አርሶ አደሮች ገንዘባችንን ተቀማን አሉ

መጋቢት ፬(አራት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአማራ ክልል በባህር ዳር ከተማ በብአዴን አመራሮች እና በግንባር ቀደም አርሶ አደሮቸ ላለፉት አምስት አመታት የወረቀት ፈብሪካ ለመገንባት በሚል ከተሸላሚ አርሶ አደሮች የተሰበሰበው በሚልዮን የሚቆጠር ገንዘብ የት እንደገማ እንደማይታወቅ አርሶ አደሮች ተናግረዋል። ገንዘባቸው እንዲመለስልቸው ቢወተውቱም  ምላሽ ማጣታቸውን ተናግረዋል።

በሰባተኛው የአርሶአደሮች እና ከፊል አርብቶ አደሮች ስብሰባ ላይ የተገኘው ዘጋቢያችን   ያነጋገራቸው አርሶ አዶሮች “ከአምስት አመታት በፊት በሁለተኛው እና በሶስተኛው የአርሶ አደሮች በዓል ላይ በክልሉ ካቢኔ ጎትጓችነት የኢንዱስትሪ አክሲዩን ባለቤት ትሆናላችሁ በሚል ጥሪታችንን አሟጠን፣  ከ70ሺ ብር ጀምሮ በየአመቱ በአስር ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ብናዋጣም እስካሁን ምንም ነገር ለማየት አልቻልም” ብለዋል።

ከስራ አሰፈፃሚው አቶ አለምነው መኮንን በተገኝ መረጃ መሰረት የአማራ ፐልፕ የወረቀት ፋብሪካን ለመገነባት ሙሉ በሙሉ ከተሸላሚ አርሶ አደሮቸ አክሲዩን እንዲዋጣ ተደርጎ  ከ 21 ሚልዩን ብር በላይ ተሰብስቧል።