ጀርመን ከ30 ሺ በላይ ናይጄሪያውያንን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ ነው

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 9/2010) ጀርመን ከ30 ሺ በላይ ናይጄሪያውያንን ወደ ሀገራቸው ልትመልስ መዘጋጀቷን አስታወቀች።

በህገ ወጥ መንገድ ሲኖሩ ነበሩ የተባሉትን ናይጄሪያውያኑን ስደተኞች ወደ ሃገራቸው ለመመለስ በቂ ዝግጅት መደረጉን የጀርመን መንግስት አስታውቋል።

የናይጄሪያ የውጪ ጉዳይ ሚኒስትር ጂዮፌሪ ኦኒዮማ የጀርመን መንግስት ይህንን የሚገልጽ ደብዳቤ መላኩንና ስራውንም ከናይጄሪያ ኤምበሲ ጋር በጋራ እንደሚሰራ አስታውቆናል ብለዋል።

የጀርመን መንግስት ይህንን ይበል እንጂ ህገወጥ ናቸው የተባሉትን 30ሺ ናይጄሪያውያንን የማስወጣቱ ሂደት ረጅም ጊዜ ሊወስድ ይችላል ብለዋል።

የጀርመን መንግስት ይህንን ካሳወቀ ግዜ አንስቶም 200 ናይጄሪያውያንን ብቻ ወደ ሃገር ቤት መመለሱን ነው ብሬኪንግ ታይምስ የተባለው ድረገጽ ይፋ ያደረገው መረጃ የሚያመለክተው።