አሜሪካ C-130 የተባሉ የጦር መጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ በስጦታ አበረከተች

(ኢሳት ዲሲ–ግንቦት 30/2010) አሜሪካ C-130 የተባሉ የጦር መጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ በስጦታ ማበርከቷን በእንግሊዝ ሀገር የሚታተም አንድ የመከላከያ መጽሄት ይፋ አደረገ፡፡

የአሜሪካ መንግስት ዘመናዊ የተባሉና በጦርነት ጊዜ የማጓጓዝ ተግባር የሚፈጽሙ C-130 የጦር አውሮፕላኖች ለኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በስጦታ ማበርከቱ ነው የተገለጸው።

አውሮፕላኖቹ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠታቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሴም አረጋግጧል ።

ሎክሂድ ማርቲን c-130 ሔርኩለስ ተብሎ የሚጠራውና በአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት ጥቅም ላይ የነበሩት የጦር አውሮፕላኖች መሳሪያ፣ ስንቅና መድሃኒት ለማቀበል የሚረዱ ናቸው።

የቆሰሉ ወታደሮችን ለማመላለስና ለአስቸኳይ አደጋዎች የሚረዱት አውሮፕላኖቹ በማንኛውም የጦርነትና የአደጋ ቀጠናዎች ልዩ እገዛ በመስጠት ይታወቃሉ፡፡

በጦር ቀጠናዎችም ቦምብ በማዝነብ ድብደባ መፈጸም ይችላሉም ተብሏል።

በአሜሪካም ሆነ በሌሎች አገራት ከተመረቱ የጦር አውሮፕላኖች ተመራጭና በተዋጊ ወታደሮች የሚወደድ መሆኑም ይነገራል።

አሜሪካ C-130 የተባሉ የጦር መጓጓዣ አውሮፕላኖችን ለኢትዮጵያ በስጦታ ማበርከቷን በእንግሊዝ ሀገር የሚታተም አንድ የመከላከያ መጽሄት ይፋ አደርጓል፡፡

የአሜሪካ መንግስት ዘመናዊ የተባሉና በጦርነት ጊዜ የማጓጓዝ ተግባር የሚፈጽሙትን C-130 የጦር  አውሮፕላኖች ለኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል በስጦታ አበረክቷል ተብሏል፡፡

አውሮፕላኖቹ ለኢትዮጵያ መንግስት መሰጠታቸውን አዲስ አበባ የሚገኘው የአሜሪካ ኢምባሲም አረጋግጧል ።

የዋዜማ ደረገጽ እንዳመለከተውም የአሜሪካው መከላከያ መስሪያ ቤት እነዚህን  የጦር አውሮፕላኖች ረቡዕ ግንቦት 29/ 2010 ለኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል አስረክቧል።

ርክክቡም በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር ኃይል ግቢ ውስጥ መከናወኑ ነው የተነገረው።

በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር  ሚካኤል ሬይነር እና በአውሮፓና አፍሪካ የአሜሪካ አየር ኃይል ተወካይ  ብርጋዴር ጄነራል ዴይተር ባሬይሽ   እንዲሁም በኢትዮጵያ በኩል የአየር ኃይል አዛዥ ሌተናል ጀነራል አደም መሃመድ ርክክቡን ፈጽመዋል፡፡

በቴክሳስ በሚገኘውና በዓለም ግዙፉ የጦር አውሮፕላን አምራች ሎክሂድ ማርቲን ከ2,700 በላይ አውሮፕላኖች እንዳመረተ ይነገራል፡፡ የአንዱ አውሮፕላን ሽያጭ አማካይ ዋጋው 35 ሚሊየን ዶላር ያህል ነው ተብሏል።

ኢትዮጵያ በደርግ ጊዜ የ C-130 ዝርያ የሆነ ሁለት L100 ሄርኩልስ አውሮፕላን ነበራት።