አሜሪካ ለኢትዮጵያ የጦር አውሮፕላን ሰጠች። (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ በሰጠው መግለጫ ፣በዩናይትድ ስቴትስ መንግስት ስም- ለኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ጀነራል አደም መሀመድ ሲ- 130 የጦር አውሮፕላንን በማበርከቱ ሂደት – አምባሳደር ሚካኤል ሬይኖር ተሳትፈዋል። ሲ-130 አውሮፕላን፣ ኢትዮጵያ የቀጣናውን ሰላም ለማስጠበቅ የተቀበለችውን ተልዕኮ በብቃት እንድትወጣ፣ የሰብዓዊ እርዳታ በሚያስፈልግባቸው በማናቸውም አካባቢ አቅርቦቱን በፍጥነትና በሰዓቱ ለማድረስ ...
Read More »Author Archives: Central
በአማራ ክልል በሚሊሻነት ሲያገለግሉ የቆዩ ነዋሪዎች ከመደበኛው ወታደር ጋር ተሰልፈው በተለያዩ አውዶች በመዋጋት አካላቸውን ቢያጡም፣ በመንግስት ስራ እንዳያገለግሉ መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡
በአማራ ክልል በሚሊሻነት ሲያገለግሉ የቆዩ ነዋሪዎች ከመደበኛው ወታደር ጋር ተሰልፈው በተለያዩ አውዶች በመዋጋት አካላቸውን ቢያጡም፣ በመንግስት ስራ እንዳያገለግሉ መከልከላቸው አግባብ እንዳልሆነ ተናገሩ፡፡ (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) ሰሞኑን በሰሜን ሸዋ በተደረገው ህዝባዊ ስብሰባ በዞኑ ነዋሪ የሆኑ የቀድሞ ሚሊሻ አባላት የክልሉ መንግስት ለሰሩት ስራ ተገቢውን ድጋፍ እንዳልሰጣቸው ተናግረዋል፡፡ የሚሊሻ አባላቱ እንደተናገሩት ከስድስተኛ እስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል የሚማሩ ተማሪዎችን በውትድርና ...
Read More »የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር፣ በደጋፊቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም ጠየቀ።
የፋሲል ከነማ እግር ኳስ ቡድን የደጋፊዎች ማህበር፣ በደጋፊቻቸው ላይ የሚደርሰው እንግልት እንዲቆም ጠየቀ። (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም)ማህበሩ የፋሲል ከነማ መለያ ልብስን በመልበሱ ምክንያት ወልቃይት ላይ የታሰረውን ፍቃዴ አሰፋን የአባልነት መታወቂያ አያይዞ “ለሚመለከተው ክፍል” በሚል ርዕስ በላከው ደብዳቤ፣ የክለቡ ደጋፊ የክለቡን መለያ በመልበሱ እና መታወቂያ በመያዙ ምክንያት የደረሰበትን እስርና እንግልት ነቅፏል። ፍቃዱ አሰፋ- የፋሲል ከነማ ማልያን በመልበሱ ወልቃይት ...
Read More »ባለፈው ዓመት በስዊድን ስቶኮሆልም በከባድ መኪና ሕዝብ ላይ በመንዳት አምስት ሰዎችን የገደለው የኡዝቤክ ተወላጅ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።
ባለፈው ዓመት በስዊድን ስቶኮሆልም በከባድ መኪና ሕዝብ ላይ በመንዳት አምስት ሰዎችን የገደለው የኡዝቤክ ተወላጅ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት። (ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የ40 ዓመቱ ራክማት አኪሎቭ የስቶኮሆልሙን ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ራሱን ኢስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ተመልክቷል።. ይሁንና አይ ኤስ ግን ከጥቃቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት ምንም ያለው ነገር የለም። የስደተኝነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት ...
Read More »ወደየመን ሊሻገሩ የነበሩ 46 ኢትዮጵያውያን ሞቱ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010) በባህር ወደየመን ሊሻገሩ የነበሩ 46 ኢትዮጵያውያን መሞታቸው ተገለጸ። ዓለም ዓቀፉ የስደተኞች ድርጅት አይ ኦ ኤም ትላንት እንዳስታወቀው 100 ሰዎችን ጭና ትጓዝ የነበረች ጀልባ በመስጠሟ ምክንያት አደጋው የደረሰ ሲሆን በሕይወት የተገኙት 38 መሆናቸው ተገልጿል። 16 ሰዎች እስካሁን እንዳልተገኙ ድርጅቱ ባወጣው ሪፖርት ላይ ተመልክቷል። ጀልባዋ የጫነችው በሙሉ ኢትዮጵያውያንን ነበረ። ከትላንት በስትያ መነሻዋን ከቦሳሶ ወደብ ያደረገችው ጀልባ አንድ መቶ ኢትዮጵያውያንን ...
