የኬንያ ልዩ ተጠባባቂ ሀይል ከኢትዮጵያ ሰርገው በገቡ ታጣቂ ሀይሎች ላይ ዛሬ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ይፋ አደረገ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡ ታጣቂ ሀይሎች አራት የኬንያ ተጠባባቂ ፓሊሶችንና ስድስት አሳ አጥማጆችን በመግደላቸው በሁለቱ ድንበር አካባቢ ከፍተኛ ውጥረት ነግሷል፡፡ የኬንያና የኢትዮጵያ የፀጥታ እና ደህንነት ባለስልጣናት ጉዳዩን አስመልክቶ በመወያየት ላይ ሲሆኑ ጉዳዩ ያሳሰበው የኬንያ ተጠባባቂ ልዩ ሀይል ዛሬ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ በገቡት ታጣቂ ሀይሎ ላይ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ተናግረዋል፡፡ ከኢትዮጵያ ወደ ኬንያ የገቡት ...

Read More »

አራት የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ሀላፊዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተሰማ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አራቱ የደቡብ ክልል ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ከፍተኛ ሀላፊዎች በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኙ የመንግስት መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ የክልሉ ውሃ ሀብት ልማት ቢሮ ምክትል ሀላፊው አቶ ውብሸት ፀጋዬ፣ የግዢና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ሀላፊው አቶ ይገረሙ ፋሲቆ፣ የክፍያዎች ሀላፊው አቶ አቦሰጥ መብራቱ፣ መሐንዲሱ አቶ ሞገስ ዩሀንስ እና ኮንትራክተር የነበሩት አቶ ተክለወልድ ማሞ በቁጥጥር ስር ...

Read More »

አንድ የቻይና ኩባንያ ሰራተኞችን እያሰቃየ መገኙትን የሰብአዊ መብት ጉባኤ አስታወቀ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቀድሞ የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ፣ አሁን ሰብአዊ መብቶች ጉባኤ እየተባለ የሚጠራው ታዋቂው ድርጅት ባወጣው 127ኛ ልዩ መግለጫ በኦሮሚያ ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት አርሲ ዞን በመንገድ ሥራ ላይ በተሰማራው የጃይናው CGCOC (ሲጂሲኦሲ) ዲራ ማኛ መቻራ መንገድ ሥራ ፕሮጀክት ውስጥ የሚሰሩ ሰራተኞች ማህበር የሆነው የዳንዲ ደራርቱ አርሲ ሰራተኛ ማህበር አመራርና አባላት በአሰሪዎቻቸው ከፍተኛ የሰብአዊ መብቶች ጥሰት እየተፈጸመባቸው ...

Read More »

የአቶ መለስ መሞት ወደ ውጭ በወጣው 11 ቢሊዮን ዶላር ምርመራ ላይ ተጽኖ መፍጠሩ ተገለጸ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከኢትዩጵያ በህገ ወጥ የተሻገረውን 11 ቢሊዩን ዶላር ለማስመለስ እና የባለስልጣናትን የሀብት መጠን ይፋ ለማድረግ የተያዘው ቀጠሮ በመለስ ሞት ምክንያት ዳር ሳይደርስ መቅረቱን የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ኪሚሺን ኪሚሺነር አቶ ዓሊ ሱሊማን ተናገሩ፡፡ አቶ አሊ በጠቅላይ ሚኒስተር መልስ ዜናዊ የስራ ትጋት እና አርቆ  አሳቢነት ምስክርነት ለመስጠት በ ኢቲቪ የፖሊስ ፕሮግራም ላይ በተጠየቁበት ስዓት ነው ...

Read More »

መንግስት በመርካቶ አካባቢ በቢሊዮን የሚቆጠር ታክስ መሰብሰብ አልቻለም

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስትን ከአካባቢው ማግኘት የነበረበትን ከ 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር በላይ የገቢ ግብር መሰብሰብ እንዳልቻለ ከገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡ የመንግስትን የገቢ ግብር መሰበሰብ ያልተቻለው የአዲስ አበባና የአገሪቱ የንግድ ማዕከል በሆነው በመርካቶ አካባቢ እስከ ቅርብ ጊዜ ሲከናወን የቆየው የግብይት ስርዓት በአብዛኛው ሕገወጥ በመሆኑ ነው ብሏል። ይህንን ችግርም ለመቅረፍ ባለሰልጣኑ የመርካቶ አካባቢን የታክስ ሕግ ተገዢነት ...

