ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ታዋቂው የኢኮኖሚክ ባለሙያ የሆኑት ፕ/ር በፈቃዱ ደግፌ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ መንግስት የህዝብን ብሶት አልሰማ በማለቱ አንድ ቀን ያልጠበቀው አደገኛ ሁኔታ ሊፈጠርበት እንደሚችል አስጠንቅቀዋል። ” ህዝቡ የሚሄድበት ቦታ አጥቷል፣ ብሶታል” ያሉት ፕ/ር በፈቃዱ ከአረብ አብዮት የምንማረው ህዝብ መሪ ሳያስፈልገው በብሶቱ ብቻ ሆ ብሎ ሊነሳ የሚችል መሆኑን ነው ሲሉ ገልጸዋል። በኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ጉዳዮች ...
Read More »የለገጣፎ/ለገዳዲ ነዋሪዎች አዲሱን ከንቲባ አንቀበልም አሉ
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከመሬት ዝርፊያ ጋር በተያያዘ የከተማው ነዋሪዎች ያሰሙትን ከፍተኛ ተቃውሞ ተከትሎ በቅርቡ ከንቲባውን አቶ መገርሳ ገለታን ጨምሮ 5 የካቢኔ አባላትን ከስልጣን ያወረደው መንግስት፣ ከአካባቢው ህዝብ ያልተመረጠ አዲስ ከንቲባ በመሾም ለህዝቡ ለማስተዋወቅ የጠራው ስብስባ በተቃውሞ እንዲበተን ተደርጓል። ህዳር 21 ቀን 2005 ዓም ከፍተኛ የኦህዴድ ባለስልጣን የሆኑት አቶ ቀነአ ኩማ የለገጣፎ ለገዳዲን ህዝብ በመሰብሰብ አዲስ ...
Read More »ነጋዴዎች አዲስ ራእይ መጽሄትን እንዲገዙ እየተገደዱ ነው
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ነጋዴዎቹ ለኢሳት እንደተናገሩት ፣ አንድ ነጋዴ በ100 ብር ቢያንስ ሁለት የአዲስ ራእይ መጽሄትን መግዛት ግድ ይለዋል። ይህን መጽሄት ለመግዛት ፈቃደኛ ካልሆ ጸረ ልማትና ጸረ ህገመንግስት ተደርጎ ይቆጠራል። መጽሀፉን የሚሸጡት የኢህአዴግ አባላት ሲሆኑ ፣ አንድ አባል በነፍስ ወከፍ እስከ 50 አዲስ ራእይ መጽሄቶችን መሸጥ ይጠበቅበታል። ኢሳት ከመንግስት በኩል ማረጋጋጥ ባይቻልም ስለመለስ ዜናዊ ማንነት ...
Read More »በጅማ ዩኒቨርስቲ በተነሳው ተቃውሞ የታሰሩት ተማሪዎች ቁጥር ከ100 በላይ መድረሱን የፖሊስ ምንጮች ገለጹ
ህዳር ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ፖሊሶች ለኢሳት እንደገለጡት በእስር ላይ የሚገኙት ተማሪዎች ቁጥር 115 ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል የተወሰኑት ትናንት ተለቀዋል። 2 ተማሪዎች ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ምንጮች ጠቁመዋል። መጠነኛ ጉዳት የደረሰባቸው ተማሪዎች በመቶዎች የሚቆጠሩ መሆኑን የገለጡት ፖሊሶች፣ ትምህርት አንጀምርም ያሉትን ተማሪዎች ከሙስሊም እንቅስቃሴና ከተቃዋሚዎች ጋር በማያያዝ ለመክሰስ መታቀዱን ገልጸዋል። ተማሪዎች ያነሱት ጥያቄ ...
Read More »መድረክ በቅርቡ የተደረገውን የ3ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል አወገዘ
ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራሊስት አንድነት መድረክ በቅርቡ የተደረገውን የ3ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል አወገዘ። መድረክ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ ሹመት የህገመንግስቱን ሁለት አንቀጸች የጣሰ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡ 34ቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህገመንግስቱ ተጥሶ 3 ም ክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች መሾማቸውን በማውገዝ ጉዳዩን ወደ ...
