ትልቁ የዲን መማሪያ ማዕከል ታሸገ::

ጥቅምት ፲፬(አስራ አራት)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-በአዊ ዞን ቻግኒ ከተማ የሚገኘው ትልቁ የእስልምና ሀይማኖት ትምህርት ቤት በመንግስት ትእዛዝ እንዲታሸግ ተደርጓል፡፡

በትምህርት ቤቱ ውስጥ ከ600 በላይ ተማሪዎች የእስልምና ሀይማኖት አስተምሮዎችን ይማሩበት ነበር።

መንግስት ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ የሀይማኖት ተቋማትን እያሸገ ነው። መንግስት  ድርጅቶቹ የአክራሪነት መፈልፈያ ሆኗል በማለት ይከራከራል።

የመንግስትን እርምጃ የሚቃወሙ ሙስሊሞች በበኩላቸው መንግስት ሙስሊሙን ለመከፋፈልና ለማጋጨት እርምጃ እየወሰደ ነው በማለት ክስ ያሰማሉ።