ባለፉት 21 አመታት በአማራው ብሄረሰብ ላይ በገዥው ፓርቲ የደረሰበትን መፈናቀል፣ መገፋት መገለልና የዘር ማጽዳት እርምጃ ለመታደግና ለመታገል ያለመ ሲቪክ ድርጅት እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ተመሰረተ:: ሞረሽ ወገኔ የአማራው ድርጅት የተሰኘው ይህ ሲቪክ ተቆም ከትላንት በስቲያ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላለፉት 21 አመታት የአማራው ብሄረሰብ አባል ተዋራጅና ተሸማቃቂ ተደርጎል፣የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጥቅሞቹ ተነጥቀዋል ከምስራቅ፣ከደቡብ ምእራብ፣ከደቡብና ከመሀል ኢትዮጵያ መኖር አትችልም ተብሎ ሀብት ንብረቱ ተነጥቆ ተባሮል ...
Read More »የንግዱ ማህበረሰብ አሁንም በታክስ ክፍያ እየተማረረ ነው
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአማራ ክልል የሚገኙ ነጋዴዎች መንግስት ከገቢያቸው ጋር ያልተጣጣመ ታክስ እንዲከፍሉ በማስገደዱ ድርጅታቸውን ለመዝጋት እየተገደዱ መሆኑን ለኢሳት ገልጠዋል። በደቡብ ጎንደር ወረታ ከተማ ውስጥ የሚኖር አንድ ነጋዴ እንዳለው በግብር የተነሳ ህዝቡ እየተሰደደ ነው ብሎአል ። ስሙ እንዳይጠቀስ የፈለገ በጨርቃጨርቅ ስራ ላይ የተሰማራ ነጋዴ በበኩሉ በግብር የተነሳ ቤተሰቡን እስከመበተን መድረሱን ተናግሯል ወረታ በእህል ንግድ ላይ ...
Read More »የሙስሊም ችግር መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አዲስ የትግል ስልት መቀየሱን አስታወቀ
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ሙስሊም ማህበረሰብ ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ ተወካዮች የ ኢህአዴግ መንግስት ከ ህገመንግስት እውቅና ውጭ በሀይማኖት ውስጥ የሚያደርገውን ጣልቃ ገብነት ለማስቆም እና በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የአህባሽን አስተምሮ በግድ የሚጭንበት ፣ እንዲሁም በቅርቡ በወረዳዎች ባካሄደው ምርጫ ካድሬዎቹን በሙስሊሙ ላይ የሾመበትን ሁኔታ ለ አንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመግታት አዲስ ስልት መቀየሱን አስታውቋል። እስካሁን በተደረገው መብትን ...
Read More »በኢህአዴግ ውስጥ በተፈጠረው አለመግባባት የተነሳ አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ካቢኔያቸውን ሊመሰርቱ አልቻሉም
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አንድ ስማቸው እንዳይጠቀስ የፈለጉ የኢህአዴግ ባለስልጣን ለኢሳት እንደተናገሩት ኢህአዴግ የድርጅቱን አባላት የአመለካከት መዛባት ለማጥራት በሚል ከክልል ጀምሮ ግምገማ የጀመረ ሲሆን፣ ግምገማውን ወደ ወረዳ ለማድረስ ማቀዱም ታውቋል። በአሁኑ ጊዜ የአባላቱ አመለካከት እየተጣራ ፣ አዲሱን የጠቅላይ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት አይቀበሉም የተባሉትን ለማግለል እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው። በድርጅቶች መካከል በተነሳው አለመግባባትም አቶ ሀይለማርያም ደሳለኝ ...
Read More »በአዲስ አበባ በተካሄደ የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ አንድም ኢትዮጵያዊ አለመሳተፉ ተዘገበ
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ሪፖርተር እንደዘገበው ፤በአዲስኢትዮጵያውያን ያልተሳተፉበትን የኢንቨስትመንትኮንፈረንስ ያዘጋጁት አበባ የተካሄደውንና ፤ተቀማጭነቱ በስፔን የሆነው ሲንጉላ ሪስ አድቫይዘርስ የተባለ ኩባንያ – “ዋይ.ኤች.ኤም ኮንሰልቲንግ” ከተባለ አማካሪ ድርጅት ጋር በመተባበር ነው። ባለፈው ሳምንት ለሦስት ቀናት በሒልተን ሆቴል በተካሄደው የኢንቨስትመንት ኮንፈረንስ አንድም የኢትዮጵያ ኩባንያ አልተሳተፈም። በጣም አስገራሚው ነገር ፤ስብሰባው የተዘጋጀው ኢትዮጵያን ጨምሮ ለኢንቨስትመንት ፕሮጀክቶቻቸው ገንዘብ የሚፈልጉ የአፍሪካ ኩባንያዎችን ከአውሮፓና ከመካከለኛው ምሥራቅ ከመጡ ...
Read More »የእስራዔል መንግስት 237 “ፈላሻ ሙራዎችን” ከኢትዮጵያ መውሰዱን አስታወቀ
ጥቅምት ፳፩ (ሀያ አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:- “የእርግብ ክንፍ” የሚል ስያሜ በተሰጠው በዚሁ ዘመቻ ከተጓጓዙት ፈላሻ ሙራዎች መካከል ግማሽ ያህሉ ሕፃናት ሲሆኑ፣ እስከ ሕዳር 2006 ዓ.ም ድረስ ተጨማሪ 2000 ቤተ እስራኤላውያንን ከጎንደር ለመውሰድ እቅድ እንደያዘ የ የእስራኤል መንግስት ይፋ አድርጓል።፣ ለነኚሁ ተጓዦቹ ማረፊያ ይሆን ዘንድም፣ አስፈላጊው ነገር የተሟላለት 16 የመጠለያ ጣቢያ ነጂቭ በረሃ ላይ መዘጋጀቱ ታውቋል። በእስራኤል ከሚኖሩት ...
Read More »በማረቃ ወረዳ የየኔሰው ገብሬ ጓደኛ የሆነው ወጣት ራሱን በአደባባይ ሰቀለ
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ በኢኮኖሚክስ የትምህርት ክፍል የሜዳሊያ ተሸላሚ የነበረው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም ራሱን በአደባባይ ለመስቀል የተገደደው በአካባቢው ያለውን የመልካም አስተዳዳርና የፍትህ እጦት በመቃወም መሆኑን ጓደኞቹና ቤተሰቦቹ ለኢሳት ገልጠዋል። በደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ክልል ፣ በዳውሮ ዞን ፣በማረቃ ወረዳ ፣ በዋካ ቀበሌ ነዋሪ የሆነው ወጣት ግርማ ወ/ማርያም፣ በ1980 ዓም ነበር የተወለደው ። የ10ኛ ክፍል ትምህርቱን 3 ...
Read More »በኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር ሀዲድ ላይ ከፍተኛ ሙስና የፈጸመው ኩባንያ በተመሳሳይ ወንጀልም ይፈለጋል ተባለ
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጉዳዩን በቅርብ የሚያውቁ የውጭ አገር ዜጎች “ኢሳት የህወሀቱ መስፍን ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በሀዲድ አምራችነት የሚሳተፍበት የኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር መንገድ ግንባታ በከፍተኛ ሙስና ስራውን ማጠናቀቅ አልቻለም” በሚል ርእስ በኢሳት የወጣውን ዜና ከተመለከቱ በሁዋላ በዜናው ላይ ማሻሻያ ያሉዋቸውን ነጥቦች በማከልና ኩባንያው በመላው አለም ስለሚፈጽመው ሙስና የሚያትት በጣሊያንኛ ቋንቋ የተጻፈ መልእክት ልከዋል። ከአውሮፓ ህብረት በተገኘው 41 ሚሊዮን ዩሮ ...
Read More »ኢትዮጵያ ለግብጽ አንድ ሚሊዮን ስኩዌር ሜትር መሬት ልትሰጥ ነው
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-እየተገነባ ባለው የህዳሴው ግድብ ሳቢያ ግብጽ ችግር ልትፈጥርብን ትችላለች የሚል ስጋት በተደጋጋሚ በኢትዮጵያ መንግስት ደጋፊ ሚዲያዎች ሲስተጋቡ ቢሰሙም፤ የግብጽ ጠቅላይ ሚኒስትር ግን በተቃራኒው በኢትዮጵያና በግብጽ መካከል ያለው የልማት ግንኙነት እየተሻሻለ መምጣቱን ነው ይፋ ያደረጉት። የግብጹ ጠቅላይ ሚኒስትር ሀሺም ካንዲ በቅርቡ በአልጀሪያ ባደረጉት የሁለት ቀናት ጉብኝት ላይ ፤አገራቸው ፤ በአልጀሪያና በኢትዮጵያ ሁለት የኢንዱስትሪ ዞኖችን ...
Read More »የሚኒሰትር ጁኔዲን ሳዶ ባለቤት ፍርድ ቤት ቀረቡ
ጥቅምት ፳ (ሀያ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፌደራል ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት 4ኛ ወንጀል ችሎት ትናንት 4፡30 ላይ ጀምሮ ማእከላዊ ፖሊስ ጣቢያ በእስር ላይ የሚገኙትን የኢትዮጵያ ሙስሊም ችግሮች መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ እና የሀይማኖት መብታችን ይከበርልን ባሉ ሼሆችና ኡላማዎች ላይ የፌደራሉ አቃቢ ህግ ክስ ከመሰረተባቸው ሰዎች መካከል አንዷ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒሰትሩ ባለቤት የሆኑት 28ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ ሀቢባ ሙሀመድ መሆናቸው ...
Read More »