Read More »ሰማያዊ ፓርቲ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት መፍረስ ተቃወመ
ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ፓርቲው ባወጣው መግለጫ ማንኛውም ልማት ወጪን ቆጣቢ ሆኖ መሰራት እንዳለበት የሚታመን ቢሆንም በዋጋ ሊተመኑ የማኢችሉ ቅርሶችን በማጥፋት ግን ወጪን ለመቀነስ ማሰብ የእብደት አስተሳሰብ ነው ብሎአል። የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ይልቃል ጌታሁን ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ ኢህአዴግ ከፍ ብሎ ለመታየት ባለው ፍላጎት የተነሳ ከዚህ በፊት የተሰሩትን ስራዎች ሁሉ ለማሳነስ እንደሚሞክር ገልጠው፣ የአቡነ ጴጥሮስን ሀውልት ...
Read More »በጥንቁር አንበሳ የካንሰር ተጠቂው ቁጥር ከሆስፒታሉ አቅም በላይ ሆኗል ተባለ
ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በካንሰር በሽታ ተጠቅተው ወደ ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የሄዱ ህሙማን ለኢሳት እንደገለጹት ሆስፒታሉ ለካንሰር ህመምተኞች ያዘጋጀው አልጋ እና ህክምና የሚሰጡት ባለሙያዎች ቁጥር ከበሽተኛው ቁጥር ጋር ሊጣጣም ባለማቻሉ በሽተኞች ተገቢውን ህክምና ለማግኘት አልቻሉም። በጥቁር አንበሳ ለካንሰር በሽተኞች ተብሎ የተዘጋጀው አልጋ ቁጥር አነስተኛ ሲሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በየአመቱ ከ200 ሺ በላይ አዳዲስ የካንሰር ተጠቂዎች እንዳሉ መረጃዎች ...
Read More »የቻይና ጋዜጠኞች ማህበር የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለመደገፍና በትብብር ለመስራት ይፈልጋል ተባለ
ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-አቶ በረከት ስምዖን በሚስተር ዡ ሾሼን የተመራ የጋዜጠኞች ልዑካን ቡድንን አነጋግረዋል። የመላው ቻይና ጋዜጠኞች ማህበር ዋና ፀሐፊ ሚስተር ዝሁ ሾቼን የኢትዮጵያ ጋዜጠኞችን አቅም ለመደገፍና የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት ፍላጎት እንዳለው ገልጸዋል። የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ኃላፊ ሚኒስትር አቶ በረከት ስምዖን ቻይና የረጅም ዓመታት የዳበረ ልምድና ተሞክሮ ያላት አገር መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያ ከቻይና ...
Read More »ከፍተኛ ሙስና ፈጽመዋል የተባሉት ግለሰብ የኦሮምያ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው ተሾሙ
ህዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኦሮሚያ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ጉባኤውን ሲያጠናቅቅ የ77 ዳኞችን ሹመት አጽድቋል።የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት ሆነው የተሾሙት አቶ ፍቅሩ አያና ከምክር ቤት አባላቱ ከፍተኛ የሆነ ተቃውሞ ቢቀርብባቸውም፣ ከፍተኛ አመራሮች ስለፈለጉዋቸው ብቻ እንዲሾሙ መደረጉን የኦህዴድ ምንጮች ገልጸዋል። የምክር ቤት አባላት በአቶ ፍቅሩ ላይ ካቀረቡዋቸው የመቃወሚያ ሀሳቦች መካከል ግለሰቡ በሙስና የተዘፈቁ ናቸው፣ በዞናቸው ዳኛ ...
Read More »የጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ክስ እንደገና ተቀሰቀሰ
ህዳር ፳፪ (ሃያ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የፍትህ ጋዜጣ ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ከዚህ ቀደም በፌዴራል ዐቃቤ- ሕግ ቀርቦበት የነበረው ክስ እንደገነ ተቀሰቀሰ፤ ትላንት ሃሙስ ህዳር 20 ቀን 2005 ዓ.ም ከቀትር በኋላ ወደ ጋዜጣው ቢሮ የፍርድ ቤት መጥሪያ ይዘው የመጡት የፖሊስ አባላት ጋዜጠኛ ተመስገን ከአዲስ አበባ ውጪ መሆኑ ተነግሯቸው ተመልሰዋል ። ዓርብ ህዳር 21 ቀን 2005 ዓ.ም ከሰሃት ...
Read More »