ባለፈው ዓመት በስዊድን ስቶኮሆልም በከባድ መኪና ሕዝብ ላይ በመንዳት አምስት ሰዎችን የገደለው የኡዝቤክ ተወላጅ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።

ባለፈው ዓመት በስዊድን ስቶኮሆልም በከባድ መኪና ሕዝብ ላይ በመንዳት አምስት ሰዎችን የገደለው የኡዝቤክ ተወላጅ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደበት።
(ኢሳት ዜና ግንቦት 30 ቀን 2010 ዓ/ም) የ40 ዓመቱ ራክማት አኪሎቭ የስቶኮሆልሙን ጥቃት ከመፈጸሙ በፊት ራሱን ኢስላማዊ መንግስት ብሎ ከሚጠራው ከአይ ኤስ ጋር ግንኙነት እንደነበረው ተመልክቷል።.
ይሁንና አይ ኤስ ግን ከጥቃቱ ጀርባ እጁ እንዳለበት ምንም ያለው ነገር የለም።
የስደተኝነት ጥያቄው ውድቅ የተደረገበት አኪሎቭ ጥቃቱን እንደፈጸመ ለማምለጥ ሲሞክር ወዲያውኑ ተይዞ የታሰረ ሲሆን፣ በፖሊስ ምርመራ ወቅት የፈጸመውን ተግባር ተናዟል።.
አኪሎቭ እንደአውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2014 ነው እዚያው ለመኖር በማሰብ ሀገሩን ኡስቤኪስታንን በመልቀቅ ወደ ስዊድን ያቀናው።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ፣ የ40 ዓመቱ ጎልማሳ ጥቃት ከመፈጸሙ ጥቂት ወራት በፊት በመሰወሩ በፖሊስ የተፈላጊዎች መዝገብ ውስጥ ሰፍሮ ቆይቷል።