ኦህዴድ 25ኛ አመት በአሉን ለማክበር ለሚያደርገው ዝግጅት የመንግስት ሰራተኛውን ለቅስቀሳ አሰማራ

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኦህዴድ የ25ኛ አመት በአሉን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማክበር የነበረው ፍላጎት ከተደናቀፈ በሁዋላ፣ በደራ ወረዳ ጉንዶመስቀል ከተማ ለማክበር ከፍተኛ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን፣ የተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ተዘግተው ሰራተኞች የገጠሩን ህዝብ እንዲቀሰቅሱ ተሰማርተዋል። መጋቢት 10 የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናት ጉንዶመስቀል ይገባሉ ተብሎ በመጠበቁ እጅግ በርካታ የፌደራል ፖሊስ አባላትና የደህንነት ሰራተኞች ወደ ከተማዋ ገብተዋል። የመንግስት መስሪያ ቤቶች ...

Read More »

ኢህአዴግ በመንግሥት  በጀት ለካድሬዎችና አባላቱ ሥልጠና   እየሰጠ ነው።

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢህአዴግ ካድሬዎችን የሚያሰለጥነው አካዳሚ ፕሬዚዳንት የሆኑት አቶ አዲሱ ለገሰ ሰሞኑን በሰጡት መግለጫ  በመለስ ዜናዊ ስም የተሰየመው  የአመራር አካዳሚ በመንግስት በጀት ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ በአምስት ዙሮች 2ሺ 500 ያህል ከፍተኛ አመራሮችን፣ ከ30ሺ በላይ መካከለኛ አመራሮችን አሰልጥኗል፡፡ አካዳሚው ያለአንዳች ፈቃድ ከ2003 ዓ.ም እስከ 2006 ዓ.ም ሲሰራ ከቆየ በሃላ በ2006 ዓ.ም በሚኒስትሮች ደንብ ቁጥር 321/2006 ተጠሪነቱ ...

Read More »

ድምጻችን ይሰማ ትግሉን ወደ አንድ ደረጃ ከፍ ሊያደርግ ነው

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፉት ሶስት አመታት የኢትዮጵያን ሙስሊሞች በመወከል ድምጹ እንዲሰማለት ጠይቆ፣ መለስ የተነፈገው ድምጻችን ይሰማ አመራሮቹን ለማስፈታትና ጥያቄዎቹ እንዲመለሱለት ግፊት ለማድረግ እስካሁን ሲከተለው ከነበረው የትግል ስልት አንድ ደረጃ ከፍ ያለ የትግል ስልት ይፋ እንደሚያድርግ አስታውቋል። ድምጻችን ይሰማ ” መብቴን ካላከበርክ እኔም..” በሚል ርእስ ባወጣው መግለጫ ፣ ህዝብ ሲመረው መብቴ ይከበርልኝ ከሚል ጩኸት መብቴን ካላከበርክ እኔም ...

Read More »

የ119ኛው አድዋ በአል በተለያዩ አህጉሮች እየተከበረ ነው

መጋቢት ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአሉ በአውስትራልያ ክዊንስላንድ ግዛት ነዋሪ በሆኑ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን እሁድ መጋቢት 7 ቀን 2007 ዓም ተከብሯል። በበአሉ ላይ በግዛቱ ነዋሪ የሆኑ በርካታ ኢትዮጵያውያን የተገኙ ሲሆን የአድዋን ድል ታሪካዊነትን የዳሰሰ ሰፋ ያለ ዝግጅት ለታዳሚው ቀርቧል:: ዓድዋን አስመልክቶ በፕሮጀክተር በታገዘና በምስልና ድምጽ የተደገፉ ማስረጃዎች በቀረቡበት በዚህ ዝግጅት ላይ የዓጼ ምንሊክን አስተዋይነት የቴጌ ጣይቱ ብልህነትና የኢትዮጵያ ...

Read More »

የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ያነሱትን ተቃውሞ ተከትሎ ፖሊሶች አንድ ሰው ገድለው 8 አቆሰሉ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግዲቾ ብሄረሰብ አባላት ተቃውሞውን ያስነሱት መሬታቸው ለትምባሆ ተክል እርሻ ለአንድ ባለሀብት መሰጠቱን ተከትሎ ነው። በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በምእራብ አባያ ወረዳ የሚኖሩት ቁጥራቸው እስከ 5 ሺ የሚደርሱ የብሄረሰቡ አባላት፣ ቀደም ብሎ በአባያ ሃይቅ መካከል በሚገኘው ደሴት ይኖሩ ነበር። ደሴቱ በሃይቁ ሙሉ በሙሉ መሸፈኑን ተከትሎ የብሄረሰቡ አባላት ሃንቲ ወደ ሚባል አጎራባች ቀበሌ በመሄድ ኑሮአቸውን ...

