ጀግናዋ ጸሀፊና መምህርት ርእዮት አለሙ በህመም ላይ ናት ተባለ

 ሚያዚያ ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በአላማ ጽናቷ ተደናቂነትን እያተረፈች የመጣቸው ብእረኛዋ መምህርት ርእዮት አለሙ በጡቷ ላይ በተፈጠረ እጢና በጨጓራ ህመም እየተሰቃየች በመሆኑዋ ጥቁር አንበሳ እየተመላለሰች በመታከም ላይ መሆኑዋን ፍኖተ ነጻነት ዘግቧል። ሀኪሟ የናሙና ጥናቱን አድርጎ የቀዶ ህክምና እንደሚያስፈልጋት መወሰኑን ጋዜጣው ዘግቧል። ተደጋጋሚ የህክምና ቀጠሮ ቢኖራትም ማረሚአ ቤቱ አንዴ መኪና የለኝም፣ ሌላ ጊዜ አጃቢ የለኝም በማለት እያጉላላት መሆኑን ቤተሰቦቿን ዋቢ አድርጎ ጋዜጣው ዘግቧል።

ርእዮት አለሙ 14 አመት የግፍ እስር እና  33 ሺ ብር መቀጣቷ ይታወቃል።  የቀድሞው የፖሊስ ኮሚሽነር የነበሩት ሀሰን ሽፋ ርእ ት በጓደኞቹዋ ላይ መስክራ እንድትወጣ ለማባበልና ለማስፈራራት ሙከራ ቢያድርጉም ርእዮት ግን አሻፈረኝ ብላለች። አቶ ሀሰን ይህን አቋም ከያዝሽ ለምን ጫካ አትገቢም እንዳሉዋት ርእዮት ለፍርድ ቤት መግለጧ ይታወሳል። አሁንም ይቅርታ ጠይቃ እንድትፈታ  ሽማግሌዎች ወደ ቃሊቲ ቢላኩም ርእዮት ይቅርታ ጤኢቃ እንደማትፈታ ግልጽ አድርጋለች።

የርእዮት የአቋም ጽናት የሚደነቅ መሆኑን ፣ በዚህም ጽናቷ ለተለያዩ ሽልማቶች መታጨት እንዳለባት አስተያየታቸውን የሚሰነዝሩ በርካቶች ናቸው። ኢሳት ርእዮት የአውሮፓ ህብረትንና የሌሎችን ምእርባዊያንን ትኩረት በማግኘት ለሽልማት እንድትበቃ ጥረት በማድረግ ላይ ነው።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide