የኢትዮጰያ መንግስት  በተያዘው ዓመት 3 ሚሊዮን ለሚጠጉ ሰዎች እርዳታ  እንደሚያስፈልገው ማሳወቁን ተመድ ገለጸ።

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ተመድ የመንግስትን ሪፖርት ዋቢ አድርጎ ባወጣው መግለጫ ዘንድሮ  በኢትዮጰያ 2.9 ሚሊዮን ሰዎች አስቸኳይ የምግብ እርዳታ ያስፈልጋቸዋል ብሏል። ከተረጅዎቹ መካከል 38 በመቶው  ከኦሮሚያ፣ 31 ከመቶው ደግሞ ከሶማሌ፣ 12 በመቶው ከትግራይ እና 6 በመቶው ካማራ ክልሎች መሆናቸውን ሪፖርቱ ያመለክታል። ለተረጅዎቹ ድጋፍ ለማድረግ  386 ሚሊዮን ዶላር  እንደሚያስፈልግ ያመለከተው ተመድ፤ ይሁንና  የረድኤት ድርጅቶች የፈንድ እጥረት እንዳለባቸው ...

Read More »

መንግስት- የትግራይ ህዝብ ዲሞክራሲያዊ ድርጅት  አባላት  ናቸው ባላቸው ሁለት  የመቀሌ ነዋሪዎች ላይ የሽብርተኝነት ክስ መሰረተ

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በኢትዮጵያ ውስጥ አባላትን ሲመለምሉና  መንግሥትንና ተቋማቱን ሲሰልሉ  ተደርሶባቸዋል፣ እና  የትግራይ ሕዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ዴምሕት)  ቡድን ምልምሎች  ናቸው>>  ባላቸው ሁለት ተጠርጣሪዎች ላይ ዐቃቤ ህግ ክስ መሠረተ፡፡ <<የወንጀሉ ድርጊት በሚሰጠው ውጤት ሙሉ ተካፋይ በመሆን የፖለቲካ፣ የሃይማኖት ወይም የአይዲዎሎጂ ዓላማን ለማራመድ፣ ሕዝብን ለማስፈራራትና በመንግሥት ላይ ተፅዕኖ ለማሳደር ሲንቀሳቀሱ ነበር>> ተብለው  ክስ የተመሠረተባቸው፣ ነዋሪነታቸው በትግራይ ክልል ...

Read More »

በባሌ ብሔራዊ ፓርክ የተቀሰቀሰውን እሳት ለማጥፋት ሲታገል የነበረው ወጣት ህይወቱ አለፈ

መጋቢት ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የአካባቢ ተቆርቋሪና የማህበረሰብ ቱሪዝም ኤክስፐርት  የሆነው ወጣት  ቢኒያም አድማሱ ሰሞኑን በባሌ ተራሮች ብሄራዊ ፓርክ  እንደተቀሰቀሰ መስማቱን ተከትሎ  ወደዚያው በማቅናት  እሳቱን  ለማጥፋት  ሲረባረብ ነው  በቃጠሎ ህይወቱ ያለፈው። ወጣት ቢኒያም ወደባሌ ብሄራዊ ፓርክ ያቀናው እንደሱ እሳቱን ለማጥፋት  ከዘመቱ ከሌሎች ወጣቶች ጋር በመሰባሰብ ነበር። በስፍራው ደርሰው በጋራ ርብርብ በሚያደርጉበት ወቅት  እሳቱ ቢኒያምን ጨምሮ ሌሎቹን ወጣቶች ...

Read More »

ጄ/ል ሳሞራ የኑስ በአየር ሃይል አባላት ላይ እየዛቱ መሆናቸው ተሰማ

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- አብራሪዎች ባለፉት 6 ወራት ከድሬዳዋ አየር ሃይል ግቢ ጠፍተው ተቃዋሚዎችን መቀላቀላቸውንና መሰደዳቸውን ተከትሎ ኢታማዦር ሹሙ ሳሞራ የኑስ በቀሪዎቹ ላይ የዛቻና የማስፈራሪያ ንግግሮችን በማድረግ ላይ መሆናቸው ተሰምቷል ። የአየር ሃይል ምንጮች እንደተናገሩት፦ጀነራሉ <<ከጠፉት የአየር ሃይል አባላት ጋር ግንኙነት ነበራቸው>>ያሏቸውንና  <<ሊጠፉ ሲሉ ተያዙ የተባሉ ሌሎች የአየር ሃይል አባላትን>>  ለቀሪዎቹ አባላት ሲያሳዩ ሰንብተዋል። ኢታማዦር ሹሙ  ሰሞኑንም ...

Read More »

ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ድብደባ ተፈጸመባቸው

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- ጠበቃ ተማም አባ ቡልጉ ዛሬ ከቀትር በሁዋላ ማንነቱን በማያውቁት ሰው ድብደባ ተፈጸመባቸው። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ወደ ፍርድ ቤት እየሄዱ ሳሉ ሜክሲኮ አካባቢ ብሔራዊ አረቄ ፋብሪካ መታጠፊያ ላይ አንድ  እብድ የሚመስል ሰው  ተንደርድሮ ዐይናቸውን በቡጢ  ክፉኛ መቷቸዋል። ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች ጠበቃ ሆነው ለረዥም ጊዜ በመከራከራቸው በስርዓቱ  ሰዎች ዛቻና ማስፈራሪያ ...

