በደቡብ አፍሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከዋሊያዎች ጎን እስከመጨረሻው እንደሚቆሙ ገለጹ

ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ያነጋገራቸው ደጋፊዎች እንዳሉትምንም እንኳ ብሄራዊ ቡድኑ ከቡርኪና ፋሶ ጋር በተጫወተበት እለት ያገኘው ውጤት  አሳዛኝ ቢሆንም፣ በቀጣዩ ጨዋታ የናይጀሪያን ቡድን በማሸነፍ ለቀጣዩ ዙር ለማለፍ ድጋፋቸውን አጠንከረው እንደሚሰጡ ገልጸዋል። በደቡብ አፍሪካ የሚኖረው ደጀኑ በቀለ ድሉ የኢትዮጵያ ህዝብ እንደሚሆን ሙሉ እምነት እንዳለው ገልጿል ከቡርኪና ፋሶ ከነበረው ጨዋታ በፊት ኢትዮጵያውያን ኮከብ ካለው ሰንደቃላማዎች ውጭ ሌሎችን ...

Read More »

የኢሳት ቀን በሳንድሽን ኖርዌይ ካምፕ ውስጥ ተከበረ

ጥር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በስደተኛ ካምፕ ውስጥ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው ተነሳሽነት  ስለ ኢሳት አላማ ለ ኖርዌጅያን ማህበረሰብ ፣ በ ሳንድሽን አካባቢ ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና የኢትዮጵያውያን ወዳጆች በሙሉ ለማሳውቅ እና ኢሳትንም እንዲደግፉ ለማድረግ የኢሳት ቀን በሚል ያዘጋጁት በአል መከበሩን ገልጸዋል። በእለቱም  በሳንድሽን  ለሚኖሩ ኖርዊጅያን የተለያዩ የፖለቲካ ተወካዮች ፣ የስደተኞች አስተማሪዎች በሙሉ ስለ ኢሳት የሚገለጽ በራሪ ወረቀት በማዘጋጀት ...

Read More »

ኢሳት ወደ ኢትዮጵያ የሚያስተላልፈውን ስርጭት በተሻለ ሳተላይት ለማስተላለፍ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ

ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የኢሳት አስተዳደር እንደገለጸው የአሞስ የሳተላይት ስርጭት ለጊዜው በቴክንክ ችግር ምክንያት ቢቋረጥም፣  ቦርዱ ባወጣው ስታራቲጂካዊ እቅድ መስረት ኢሳት ስርጭቱን በአስተማማኝና በዘላቂ መንገድ ማስተላለፍ ይቻል ዘንድ ከልዩ ልዩ የሳተላይት ኩባንያዎች ጋር ተስማምቶ አገግሎቱን  ለኢትዮጵያ ህዝብ በስፋትና በጥራት  ለማድረስ እየሰራ ነው ብሎአል። የኢሳት ሬዲዮናችን በአጭር ሞገድ በየቀኑ  በኢትዮጵያ አቆጣጠር ከምሽቱ 2 ሰዓት እስከ 3 ሰዓት ...

Read More »

በብዙ መቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ ዋሉ

ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በአዲስ አበባ በአንዋር መስጊድ በተካሄደውና በብዙ መቶሺዎች የሚቆጠሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን በአንዋር መስጊድ እና ከመስጊዱ ውጭ ያሉ መንገዶችን ሞልተው የተለያዩ መፈክሮችን አሰምተዋል። “በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ላይ የሚደረግ ጭቆና ይብቃ፣ በቃል ኪዳናችን እንጽና፣ ውሸት ሰለቸን፣ ኮሚቴዎች ይፈቱ፣ የሀሰት ምስክሮች አይቅረቡ ” የሚሉ መፈክሮች በብዛት መታየታቸውን የዘገበው ሪፖርተራችን፣ አንዳንድ አማንያንም “መንግስት የለም” በማለት ሲናገሩ ተሰምተዋል። አብዛኛው ...