Read More »

የፌዴራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለአንድ ወር ለዕረፍት ተዘጋ

ነሃሴ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ ከነሃሴ 1/2005 እስከ መስከረም 25/2005 ዓ.ም ድረስ በዳኞች እረፍት ቀን ምክንያት ዝግ የሚሆን ሲሆን በነዚህ የእረፍት ጊዜያት በአዲስ አበባ ካሉት አስር ምድብ ችሎቶች አምስት ያህሉ በተረኝነት የሚሰሩ ሲሆን በድሬዳዋ የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በተጠቀሰው ጊዜም መደበኛ ስራውን የሚቀጥል መሆኑን አስታውቆአል፡፡ በዚህም የልደታ እና የኮልፌ ቀራንዮ ...

Read More »

33 የፖለቲካ ድርጅቶች በሙስሊሙ ማህበረሰብ ላይ የተወሰደውን እርምጃ አወገዙ

  ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የ33 ፓርቲዎች ትብብር ለኢሳት በላከው መግለጫ እንዳመለከተው መንግስት እየተከተለ ያለው የሀይል እርምጃ በዜጎች ህገመንግስታዊ ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብት ላይ የተፈጸመ ህገወጥ አምባገነናዊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ድርጊቱን ሊቃወምና ሊያወግዝ ይገባዋል። በአገር ቤትና በውጪ ያሉ የመገናኛ ብዙኃን፣ የነጻው ፕሬስ አባላት እና ማኅበራዊ ድረ-ገጾች በህዝበ ሙስሊሙና ክርስቲያኑ መካከል ያለመተማመን ለመፍጠር ከሚሰራጨው አፍራሽ ፕሮፖጋንዳ ሰለባነት የመታደግና የዘመናት ...

Read More »

ኢትዮጵያ ከወጪ ምርት ያገኘችው ገቢ ከሌሎች አገራት ጋር ሲነጻጸር በጣም በአነስተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ ተገለጸ።

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አሜሪካ በሰጠችው የአጎዋ የገበያ ዕድል ቀነ ቀጠሮ ማራዘም ላይ በሰፊው ሲመክር የነበረው 12ኛው የአጎዋ ጉባዔ አፍሪካ ዕድሉ እንዲራዘም መፈለጓን የአሜሪካ የህግ አውጭ ምክርቤት ተወካዮች ለምክር ቤቱ እንዲያሳውቁላቸው በመጠየቅ ተጠናቋል፡፡ በ12ኛው የአጎዋ ፎረም የንግድ ሚኒስትሩ አቶ ከበደ ጫኔ  ኢትዮጵያ ባለፉት 12 ዓመታት ወደ አሜሪካ የላከችው ምርት በየዓመቱ በአማካይ 80 በመቶ ጭማሪ ያሳዬ ቢሆንም፤ ከወጪ ምርቱ ...

Read More »

ሁለት ተቀጣጣይ ባእድ እቃ የያዙ ሲሊንደሮች በቦሌ አውሮፓላን ማረፊያ መገኘታቸውን መንግስት ገለጸ

ነሃሴ ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌዴራል ፖሊስ የጋራ የፀረ ሽብር ግብረ ሃይል እንዳስታወቀው፣ ሁለቱ ሲሊንደሮች የተገኙት በጽዳት ሰራተኞች ጥቆማ ነው። መንግስት ባእድ ነገሩን ማን እንዳስቀመጠው፣ በባእድ ነገሩ ውስጥ ምን እንዳለ ያስታወቀው ነገር የለም።

Read More »

12 የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ዋሉ

ነሃሴ ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢድ አልፈጥርን በዓል ለማክበር ባለፈው ሳምንት ወደ ኢትዮጵያ ከተጓዙ በርካታ የእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል አስራ ሁለት የውጭ ሀገር ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተካሄደባቸው እንደሚገኙ ቤተሰቦቻቸው ለኢሳት አስታወቁ፡፡ አራት የአሜሪካ፣ ሁለት የሲዊዲን፣ አንድ የአውስትራሊያና አምስት የተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት ዜግነት ያላቸው ኢትዮጵያውያኑ ከትላንትናው እለት ጀምሮ በማዕከላዊ ማረሚያ ቤት እንደሚገኙ ቤተሰቦች ተናግረዋል፡፡ በቁጥጥር ስር ...

Read More »