርም በሚል አስከሬናቸው ላይ ምርመራ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል። እንደዘገባው ከሆነ ቫይረሱ ወደ ገጠር ከተማዋ ማባንዳካ መዛመቱ በአንድ ሰው ላይ ምልክቱ መታየቱ ተሰምቷል። ከተማዋ አንድ ሚሊየን ያህል ሕዝብ የሚኖርባት መሆኑ ደግሞ ...
Read More »Author Archives: Central
ለደቡብ ሱዳን ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሊሰጥ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9/2010) በመቶ ሺዎች ለሚቆጠሩ የደቡብ ሱዳን ተወላጆች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ለመስጠት መወ ሰኑ ተቃውሞ አስነሳ። የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት በፌደራል መንግስቱ የተደረሰውን ስምምነት ለማስፈጸም ውሳኔ ማሳለፉ ታውቋል። ለደቡብ ሱዳናውያን በጅምላ የኢትዮጵያ ዜግነት እንዲሰጣቸው የተወሰነበት ይፋዊ ምክንያት አልተገለጸም። የጋምቤላ የመብት ተሟጋቾች ዜግነት የሚሰጣቸው ደቡብ ሱዳናውያን ቁጥራቸው 400ሺህ እንደሚጠጋ ይገልጻሉ። የኢትዮጵያውያን አኝዋኮችን ህልውና ለማጥፋት የሚደረገውን ሚስጥራዊ እንቅስቃሴ የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲያስቆም የመብት ...
Read More »ኢትዮጵያ፣ ግብጽና ሱዳን በአባይ ጉዳይ ላይ ተስማሙ ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010)ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በአባይ ጉዳይ ላይ ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተነገረ። በሶስቱ ሃገራት መካከል ጊዜያዊ ስምምነት በመደረሱም በመካከላቸው የነበረው ውጥረት ረግቧል ተብሏል። በጋራ ሚንስትሮቻቸው አማካኝነት ስምምነት ላይ የደረሱት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን የግድቡን ውሃ አሞላል በተመለከተ ጉዳዩን የሚከታተል የሳይንቲስቶች ቡድን ጥናት እንዲያደርግ ነው ። ኢትዮጵያ ግብጽና ሱዳን በአባይ ግድብ ግንባታ ጉዳይ ላይ በርካታ ውይይቶች ሲያደርጉ የነበረ ቢሆንም ስምምነት ለይ ...
Read More »የመንግስት ሹማምንት የውጭ ጉዞ ሒሳባቸውን አያወራርዱም ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010) የመንግስት ሹማምንት ለስራና ለህክምና ወደ ውጭ በሄዱበት ሀገር የተጠቀሙበትን ገንዘብ እንደማያወራርዱ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ። ገንዘቡ ስለማይወራረድም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከፍተኛ የኦዲት ጉድለት እንዳለበት አስታውቋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ወርቅነህ ገበየሁ ችግሩ ስላሳሰባቸው ጉዳዩን ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል ተብሏል። የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ያልተወራረዱ እና መከፈል ያለባቸው ሒሳቦች እንዳሉ ቢያሳውቅም መጠኑ ግን ...
Read More »በኢሕአዴግ የተዋቀሩት ግብረ ሃይሎች ፈረሱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 10/2010) በሃገሪቱ መንግስታዊ መዋቅር ውስጥ በመግባት ስራዎችን እንዲመሩ እና እንዲያስተባብሩ በኢሕአዴግ የተዋቀሩት 12 ግብረ ሃይሎች እንዲፈርሱ መወሰኑ ተገለጸ። እነዚህ ግብረሃይሎች በአቶ በረከት ስምኦን፣አቶ አባዱላ ገመዳ እና በሕወሃት ሰዎች የሚመሩ እንደነበሩም ታውቋል። በኢትዮጵያ ውስጥ የተፈጠረውን ቀውስ ተከትሎ የኢሐዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በታህሳስ ወር 2010 በወሰነው መሰረት ተዋቀረ የተባለው ኮሚቴ የካቢኔ ድልድልን ጨምሮ ፣በመንግስት ስራ ውስጥ በግልጽ ጣልቃ የሚገባ እና ...