Read More »

ገቢዎች እና የከፍተኛ ግብር ከፋይ ኩባንያ ባለአክስዮኖች እንደተፋጠጡ ነው

ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን  በንግድ ማኀበራት ባልተከፋፈለ ትርፍ ላይ የ10 በመቶ የጣለው የግብር ውሳኔ ከፍተኛ ግብር ከፋዮችን ኩባንያዎችና ባለአክስዮኖችን አስቆጥቷል፡፡ ባለስልጣኑ በተሻሻለው የገቢ አዋጅ ቁጥር 286/94 በአንቀጽ 4 ላይ የአክስዮን ማኀበራትና ኀላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኀበር ካከፋፈሉት የአክስዮን ድርሻ ትርፍ ገቢ የሚያገኝ ማንኛውም ሰው ባገኘው ገቢ ላይ የ10 በመቶ ግብር እንደሚከፍል ይደነግጋል፡፡ ባለስልጣኑ ከዚህ ...

Read More »

አንዲት ኢትዮጵያዊት የቤት ሰራተኛ ራሱዋን መስቀሉዋ ተዘገበ

ጥር 17 (አስራ ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-በኩዌት በቤት ሰራተኛነት ተቀጥራ ትሰራ የነበረች ኢትዮጵያዊት ራሱን በገመድ በስቀል አረብ ታይምስ በፎቶግራፍ አስደግፎ ያወጣው ዘገባ ያመለክታል። የጸጥታ ሀይሎች በአካባቢው ሲደርሱ ስሟ  ያልተጠቀሰው ኢትዮጵያዊት ራሱዋን አንቃ መግደሉዋ ለመመልከት መቻላቸውን በዘገባው ተመልክቷል። የልጂቱ አስከሬን ለምርመራ መወሰዱ ቢታወቅም፣ ሰራተኛዋ ራሱዋን ማጥፋቱዋንና አለማጥፋቱን የኩየት የደህነነት ሰራተኞች ከገለጹት ውጭ በሌላ ወገን የተረጋገጠ ነገር የለም። የኢትዮጵያ ኢምባሲም ...

Read More »

ለመጪው የአካባቢ ምርጫ የተመዘገበው ህዝብ ከ30 በመቶ ከፍ ሊል አልቻለም

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ኢሳት ከምርጫ ቦርድ የውስጥ ምንጮች ባገኘው መረጃ መሰረት በምርጫው ለመሳተፍ የተመዘገበው ሰው ቁጥር ድርጅቱ በይፋ ከተገለጠው በእጅጉ ያነሰ ነው። የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ከ89 በመቶ በላይ መራጭ ህዝብ እንደተመዘገ በይፋ ቢያስታውቅም፣ እስካሁን በትክክል የተመዘገበው ግን 33 በመቶ ብቻ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። በህዝቡ የምርጫ ፍላጎት ማጣት ግራ የተጋባው ኢህአዴግ በተለያዩ ወረዳዎች የሚገኙ አመራሮችን ” ...

Read More »

በኢትዮጵያ የሚታየው ወታደራዊ እንቅስቃሴ እየጨመረ ነው

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ከአቶ መለስ ዜናዊ ሞት በሁዋላ ከፍተኛ የተባለ ወታደራዊ እንቅስቃሴ በመላ አገሪቱ እየታየ መሆኑን ዘጋቢያችን መረጃዎችን ዋቢ በማድረግ ገለጸ ከሁለት ሳምንት በፊት ከ35 በላይ ታንኮችን የጫኑ ከባድ ተሽከርካሪዎች ወደ ምስራቅ የአገሪቱ ክፍል የተጓዙ ሲሆን፣ ከሁለት ቀናት በፊት ደግሞ ከ30 ያላነሱ ታንኮች ወደ ሰሜን ተንቀሳቅሰዋል። ገዢው ፓርቲ መሳሪያዎችን ለምን እንደሚያንቀሳቅስ በትክክል ለማወቅ ባይቻልም፣ አንዳንድ ...

Read More »

የዋልድባ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለክልሉ መንግሥት አቀረቡ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-የዋልድባ አብረንታንት ገዳም ቤተ-ሚናስ ማኅበረ መነኮሳት አቤቱታቸውን ለአማራ  ክልላዊ መንግሥት ርዕሰ መስተዳድር ጽ/ቤት እና ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን አቀረቡ።   የሚደርስባቸውን የሰብዓዊ መብት ረገጣ በደብዳቤ የዘረዘሩት መነኮሳቱ ፤መንግሥት በሰላማውያን መነኮሳት ላይ የሚደርሰውን እንግልት እንዲያስቆም ጠይቀዋል። የታሰሩ፣ የተንገላቱ፣ ሰብዓዊ መብት ጥሰት የደረሰባቸውን መነኮሳትንም ዝርዝር አቅርበዋል።   <<መብታችን እየተጣሰ ስለሆነ የእርምት እርምጃ እንዲወሰድልን ስለመጠየቅ>>በሚል ርዕስ ...

Read More »

የህሊና እስረኞችን ለማነጋገር ወደ ቃሊቲ የተጓዘው የሽማግሌዎች ቡድን በተቃውሞ ተመለሰ

ጥር ፲፮ (አስራ ስድስት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና:-ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በማስታወሻው ላይ እንዳሰፈረው ወደ ቃሊቲ በማምራት ርዕዮት አለሙን ያነጋገሩት ፓስተር ዳንኤል ‹‹የእስከዛሬው ተግባርህ የሚያስረዳው የኢህአዴግ ጉዳይ አስፈጻሚክንፍመሆንህን ነው፡፡ ስለዚህም በምንም አይነት ጉዳይ ላይ ካንተ ጋር ለመነጋገር ፈቃደኛ አይደለሁም›› የሚልያልጠበቁትን መልስ በማግኘታቸው የይቅርታ አጀንዳውን ሳያነሱ ተመልሰዋል፡፡ የሙስሊሙማህበረሰብ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴዎች በበኩላቸው ለፓስተር ዳንኤል እና ለፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ  ፦‹‹ያቀረባችሁትን የይቅርታ መጠየቅ ሀሳብ  በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነንም አንልም፣ አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› የሚል መልስ ሰጥተዋቸዋል፡፡ ከርዕዮትና ከሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊዎች ያልጠበቁትን መልስ ያጘኙት  የሽማግሌዎቹ ልዑካን፤ እስክንድር ነጋን ሳያነጋግሩተመልሰዋል፡፡ ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ በግል የፌስ ቡክ ገጹ ላይ እንዳሰፈረው ሀሙስ ጥር 2 ቀን 2005 ዓ.ም በፕሮፌሰር ኤፍሬም ይሳቅ ይመሩ ከነበሩት ሽማግሌዎችውስጥ የተዘጋጀ ሶስት ሰዎች ያሉት አንድ ቡድን በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ተገኝቶ ነበር፡፡ ከቡድኑ አባላትመካከል ፓስተር ዳንኤል እና ፕሮፌሰር አህመድ ዘካርያስ ለታሳሪዎቹ  ‹‹ጉዳያችሁበፍርድ ቤት እየታየ ነው፤ ስለዚህም ክሱ አሁን ባለበት ደረጃ ሊቋረጥ አይችልም፡፡ እናም ክርክራችሁን አቋርጡና ጥፋተኛ ነን በሉ፣ ከዛም ፍርድ ቤቱ ከፈረደባችሁበኋላ ‹ይቅርታ› ጠይቃችሁ እናስፈታችኋለን›› የሚል  መደራደሪያ አቅርበው ነበር፡፡ ሆኖም የሙስሊሙ መሪዎች ‹‹ይህንን በጭራሽ አንቀበለውም፣ ጥፋተኛ ነኝም አንልም፣አላሁ አእለም! ይቅርታ አንጠይቅም›› ሲሉ በድፍረትና በቁርጠኝነት መልሰውላቸው ወደ እስር ክፍላቸው መመለሳቸውንና በተጠቀሰው ዕለት እስክንድር ነጋ ዘለው   አንዱአለምአራጌን ነጥለው ማናገራቸውን ታውቋል። ተመስገንአክሎም  የሽማግሌ ቡድኑ ለሙስሊሙ መሪዎች ‹‹የመጣነው አንዱአለምን ፈልገን ነው፣እናንተን እግረ መንገዳችንን ሰላም እንበላችሁ ብለን ነው›› ሲሏቸው፣ ለአንዱአለምም በተመሳሳይ  <የመጣነው ...

Read More »