Author Archives: Central

መንግስት ሙስሊሙ ያቀረበውን ጥያቄ በሀይል ለመፍታት ቆርጦ ተነስቷል

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከሳምንት ሳምንት እየተጠናከረ የመጣው የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞ ፣ መላው ክርስቲያኖችንን እንዲያካትት ጥሪ እየተላለፈ ባለበት በአሁኑ ወቅት መንግስት ችግሩን በሰላም ለመፍታት ከመሞከር ይልቅ የሀይል አማራጭን ለመጠቀም ፍላጎት እያሳየ ነው። የአቶ መለስ ዜናዊን የሰሞኑን የፓርላማ ንግግር ተከትሎ በመላ አገሪቱ የሚገኙ በርካታ ሙስሊሞች ባለፈው አርብ ተቃውሞዓቸውን ካሰሙ በሁዋላ፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከመንግስት ...

Read More »

የግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ የኃይል ማመንጫ ግድብ በደለል ተሞላ

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ የኃይል ማመንጫ ግድብ በደለል ተሞላ።ችግሩ ፤በአገሪቱ ላይ ከባድ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ችግር  እንዳይፈጥር የመንግስት ባለስልጣናት ጭንቀት ውስጥ ናቸው። አንድ ባለሥልጣን፦”የግልገል ጊቤን ችግር መቅረፍ ካልቻልን፤ይሄ መንግስት ግድብ መገደብ እንጂ፤የገደበውን አይከታተልም የሚል ፖለቲካዊ አንድምታ  ይፈጥርብናል” ሲሉ ተደምጠዋል። በፓርላማው የተፈጥሮ ሀብት ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፤ ከውኃና ኢነርጂ ሚኒስትሩ አቶ ...

Read More »

በቶሮንቶ ከተማ ታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

የግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ የኃይል ማመንጫ ግድብ በደለል ተሞላ። ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በዚህ በቶሮንቶ ከተማ በዋልድባ፤ በአሰቦት እና በዝቋላ ገዳማት ላይ የኢትዮጵያ መንገሥሰት እያከሄደ ያለውን ታሪክን፤ ሃይማኖትን እና ለዘመናት ተጠብቀው በነበሩት እንሰሳትና እፀዋት ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት ለመቃወም በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክረስቲያን በጠራው ሠላማዊ ሰልፍ የተለያዩ የሰባዊ መብት ድርጅት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በሠላማዊ ሰልፉ ላይ ...

Read More »

በለሀ ከተማ በተፈጠረው ረብሻ ከ5 ያላነሱ ሰዎች በፖሊሶች ተገደሉ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በጋሞጎፋ ዞን በመለኮዛ ወረዳ በለሀ ከተማ ከአራት ቀናት በፊት በተነሳው ረብሻ ልዩ የፌደራል ፖሊስ እና የመከላከያ አባላት ህዝቡ ላይ በከፈቱት ተኩስ ቁጥሩ በትክክል ለማወቅ ያልተቻለ በርካታ ሰዎች ሙትና ቁስለኛ ሆነዋል። አንዳንድ የአካባቢው ምንጮች የሟቾችን ቁጥር 10 ሲያደርሱት ሌሎች ደግሞ ወደ 5 ዝቅ ያደርጉታል። በተመሳሳይም በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች ቁስለኞች ሆነዋል፣ ድብደባ የደረሰባቸው እና ...

Read More »

በአልቃይዳ ምክንያት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሸኚዎች እንዳይገቡ አገደ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አየር መንገዱ ሸኚዎች ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ያገደው ከአራት ቀናት በፊት ጀምሮ ነው። የፋሲካ በአልን ለማክበር ወደ ኢትዮጵያ የተጓዙ መንገደኞች ወደ አየር ማረፊያው ሲገቡ ከወትሮው የተለየ ጥብቅ ፍተሻም እየተካሄደባቸው ነው። ተጓዦችን ለመሸኘት የመጡት ግን ወደ ውስጥ እንዳይገቡ ተደርጓል። ወደ ውስጥ ሲገቡና ሲወጡ የሚታዩት ልዩ የይለፍ ወረቀት የያዙ የመንግስት ባለስልጣናት ብቻ ናቸው። በርካታ ሸኚዎች ...