Read More »አሜሪካ C-130 የተባሉ የጦር መጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ በስጦታ አበረከተች
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010) አሜሪካ C-130 የተባሉ የጦር መጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ በስጦታ ማበርከቷን በእንግሊዝ ሀገር የሚታተም አንድ የመከላከያ መጽሄት ይፋ አደረገ፡፡ የአሜሪካ መንግስት ዘመናዊ የተባሉና በጦርነት ጊዜ የማጓጓዝ ተግባር የሚፈጽሙ C-130 የጦር አውሮፕላኖች ለኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በስጦታ ማበርከቱ ነው የተገለጸው። አውሮፕላኖቹ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠታቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሴም አረጋግጧል ። ሎክሂድ ማርቲን c-130 ሔርኩለስ ተብሎ የሚጠራውና በአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ...
Read More »ሜጀር ጄነራል አለምሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010) ሜጀር ጄነራል አለምሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ ማዕረጋቸው ተመለሰ ። የሁለቱ ከፍተኛ መኮንኖች ማዕረግ የተመለሰው በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ውሳኔ ነው። ሜጀር ጄነራል አለምሸት ደግፌ እና ብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ በምርጫ 1997 ማግስት ሕዝባዊ አቋም በመያዛቸው ማዕረጋቸውን ተገፈው በተራ ወታደርነት ከሰራዊቱ የተባረሩት በሟቹ ጠቅላይ ሚኒስትር መለሰ ዜናዊ ትዕዛዝ ነበር። የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት እንዳስታወቀው ሁለቱ ...
Read More »የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች ለስደት እየተዳረጉ ነው ተባለ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010) የድሬደዋ ከተማ ነዋሪዎች በከተማዋ የመኖር መብታቸው በመገፈፉ ለስደት እየተዳረጉ መሆኑ ተገለጸ። ነዋሪዎቹ እንደሚሉት ምርጫ 97ን ተከትሎ የተተገበረው 40፣40፣20 ፖለቲካ በከተማዋ ተወልደው ያደጉ ዜጎችን መብት ገፏል ሲሉም ተናግረዋል። ድሬደዋ ተወልደው አድገው የማይኖሩባት ከተማ ሆናለች ሲሉ ነዋሪዎቹ ምሬታቸውን ይገልጻሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች የድሬደዋ የፍቅር ከተማነት ጥያቄ ውስጥ የገባው ኢሕአዴግ ምርጫ 97ን ተከትሎ በ1999 በከተማ ውስጥ ቢሮውን መከፈቱ ነው ይላሉ። የቢሮውን ...
Read More »ሜቴክ ለኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ያቀረባቸው ቁሶች የማይሰሩ መሆናቸው ተጋለጠ
(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010)የብረታ ብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ በቢሊዮን ብሮች ወጪ ለኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን ያቀረባቸው ትራንስፎርመሮች እና ሌሎች ቁሶች የማይሰሩ መሆናቸው ተጋለጠ። የኤሌክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በቢሊዮን ብር ያወጣባቸው እነዚህ ቁሶች የማይሰሩ በመሆናቸው ሜዳ ላይ ተጥለው አረም እየበቀለባቸው መሆኑን በምስል ተደግፎ ለኢሳት የደረሰው ዜና ያስረዳል። የማይሰሩ ቁሶች ሜዳ ላይ ተጥለው በሚገኙበት በአሁኑ ወቅት ፣ ሜቴክ ተጨማሪ የማይሰሩ መሳሪያዎችን አሁንም በማቅረብ ላይ ...
Read More »የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈጸመ ነው ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ
የኢኮኖሚ አሻጥር እየተፈጸመ ነው ሲሉ ዶ/ር አብይ አህመድ ተናገሩ (ኢሳት ዜና ግንቦት 29 ቀን 2010 ዓ/ም) ጠ/ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት በ4ኛው ሃገር አቀፍ የፀረ ሙስና ጥምረት ጉባኤ ላይ ተገኝተው ነው። “ ከአዲሱ ጠ/ሚኒስትር መምጣት በሁዋላ የሚታዩ የኢኮኖሚ “ሳቦታጆች”፣ የሚፈጸሙ ቅጥፈቶች ህብረተሰቡ በንቃት ካልታገለው ትንሽ ተብሎ የሚናቅ እንዳልሆነ ግምት ሊሰጠው ይገባል።” ሲሉ ተናግረዋል። ዶ/ር አብይ ከእርሳቸው ወደ ስልጣን መምጣት ጋር በተያያዘ የኢኮኖሚ ...
Read More »