Read More »

መድረክ ከምርጫ ጋር በተያያዘ የተፈጸሙ ጥቃቶችን ዘርዝሮ አቀረበ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተለያዩ ክልሎችን የሚሸፍነው ሪፖርት፣ በዜጎች ላይ የተፈጸሙ ዝርዝር ጥቃቶችን አቅርቧል።  በትግራይ ክልል በአጽቢወንበርታ ምርጫ ክልል ለሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት የመድረክ ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ወ/ገብርኤል ኃይሉ የዕጩነት መታወቂያ እንደያዙ ተይዘው ከታሰሩ በኋላ የአስር ወራት የእስራት ቅጣት ተፈርዶባቸዋል፡፡  “በቆላ ተንቤን ወረዳ በወርቅ አምባ ምርጫ ክልል የክልል ም/ቤት ዕጩ ተወዳዳሪ የሆኑት አቶ ብርሃን ንጉስ ተክለእግዚም በተመሳሳይ ...

Read More »

ወደ አረብ ሀገራት በሕገወጥ  መንገድ የሚደረገው ጉዞ እየጨመረ ነው

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወደ አረብ ሀገራት በሕጋዊ መንገድ የሚደረገው ጉዞ  በሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ከአንድ ዓመት በፊት ከታገደ በሃላ ሕገወጥ ዝውውሩ በከፍተኛ ደረጃ ማደጉን ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ የሥራ ስምሪት ህጉ እስኪስተካከል ድረስ ለስድስት ወራት ብቻ ጉዞው እንዲታገድ መንግሥት ወስኖ የነበረ ቢሆንም፣  እገዳው  ሳይነሳ ከአንድ ዓመት ከአራት ወራት በላይ አስቆጥሮአል፡፡ በዘርፉ የተሰማሩት ድርጅቶችም አብዛኛዎቹ ...

Read More »

የዲፕሎማቲክና የሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ ኢትዮጵያዊያን እና የቻይና ዜጎች ብቻ አንዱ ወደ ሌላኛው ሀገር ሲሄድ ያለቪዛ እንዲገቡ የሚያስችል ስምምነት ሰሞኑን ለፓርላማ ቀረበ፡፡

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስምምነቱ መሠረት የዲፕሎማትና ሰርቪስ ፓስፖርት የያዙ የሁለቱ ሀገራት ሰዎች ለ30 ቀናትና እንደአስፈላጊነቱ ሊራዘም የሚችል ቆይታ ያለቪዛ እንዲገቡ ይፈቅዳል፡፡ ይህን ቪዛን የሚያስቀረው ስምምነት ያስፈለገበት ዋናው ምክንያት የሁለቱ ሀገራት ዜጎች ለስራ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ እየጨመረ በመምጣቱ ነው ተብሎአል፡፡ በሁለቱ ሀገራት ስምምነት መሰረት ከምክትል ሚኒስትር በላይ የሆነ ማእረግ ያላቸው የማእከላዊ መንግስቱ ባለስልጣናትና ኦፊሰሮች ወይንም ከሜጀር ጄኔራል በላይ ...

Read More »

መንግስት በውጭ የሚኖረውን ዲያስፖራ ለመያዝ ይረዳኛል በሚል ከጀመራቸው የቤት ልማት ፕሮግራም ውስጥ 40 በ60 በሚባለው ፕሮግራም የሚገነቡ ቤቶች ከምርጫ 2007 በፊት ለተጠቃሚዎች ማስተላለፍ ሳይችል ቀረ፡፡

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሚቀጥለው ሳምንት ከመጋቢት 10 እስከ 13 ድረስ ባሉት ቀናት የአዲስአበባ አስተዳደር 20 በ80 ተብሎ የሚታወቀውን የኮንዶሚኒየም 35 ሺ ቤቶች ዕጣ በማውጣት ለእድለኞች ለማስተላለፍ ያቀደ ሲሆን በዚህ የዕጣ አወጣጥ ፕሮግራም ላይ 40 በ 60 የሚባለውና አብዛኛው ዲያስፖራ ተመዝግቦበታል የተባለው ዕጣ እንደማይወጣ ታውቆአል፡፡ የአዲስአበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ድሪባ ኩማ ሰሞኑን በተካሄደው የአስተዳደሩ ም/ቤት ጉባኤ ላይ ...

Read More »

አርሶ አደሮች ገንዘባችንን ተቀማን አሉ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በብአዴን አመራሮች እና በግንባር ቀደም አርሶ አደሮቸ ላለፉት አምስት አመታት የወረቀት ፈብሪካ ለመገንባት በሚል ከተሸላሚ አርሶ አደሮች የተሰበሰበው በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገማ እንደማይታወቅ አርሶ አደሮች ተናግረዋል። ገንዘባቸው እንዲመለስልቸው ቢወተውቱም  ምላሽ ማጣታቸውን ተናግረዋል። በሰባተኛው የአርሶአደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው ዘጋቢያችን   ያነጋገራቸው አርሶ አዶሮች “ከአምስት አመታት ...

Read More »