Read More »

የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር -የአውሮፓ ህብረት ተወካዮችን ወቀሱ

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-  ‹‹ኢህአዴግ እያታለላችሁ ነው፡፡ እናንተም ለመታለል ዝግጁ ሆናችኋል›› ሲሉ ኢንጂነር ይልቃል ጌትነት ለአውሮፓ ህብረት መልእከት አስተላለፉ። የሰማያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር  ይህን ያሉት የአውሮፓ ህብረት ዛሬ መጋቢት 1/2007 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ጽ/ቤቱ ባደረገው ስብሰባ  ላይ ነው።  ኢትዮጵያ ውስጥ ኤምባሲ ያላቸው 20 ያህል የህብረቱ አባል አገራት  አምባሳደሮችና ተወካዮች በተገኙበት በዚህ ስብሰባ ላይ በተጋባዥ እንግድነት የተገኙት ...

Read More »

<<ችሎት ደፍራችሁዋል ተብለው ፍርድ የተላለፈባቸው እነ አብርሀ ደስታ፦<<የደፈርነው አሻንጉሊት እና  ወትሮም የተደፈረ  ችሎት ነው>>ሲሉ ተቃውሟቸውን ገለጹ።

መጋቢት ፩(አንድ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ ተመስርቶባቸው ከስምንት ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት የሰማያዊ፣ የአንድነት እና የዓረና ትግራይ ፓርቲ  አመራሮች ‹ችሎት በመድፈር ወንጀል› ጥፋተኛ በመባላቸው  የሰባት ወር እስራት ተፈረደባቸው። የልደታ ከፍተኛው ፍርድ ቤት  ዛሬ መጋቢት 1 ቀን  2007 ዓ.ም በዋለው ችሎት  በመድፈር በሰባት ወር እስራት እንዲቀጡ የወሰነባቸው አብርሀ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋና ...

Read More »

በጋምቤላ የድንበር ከተሞች ዜጎች ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እየተገደሉ ነው

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለደቡብ ሱዳን አዋሳኝ በሆኑ የጋምቤላ አካባቢዎች ኢትዮጵያውያን በየጊዜው እንደሚገደሉና የጸጥታው ሁኔታ እየተበላሸ መሆኑን በተለያዩ የመንግስትና የግል ስራዎች ላይ የተሰማሩ ዜጎች ገልጸዋል። መታሃር፣ ላሬ፣ ኢታንግ እንዲሁም ፑጊዶ በሚባሉ አካባቢዎች ማንነታቸው በውል የማይታወቁ ታጣቂዎች አብዛኛውን ጊዜ በግል ኩባንያዎች ተቀጥረው በሚሰሩ ዜጎች ላይ እርምጃ እየወሰዱ ነው። እነዚህ ታጣቂ ሃይሎች የሚወስዱትን እርምጃ ተከትሎ የፌደራል ፖሊስና ልዩ ሃይል ...

Read More »

በሃረር የቀን ሰራተኞች ታፈሱ፣ እድሜያቸው ለውትድርና ያልደረሱትም ወደ ማሰልጠኛ ካምፖች ተወሰዱ

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሃረር ከተማ ካለፈው ሁለት ሳምንት ጀምሮ እንዳዲስ በተጀመረው አፈሳ በርካታ በቀን ስራ የሚተዳዳሩ ነዋሪዎች ታፍሰው ወደ አልታወቀ ስፍራ የተወሰዱ ሲሆን፣ አንዳንድ ወገኖች ግን ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ተወስደዋል ብሎዋል።  እሁድ እለት ደግሞ  በርካታ  አዲስ ምልምል ታዳጊዎች ደግሞ ለወታደራዊ ስልጠና ወደ ብር ሸለቆ ተወስደዋል። እድሜያቸው ከ12 እስከ 13 አመት የሚደርሱ ወጣቶችም ወደ ማሰልጠኛ የተወሰዱ ሲሆን፣ ...

Read More »

ጀማሪ የሥራ ተቋራጮች ፈቃድ ለማግኘት የተጭበረበረ ማስረጃ እንደሚጠቀሙና ይህም ለሕዝብ ሀብት ብክነት ዋና መንስኤ እየሆነ እንደሚገኝ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡

የካቲት ፴(ሠላሳ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአሁኑ ወቅት በሀገሪቱ ደረጃ አንድ፣ ደረጃ ሁለት እየተባለ  እስከ አስር ደረጃ ድረስ የስራ ተቋራጭነት ፈቃድ የሚሰጥ ሲሆን ይህንን ፈቃድ ለማግኘት  እንደዶዘር፣ ግሬደር፣ እስካቭተርና ፒክ አፕ ያሉ መኪኖችን መያዝ በቅድመ ሁኔታነት የሚጠየቁ ቢሆንም፣  ሥራ ተቋራጮች እነዚህ ተሸከርካሪዎች እንዳሉዋቸው በማስመሰል ከትራንስፖርት ባለስልጣን አንዳንድ ሃላፊዎች ጋር እየተሻረኩና የጥቅም ትስስር እየፈጠሩ ሐሰተኛ ሊብሬ በማቅረብ ፈቃዱን የሚወስዱ ...

Read More »