በቶሮንቶ ከተማ ታላቅ ሠላማዊ ሰልፍ ተካሄደ

የግልገል ጊቤ ቁጥር አንድ የኃይል ማመንጫ ግድብ በደለል ተሞላ።

ሚያዚያ ፲፭ (አስራ አምስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በዚህ በቶሮንቶ ከተማ በዋልድባ፤ በአሰቦት እና በዝቋላ ገዳማት ላይ የኢትዮጵያ መንገሥሰት እያከሄደ ያለውን ታሪክን፤ ሃይማኖትን እና ለዘመናት ተጠብቀው በነበሩት እንሰሳትና እፀዋት ላይ እያደረሰ ያለውን ውድመት ለመቃወም በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክረስቲያን በጠራው ሠላማዊ ሰልፍ የተለያዩ የሰባዊ መብት ድርጅት ተወካዮች የተገኙ ሲሆን በሠላማዊ ሰልፉ ላይ ተለያዩ መንፈሳዊ መዝሙሮችና መፈክሮች ተደምጠዋል።ሃይል የእግዚአብሔር ነው፣ ተው፤  ተው በሏቸው!የዋልድባ ገዳም የሰኳር ፋብሪካ አይሆንም፤ የአብያተ ክርስቲያናትና የገዳማት ቃጠሎ ይቁም፣ ካናዳ አምባገነኖችን መርዳት አቁሚ፣ መለሠ ዜናዊ ብሔራዊ ጠላት ነው ወዘተ የሚሉ መፈክሮች ቀርበዋል።

ከዚህ በተጨማሪ ለተለያዩ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ መብት ተቀርቋሪ ድርጆቶችና መንግሥታት በአገራችን  ውስጥ በአብያተ ክርስቲያናትና ገዳማት ላይ እየደረሰ ያለውን ጥፋት፤ በካናዳ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክረስቲያን የተዘጋጀው ልዩ ደብዳቤ በኦታዋ ለካናዳ ጠቅላይ ሚንስትር፤ ለውጭ ጉዳይ ሚንስተር እና ለኢሚግሬሽን ሚኒሰተር በእጅ ተሰጥቷል።

ከዚያም በመቀጥል ሠላማዊ ሰልፉ ከኦንታሪዮ ክህለ አገር ፓርላማ  ተነሰቶ መንፈሳዊ መዝሙርና መፈከር እያሰማ ወደ ቶሮንተ ከተማ ማዘጋጃ ቤት በማምራት ከማጋጃ ቤቱ ፊት ለፊት በመሰባሰብ በከፍተኛ ድምጽ መፈክር በማሰማት ጥቂት ቆይታ ካደረገ በኋላ በታላቅ መንፈሳዊ መዝሙርና መፈከር እየታጀበ ጉዞውን ወደ አሚሪካን ቆንሲል ጽ/ቤት አቅንቷል። ከቦተውም እንደደረሰ  ሠላማዊ ሠለፈኛው ደምጹን ከፍ በማድረግ የአሚሪካ መንግሥት ለአምባ ገነኑ የወያኔ መንግሥት የሚሰጠውን እርዳታ እንዲያቆም መፈከር ካሰማ በኋላ ሠላማ ሰልፉ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ከብርሀኑ ተክለማርያም ዘገባ ለመረዳት ተችሎአል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide