Author Archives: Central

ኢብሳ አስፋው አቶ ናትናኤል መኮንንን ለመደብደብ ያደረገው ሙከራ በ እስረኞች ትብብር ከሸፈ

ሚያዚያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በግድያ ወንጀል 25 ዓመት እስራት ተፈርዶበት ቃሊቲ ማረሚያ ቤት የሚገኘው  ይባስ አስፋው፤ ሆነ ተብሎ ገና ካልተፈረደባቸው እስረኞች ጋር እንዲቀላቀል ከተደረገ በሁዋላ የአንድነት ፓርቲ ምክትል ሊቀ-መንበር  አቶ አንዷለም አራጌን በአሰቃቂ ሁኔታ በመደብደብ   ከፍ ያለ የአካል ጉዳት እንዳደረሰባቸው መዘገቡ ይታወሳል። ይባስ አስፋው፤ በአቶ አንዷለም ላይ  ጉዳት በማድረሱ ከተለያየ አቅጣጫ  ከፍ ያለ ተቃውሞ እየተሰማ ባለበት ወቅት  ...

Read More »

የኑሮ ውድነቱ አንገብጋቢው የአገሪቱ ችግር መሆኑን አቶ መለስ ተናገሩ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ላለፉት 8 አመታት የ11 በመቶ የኢኮኖሚ እድገት ማስመዝገባቸውን በተደጋጋሚ ሲናገሩ ይሰሙ የነበሩት አቶ መለስ፣ ዛሬ 99 ነጥብ ስድስት በመቶ የአንድ ፓርቲ አባላትና ደጋፊዎቻቸው በተገኙበት የፓርላማ ውሎ የአገሪቱ ፈታኝ እና ዋነኛው ችግር የኑሮ ውድነቱ መሆኑን ተናግረዋል። አቶ መለስ ይህን የተናገሩት “መንግስት የኑሮ ውድነቱን ለመቆጣጠር የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰድኩ ነው ቢልም የኑሮ ውድነቱ ግን እየባሰ፣ የምግብ ...

Read More »

ማተሚያ ቤቶች ሳንሱር ማካሄድ ጀመሩ፣ የህትመት ስራ አደጋ ውስጥ ወድቋል ተባለ

ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስልጣን ላይ ያለው መንግስት አስከብረዋለሁ የሚለው ህገ መንግስት በአንቀጽ 29 ላይ ማንኛውም ሳንሱር ወይም ከህትመት በፊት የሚደረግ የጽሁፍ ይዘት ቁጥጥር እንደማይኖር ቢደነግግም፣ በኢትዮጵያ ውስጥ በህትመት ስራ አንጋፋ የሆነው ብርሀን እና ሰላም ሳንሱር መጀመሩን ለማወቅ ተችሎአል። ድርጅቱ የህትመት ስራ ስታንዳርድ ውል በሚል ርእስ ያወጣው አዲስ የስራ ውል በአንቀጽ 10 ላይ ህግን የተላለፈ ይዘትን አለማተም ...

Read More »

ጀግናዋ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ በህመም ላይ ናት ተባለ

 ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአላማ ጽናቷ ተደናቂነትን እያተረፈች የመጣቸው ብእረኛዋ መምህርት ርእዮት አለሙ በጡቷ ላይ በተፈጠረ እጢና በጨጓራ ህመም እየተሰቃየች በመሆኑዋ ጥቁር አንበሳ እየተመላለሰች በመታከም ላይ መሆኑዋን ፍኖተ ነጻነት ዘግቧል። ሀኪሟ የናሙና ጥናቱን አድርጎ የቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት መወሰኑን ጋዜጣው ዘግቧል። ተደጋጋሚ የህክምና ቀጠሮ ቢኖራትም ማረሚአ ቤቱ አንዴ መኪና የለኝም፣ ሌላ ጊዜ አጃቢ የለኝም በማለት እያጉላላት መሆኑን ቤተሰቦቿን ...

Read More »

የኢትዮጵያ እስር ቤቶች በጋዜጠኞችና በተቃዋሚ ድርጅት አባላት ተሞልተዋል ተባለ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ይህን ያስታወቁት የአፍሪካ የሲፒጄ አስተባባሪ የሆኑት ሙሀመድ ኬይታ በኒውዮርክ ታይምስ ላይ ባወጡት ጽሁፍ ነው።  ሙሀመድ ኬይታ የአፍሪካ ነጻ ሚዲያ ችገሮች በሚል ርእስ ባወጡት ጽሁፍ ፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ እያደገ ሲሄድ ፣ በነጻው ፕሬስ ላይ የሚደርሰው አፈናም በዚያው ልክ እያደገ ነው ብለዋል። በአፍሪካ ውስጥ የሚካሄደውን ልማት የሚዘግቡ ጋዜጠኖች ፣ ስለ ሙስና፣ እና የውጭ አገር ባለሀብቶች ...

Read More »

በኑሮ ውድነቱ የፋሲካ በአል የጨለመበት የአትዮጵያ ህዝብ በቴዲ ሙዚቃ ብርሀን ለማየት እየሞከረ ነው

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን የዘንድሮው የፋሲካ በአል ከእስከ ዛሬዎቹ ሁሉ ደብዝዞ መዋሉን ፣ ለዚህም ምክንያቱ የዋጋ ንረቱ መሆኑን የተለያዩ  ሰዎችን በማናገር በላከልን ዘገባ ላይ አመልክቷል። በግ ከአንድ ሺ እስከ 4 ሺ፣ ዶሮ ከ150 እስከ 200 ብር ፣ ቅቤ ከ160 እስከ 180 ሲጨት በሰነበተባት አዲስ አበባ፣ ህዝቡ በአሉን በድብርት ቢያሳልፍ የሚገርም አይሆንም ያለው ዘገባ፣ ይሁን ...

Read More »

በኦሮሚያ ክልል የቡራዮ ከተማን ሁለት ከንቲባዎች ጨምሮ 25 የአካባቢው ባለሥልጣናት ታሠሩ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፍኖተ ነፃነት ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው የከተማው ከንቲባ አቶ ቸርነት ጉርሜሳና የቀድሞ የከተማው ከንቲባ አቶ ኃይሉ ደቻሳ ከሌሎች 23 የአካባቢው ባለሥልጣናት ጋር በሙስና ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ውለዋል፡፡ “ቡራዮ”በየደረጃው ያሉ የመንግስት ባለሥልጣናት “በካሽ ልምጣ ወይስ በክላሽ?” እያሉ መሬት የዘረፉበት አካባቢ ነው እየተባለ በቀልድ መልክ  በስፋት ይወራል። የታሠሩት የአካባቢው ባለስልጣናት  እርስ በርስ በጥቅም በመቆላለፍ በተለያየ ሰው ...

Read More »

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ሰሞኑን የሰጡትን መግለጫ መኢአድ፦”አሳፋሪ” አለው

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከቤንች ማጅ ዞን ጉራ ፈርዳ ወረዳ ስለተፈናቀሉት የአማራ ተወላጆች አስመልክቶ የደቡብ ክልል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ሰሞኑን የሰጡትን መግለጫ መኢአድ፦”አሳፋሪ” አለው። አቶ ሽራው ሽጉጤ ጉዳዩን አስመልክተው ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ፦”ምንም የተባረረ ሰው የለም። ደን ሲያቃጥሉና ሲጨፈጭፉ የነበሩ 33 ህገ-ወጦች ከክልሉ እንዲወጡ ተደርገዋል” ማለታቸው ይታወሳል። መኢአድ   እንዳለው ግን ከክልሉ እየተባረሩ ያሉት ሰዎች ደን ያቃጠሉና የጨፈጨፉ ...

Read More »

አሜሪካዊው ጂም ኦንግ ኪም አዲሱ የአለም ባንክ ፕሬዚዳንት ሆነው ተመረጡ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኮሪያዊው አሜሪካዊው የጤና ኤክስፐርት የሆኑት ጂም ዮንግ ኪም በምርጫ ውድድሩ ወቅት የናይጀሪያዊዋ የፋይናንስ ሚኒሰትር ከሆኑት ሚስ ኒጎዚ ኦኮንጆ ኢዊአላ ከፍተኛ ፉክክር ገጥሞአቸው ነበር። በስልጣን ላይ ያሉትን ሮበርት ዞሊክን የሚተኩት የ52 አመቱ ኪም ፣ በደሀ አገሮች ውስጥ የተስፋፉትን የኤች አይ ቪ ኤድስ ስርጭትና የቲዩበር ክሎሲስ በሽታዎችን ለመዋጋት ከፍተኛ ሚና መጫወታቸው ተነግሯል። የአለም የገንዘብ ድርጅት ...

Read More »

በሮተርዳም የማራቶን ውድድር ኢትዮጵያውያን አትሌቶች አሸነፉ

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በወንዶች የማነ ጸጋዬ በሁለት ሰዓት ከአራት ደቂቃ ከ48 ሰከንድ፣ በሴቶች ቲኪ ገላና በሁለት ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ58 ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፉ፣ በወንዶች የማነ ጌቱ ሁለተኛ ኬንያዊው ሞሰስ ሞሶፕ ደግሞ ሦስተኛነትን ደረጃ አግኝተዋል። አትሌቶቹ በለንደን ኦሎምፒክ የሚያሳትፍ ውጤት በማግኘታቸው በእጅጉ መደሰታቸውን ገልጠዋል። ________________________________________________________________________________________________ ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate ...

Read More »