መድረክ በቅርቡ የተደረገውን የ3ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል አወገዘ

ህዳር ፳፬ (ሃያ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ፌደራሊስት አንድነት መድረክ በቅርቡ የተደረገውን  የ3ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሹመት ህገመንግስቱን የጣሰ ነው ሲል አወገዘ።

መድረክ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ ሹመት የህገመንግስቱን ሁለት አንቀጸች የጣሰ ነው። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከምርጫ ቦርድ ጋር ውዝግብ ውስጥ የገቡ 34ቱ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ህገመንግስቱ ተጥሶ 3 ም ክትል ጠቅላይ ሚኒስትሮች መሾማቸውን በማውገዝ ጉዳዩን ወደ ፍርድቤት ለመውሰድ የህግ ባለሙያዎችን እያማከሩ መሆኑን ገለጸዋል።