በኑሮ ውድነቱ የፋሲካ በአል የጨለመበት የአትዮጵያ ህዝብ በቴዲ ሙዚቃ ብርሀን ለማየት እየሞከረ ነው

ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን የዘንድሮው የፋሲካ በአል ከእስከ ዛሬዎቹ ሁሉ ደብዝዞ መዋሉን ፣ ለዚህም ምክንያቱ የዋጋ ንረቱ መሆኑን የተለያዩ  ሰዎችን በማናገር በላከልን ዘገባ ላይ አመልክቷል። በግ ከአንድ ሺ እስከ 4 ሺ፣ ዶሮ ከ150 እስከ 200 ብር ፣ ቅቤ ከ160 እስከ 180 ሲጨት በሰነበተባት አዲስ አበባ፣ ህዝቡ በአሉን በድብርት ቢያሳልፍ የሚገርም አይሆንም ያለው ዘገባ፣ ይሁን እንጅ የበአሉን ድብርት በቴዲ አፍሮ አዲስ ሙዚቃ ለማባረር ሙከራ ሲያደርግም ተስተውሏል ብሎአል።

የቴዲ አፍሮን አዲሱን ሙዚቃ ለመስማት ህዝቡ በእየሙዚቃ ቤቱ ተስልፎ እንደነበር የገለጠው ዘጋቢያችን፣ የዘንድሮው በአል ያለቴዲ ሙዚቃ የማይታሰብ ነው የሚሉ ሰዎች እንዳጋጠሙት ዘግቧል።  የ32 አመቱ ሻምበል ማሩ የዘንድሮው በአል ለእርሱ ምንም ትርጉም እንዳልሰጠው ገልጦ፣ ይሁን እንጅ በቴዲ ጥቁር ሰው ልቡ እንደረካ አልሸሸገም። በአድዋ ድል እና በተወናዮቹ ላይ ተንተርሶ የተዜመው የቴዲ አዲስ አልበም መታሰቢያነቱ ለጠሀይቱ ብጡል፣ ለባለቅኔው ጸጋየ ገብረመድህንና ለቀድሞ ወታደሮች የሚል በመሆኑ በህዝብ ዘንድ ተወዳጅ እንዲሆን ያደረገው ይመስላል ሲል ዘጋቢያችን ገልጧል።

የጥቁር ሰው አልበም የኢትዮጵያን ታሪክ በተለይም የአድዋን ድል እና የአጼ ሚኒክን ሚና ለመደለዝ በስልጣን ላይ የሚገኘው መንግስት የጀመረውን ታሪክ የመከለስ እንቅስቃሴ ለመቃወም የቀረበ ነው የሚል አስተያየት እየተሰነዘ ነው ሲል ጽፏል።

ቴዲ በኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የዘር ልዩነት

ስለ ፍቅር ሲባል ስለጸብ ካወራን ተሳስተናል
አንድ ላይ ብንሆንም ተለያይተናል
አጥተናል እውነት ነው ተቸግረን ብዙ አያተናል
የመጣነው መንገድ ያሳዝናል በማለት ገልጦ፣ መታወቂያችን ስለሆነው ረሀብ ደግሞ ”

አፈር ይዞ ውስጡ አረንጓዴ

ለምን ይሆን የራበው ሆዴ” በማለት ጠይቋል።

________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide