የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ ሶስት የአማራ ክልል አመራሮችን ማገቱን አስታወቀ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአማራ ወጣቶች የጋራ ንቅናቄ በአማራ ክልል ላኩማ ወረዳ ሁለት የሚሊሽያ ሀላፊዎችንና አንድ የወረዳ አስተዳዳሪን በቁጥጥር ስራ ማድረጉን ገለፀ፡፡ ንቅናቄው ሰሞኑን 22 የፖለቲካ አመራሮች በላኩማ ወረዳ በሚገኘው በሰላ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ በስብሰባ ላይ እንዳሉ በቁጥጥር ስር ካዋለ በኋላ መልቀቁን ገልጾ ሶስቱን አመራሮች ግን አሁንም ድረስ በቁጥጥር ስር አድርጎ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡ የተያዙት አመራሮች በቁጥጥር ስር ውለው ...

Read More »

በአዲስአበባ ከተማ የማጅራት ገትር ወረርሽኝ በአዲስ መልክ ተቀሰቀሰ

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ ከተማ ባለፈው ዓመት ሚያዚያ ወር 2005 አካባቢ ተከስቶ የነበረው ማጅራት ገትር ወረርሽኝ እንደገና በአዲስ መልክ በመቀስቀሱ የክልሉ ጤና ቢሮ ሕዝቡን የመከተብ ስራ ላይ መጠመዱ ተሰማ፡፡ ክትባቱ በሁሉም ጤና ጣቢያዎች በመሰጠት ላይ ሲሆን ክትባቱን መውሰድ ያለባቸው ደግሞ ዕድሜያቸው ከ30 በታች የሆኑ ነዋሪዎች ብቻ መሆናቸው ለምን የሚል ጥያቄ አስነስቶአል፡፡ ምንጮቻችን እንደሚሉት መንግስት ...

Read More »

በጋምቤላ ለሞቱ የሰራዊቱ አባላት ካሳ ተከፈለ – ለሞቱ ነዋሪዎች ግን ካሳ አለመከፈሉ ታወቀ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በጋምቤላ ክልል ንዌር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሚኒኛንግ ከተማ ተካሂዶ በነበረ ግጭት ለሞቱ የመከላከያ ሰራዊት አባላት በነብስ ወከፍ 90 ሺህ ብር እንዲከፈል ተወሰነ፡፡ ለሞቱ ሲቪል ሰዎች የካሳ ክፍያ ሳይፈጸም መቅረቱን ግን ምንጮች ለኢሳት ገልጸዋል፡፡ የዞኑ ሚሊሺያዎች እና ነዋሪዎች ከመከላከያ አባላት ጋር ባደረጉት ግጭት ስምንት የመከላከያ ሰራዊት አባላት ሞተው ሰባት መቁሰላቸውን መዘገባችን የሚታወስ ነው፡፡ ከሞቱ እና ከቆሰሉት ...

Read More »

በአዲስአበባ የውሃ ችግርን ተባብሶ ቀጥሎአል

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስአበባ ከተማ የውሃ ሽፋን 94 በመቶ ደርሶአል ቢባልም በአሁኑ ወቅት መሃል አዲስአበባን ጨምሮ አብዛኛው አዳዲስ የማስፋፊያ አካባቢዎች በቂ የውሃ ሽፋን የማያገኙት ከ40 በመቶ አይበልጡም። የአዲስአበባ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ባለሰልጣን እንደሚናገረው የከተማዋ የውሃ ሽፋን እያደገ ቢመጣም ውሃን በቁጠባ የመጠቀም ልምድ ባለመዳበሩ እስከ40 በመቶ የሚደርስ ከፍተኛ ብክነት በከተማዋ ውስጥ አለ ብሎአል፡፡ ይህ ሁኔታም ያለውን ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት ጠየቁ

ጥቅምት ፲፭ (አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የሰሜን ኮርያ ዲፕሎማት ሆነው ሲያገለግሉ የነበሩ ኮርያዊ በደቡብ ኮርያ ኢምባሲ ጥገኝነት መጠየቃቸው ተገለጸ፡፡ ስማቸው ይፋ ያልሆነው ዲፕሎማት የሚወክሉትን ሀገር ትተው ከአንድ ወር በፊት የደቡብ ኮርያን መንግስት አዲስ አበባ በሚገኘው ኢምባሲ በኩል ጥገኝነት መጠየቃቸውን የተለያዩ የሁለቱ ኮርያዎች መገናኛ ብዙሀን በመዘገብ ላይ ናቸው፡፡ ዲፕሎማቱ ወደ ደቡብ ኮርያ ኢምባሲ በመግባት ጉዞአቸውን እንዲያመቻችላቸው ጠይቀው ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ ኮርያ ማቅናታቸው ...

Read More »

በእርዳታ ስም በርካታ ዜጎች ስቃይ እየደረሰባቸው ነው

ጥቅምት ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በባሌ ዞን በጎባ ከተማ ቀበሌ 03 ልዩ ስሙ አዲስ ከተማ እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚገኘው ኤም ኦ ሲ ሚሺኒሪ ኦፍ ቻርቲ የተባለው ድርጅት በ1984 ሲቋቋም ዋና አላማው በዞኑ እና በአካባቢው የሚኖሩ እና እንዲሁም ከመላው ኢትዮጵያ የሚመጡ የአካል ጉዳት ያለባቸው ማለትም፤ መስማት እና ማየት የማይቸሉ፤ መራመድ የማይችሉ፤የአዕምሮ ዘገምተኞች፤እንዲሁም በዕድሜ የገፉ እና ጧሪ አልባ አዛውንቶችን ...

Read More »

የመንግስት የልማት ድርጅቶች ተቆጣጣሪ እና የፕራይቬታይዜሺን ኤጀንሲ በፖለቲካ ጫና ስራውን በአግባቡ እየተወጣሁ አይደለም አለ፡፡

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የልማት ኤጀንሲው የስራ ሃላፊ ለዘጋቢያችን እንደነገሩት ድርጅቱ በተሰጠው ስልጣን እና ሃላፊነት የተለያዩ የመንግስት ይዞታ የነበሩ ተቋማት በጥናት ለህዝብ ጥቅም የመሸጥ የመለወጥ ፤ ስልጣን ተሰጥትቶታል፡፡ ይህን ስራ ተግባራዊ ለማድረግ አዳጋች ሁኖብኛል ሲሉ ገልጸዋል፡፡ እስካሁንም የአዋሺ አግሮ ኢንዱስትሪ ቲብላ እርሻ፣ የመካከለኛ አዋሺ የእርሻ ልማት፣  በሰሜን ኦሞ እርሻ ልማት ውስጥ የሚገኘው ኦሞራቴ እርሻ ልማት በመንግስት አመራሮች ...

Read More »

ለብርሀንና ሰላም ማተሚ ያ ቤት አዲስ ዋና ስራ አስኪያጅ መሾሙ ሰራተኛው ን ድንጋጤ ላይ ጥሎታል

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ብርሀንና ሰላምን ለ20 አመታት የመሩት የኢህአዴግ ደጋፊ የሆኑት ወ/ሮ ሙሉወርቅ ገብረህይወት  ጡረታ ወጥተው በእርሳቸው ምትክ የህወሀት አባሉ አቶ ተካ አባዲ ዛሬ ስራስኪያጅ ሆነው ተሹመዋል። የአርቲስቲክ ማተሚያ ቤት ስራ አስኪያጅ ሆነው የቆዩት አቶ ተካ፣ ከሰራተኛው ጋር ከፍተኛ ውዝግብ ውስጥ በመግባትና በአስተዳደራቸው ብልሹነት ይታወቃሉ። ዛሬ ከሰአት ሹመቱ ይፋ ሲሆን የብርሀንና ሰላም ሰራተኞች እና ሌሎች የአስተዳደር ...

Read More »

ትልቁ የዲን መማሪያ ማዕከል ታሸገ::

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የሚገኘው ትልቁ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት ቤት በመንግስት ትእዛዝ እንዲታሸግ ተደርጓል፡፡ በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከ600 በላይ ተማሪዎች የእስልምና ሀይማኖት አስተምሮዎችን ይማሩበት ነበር። መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የሀይማኖት ተቋማትን እያሸገ ነው። መንግስት  ድርጅቶቹ የአክራሪነት መፈልፈያ ሆኗል በማለት ይከራከራል። የመንግስትን እርምጃ የሚቃወሙ ሙስሊሞች በበኩላቸው መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈልና ለማጋጨት እርምጃ ...

Read More »

በቤይሩት የኢትዮጵያዊቷ ህይወት በመኪና አደጋ አለፈ

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤይሩት ኢትዮጵያዊቷ በመኪና አደጋ  ደርሶባት አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ባለመቻሏ ህይወቷ አለፈ። ኢትዮጵያዊቷ አስቸኳይ ህክምና ማግኘት ያልቻለችው- ቆንስላ ጽፈት ቤቱ ሀላፊነት አልወስድም በማለቱ እንደሆነ ተዘግቧል። በዚህም ሳቢያ መዳን ስትችል የነበረችው ወጣት  ህክምና ባለማግኘቷ ለህልፍት መብቃቷ፤ ዜናውን በማህበራዊ መገናኛዎች የተከታተሉትን ሁሉ አሳዝኗል። የቆንጽላ ጽህፈት ቤት ሠራተኞች፤  ለግድብና ለተለያዩ ነገሮች እያሉ ኢትዮጵያውያኑ የሰው ፊት እያዩ ተንገላተውና ...

Read More »