Read More »በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚያዚያ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ቀናት ከ5 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ከሚያዚያ አጋማሽ ጀምሮ ባሉት ቀናት ከ5 በላይ የአማራ ተወላጆች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ለአመታት በክልሉ በኖሩ የአማራ ተወላጆች ላይ የሚደርሰው ጥቃት ከቀን ወደ ቀን እየጨመረ መምጣቱን የሚገልጹት የአማራ ተወላጆች፣ ባለፉት 2 ሳምንታት ብቻ ከ5 ያላነሱ ሰዎች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል ብለዋል። ደባጢ ወረዳ ውስጥ የ14 አመት ታዳጊ የሆነው አበጠር ወርቁ እጅግ አሰቃቂ ...
Read More »በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው
በሃና ማርያም በሺዎች የሚቆጠሩ ቤቶች እየፈረሱ ነው (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) ባለፈው ሳምንት የተጀመረው የቤት ማፍረስ ዘመቻን ተከትሎ እስካሁን ከ20 ሺ በላይ ቤቶች መፍረሳቸውን ነዋሪዎች ገልጸዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ያለ መጠለያ የቀሩ ሲሆን፣ ድርጊቱን ለመቃወም ሙከራ ያደረጉ ነዋሪዎች ወደ እስር ቤት ተወስደዋል። ብዙዎቹ መደብደባቸውንና እስካሁን 2 ሰዎች መገደላቸውንና ነዋሪዎች ተናግረዋል። አንደኛዋ ቤቷ ሲፈርስ እቃዋን ለማውጣት ስትገባ ቤቱን ...
Read More »የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣን ተነሱ
የሐረሪ ክልል ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣን ተነሱ (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በሃረሪ ክልል የሚኖሩ የኦሮሞ ተወላጆችን ጥያቄዎች በአግባቡ አልመለሱም ሃላፊነታቸውንም በአግባቡ አልተወጡም በሚል ሲተቹ የቆዩት አቶ ገቢሳ ተስፋዬ ከስልጣናቸው ተነስተው ወደ ጨፌ ኦሮምያ ተዛውረዋል። በእርሳቸው ቦታ አቶ በቀለ ተመስገን የሐረሪ ክልል ኦህዴድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ቢሮ ሃላፊ ተመድበዋል። በሃረሪ ክልል የሚኖሩ ...
Read More »“ባለስልጣናቱ ወረው ለመብላት የተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች ተናገሩ
“ባለስልጣናቱ ወረው ለመብላት የተዘጋጁ ናቸው” ሲሉ በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ ነዋሪዎች ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 10 ቀን 2010 ዓ/ም) በተለያዩ ከተሞች በሃላፊነት ቦታ የተቀመጡ የገዥው መንግስት አመራሮች የድሃውን ህብረተሰብ ችግር ከመፍታት ይልቅ ለራሳቸው ጥቅም የቆሙ በመሆናቸው ፣ሰርተው ሃገሪቱን ከመለወጥ ይልቅ የራሳቸውን ጥቅም ማሳደዳቸውን መቀጠላቸው እንዳማረራቸው በአማራ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚኖሩ አስተያየት ሰጪዎች ተናግረዋል፡፡ አሁን በአመራር ላይ ያለው ትውልድ በአመራር ...
Read More »ጀርመን ከ30 ሺ በላይ ናይጄሪያውያንን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ ነው
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9/2010) ጀርመን ከ30 ሺ በላይ ናይጄሪያውያንን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ መዘጋጀቷን አስታወቀች። በህገ ወጥ መንገድ ሲኖሩ ነበሩ የተባሉትን ናይጄሪያውያኑን ስደተኞች ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በቂ ዝግጅት መደረጉን የጀርመን መንግስት አስታውቋል። የናይጄሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጂዮፌሪ ኦኒዮማ የጀርመን መንግስት ይህንን የሚገልጽ ደብዳቤ መላኩንና ስራውንም ከናይጄሪያ ኤምበሲ ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቆናል ብለዋል። የጀርመን መንግስት ይህንን ይበል እንጂ ህገወጥ ናቸው የተባሉትን 30ሺ ናይጄሪያውያንን ...
Read More »