Read More »

ትናንት ከጁምአ ጸሎት በሁዋላ ሙስሊሞች አደባባይ በመውጣት ከፍ ያለ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተዘገበ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ትናንት ከጁምአ ጸሎት በሁዋላ በትልቁ አንዋር መስጂድ እና በ አወሊያ ከተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በተጨማሪ፣ በደሴ ከ80 ሺህ እና በሀረር ከ 50 ሺህ በላይ ሙስሊሞች አደባባይ በመውጣት ከፍ ያለ ተቃውሞ ማሰማታቸው ተዘገበ። ከመቼውም በተለየ መልኩ  የሙስሊሞቹ ተቃውሞ በ አገር አቀፍ ደረጃ  እያየለ የመጣው፤አቶ መለስ ሰሞኑን ፓርላማ ቀርበው  ከሙስሊሙ ማህበረሰብ ለተሰነዘረው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ ...

Read More »

ቅዱስ ሲኖዶስ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩነቱን አቻችሎ በወያኔ ጠባብ አገዛዝ ላይ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እራሱን ህጋዊው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሲኖዶስ፤ በሚል የሚጠራው ቅዱስ ሲኖዶስ “ ሁሉም የኢትዮጵያ ህዝብ ልዩነቱን አቻችሎና አስወግዶ  አገር እያጠፋ ባለው የወያነ ጠባብ አገዛዝ ላይ በጋራ እንዲነሳ ጥሪ አቀረበ። መቀመጫውን በአሜሪካ ኦክላንድ ያደረገው ሲኖዶሱ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ-ክርስቲያን ሲኖዶስ ባወጣው መግለጫ የጥንቱ የግብጽ አገዛዝ በእስራኤል ልጆች ላይ ሲያደርግባቸው የነበረውን አሰቃቂ ግፍ በማስታወስ፤ያኔ ...

Read More »

የቦብ ማሪሊንን የህይወት ታሪክ የሚዘክር ዘጋቢ ፊልም ተሰራ

ሚያዚያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኦስካር ተሸላሚው ኬቪን ማክዶናልድ የተሰራው ፊልም የቦብ ማርሊን ህይወት ከሚገልጹት ፊልሞች ሁሉ የተሻለ ነው ተብሎአል። ፊልሙ ቦብ ማርሊንን ብሄራዊ ጀግና ለማድረግ ለተጀመረው እንቅስቃሴ እገዛ እንደሚያደርግ ታውቋል። በኪንግስተን ፓርክ በተደረገው የመክፈቻ ዝግጅት በብዙ ሺዎች የሚቆጠሩ ጃማይካዊያን ተሳትፈዋል። በዝግጀቱ እለት ለመንግስቱ ባለስልጣናት መረማመጃ ተብሎ የተነጠፈው ቀይ ቢጫ እና አረንጓዴ ባንዲራ ፣ በተመልካቹ ተቃውሞ እንዲነሳ ...

Read More »

ሙስሊሞች ዛሬ በአወልያ መስጊድ ተገኝተው ተቃውሞአቸውን አሰሙ

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊሞች ዛሬ በአወልያ መስጊድ ተገኝተው ተቃውሞአቸውን አሰሙ::  በዛሬው የጁመዓ ጸሎት እጅግ በርካታ ቁጥር ያለው ሙስሊም ተገኝቶ በተለይ አቶ መለስ በቅርቡ ያደረጉትን ንግግር  መቃወሙን የደረሰን ዜና ያመለክታል። ወጣቱ፣ ጎልማሳው አዛውንቱ የአቶ መለስ ንግግር ክርስቲያኑን ከሙስሊሙ ለማጋጨት ሆን ተብሎ የቀ ረበ መሆኑን በመረዳት በተለያዩ መንገዶች ተቃውሞውን ሲገልጽ ተሰምቷል። ከአራት ቀን ...

Read More »

ሰሜን ሱዳን ደቡብ ሱዳንን የምትወጋ ከሆነ ዩጋንዳ ጣልቃ እንደምትገባ አስጠነቀቀች

ሚያዚያ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዩጋንዳ ጦር አዛዥ የሆኑት አሮንዳ ኒያክሪማ እንዳሉት ሰሜን ሱዳን ደቡብ ሱዳንን ለመውረር ከከጀለች አገራቸው ዝም ብላ አትመለከትም። የጦር አዛዡ የአልበሽር መንግስት የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ  ሰራዊትን ይደግፋል የሚል ክስም አቅረበዋል። የኡጋንዳን መንግስት እየተፋለመ የሚገኘው የሎርድ ሬዚስታንስ አርሚ ፣ ቀደም ብሎ ከመሸገበት የማእከላዊ አፍሪካ ወጥቶ በሰሜን ሱዳን ድንበር አካባቢ ሰፍሮ እንደሚገኝ ባለስልጣኑ ተናግረዋል። የመለስ ...

Read More »