መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ጎንደር ዞን ደልጊ አካባቢ ከግጦሽ ሳር ጋር በተገናኘ በተነሳ ግጭት የአካባቢው ኗሪዎች በወሰዱት የመከላከል እርምጃ የፖሊስ አዛዡ ህይወት አልፏል፡፡ የፖሊስ አዛዡ ነዋሪዎችን ” መሬት የመንግስት በመሆኑ በተከለከለ ቦታ ላይ ከብቶችን ማሰማራት እንደማይችሉ መናገሩን ተከትሎ ነዋሪዎቹ ” መሬት የኛ መሆኑን ነው የምናውቀው፣ መሬት የህዝብ እንጅ የመንግስት አለመሆኑን ነው የምናውቀው” የሚል መልስ በመስጠታቸው ጉዳዩ ...
Read More »አቶ ሬድዋን ኢትዮጵያና ቻይና በሚዲያ ዙሪያ በቅርበት እንዲሰሩ ጠየቁ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አዲሱ የኮምኒኬሽን ጽህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ሬድዋን ሁሴን ከቻይና ከህዝብ የፖለቲካ ምክክር መድረክ ምክትል ሊቀመንበር ጋር ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያና ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በተመለከተ ተቀራርበው መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል። ሁለቱም ልማታዊ መንግስታት በመሆናቸው በመገናኛ ብዙሀን ረገድ የሚሰሩት ብዙ ስራዎች አሉዋቸው ያሉት አቶ ሬዲዋን፣ የቻይናን ብሄራዊ ቴሌቪዥንና የዢኖዋን እንቅስቃሴ አድንቀዋል። ቻይና የመገናኛ ብዙሀንን በማፈን ከሚታወቁት አገራት ...
Read More »አሜሪካ የዲቪ ሎተሪ ከ5 ቀናት በሁዋላ እንደሚጀመር አስታወቀች
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኢምባሲ ባወጣው መግለጫ ዲቪ 2015 በፈረንጆች አቆጣጠር ኦክቶበር 1 ተጀምሮ ኖቬንበር 2 ይጠናቀቃል ብሎአል።
Read More »የቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል በርካታ ወረዳዎች በጨለማ እንደተዋጡ 3 ወራትን አስቆጠሩ
መስከረም ፲፮(አስራ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመተከል ዞን በሚገኙ ከተሞች እንዲሁም በአዊ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች ካለፉት 3 ወራት ጀምሮ መብራት እንደተቋረጠባቸው ለዘጋቢያችን ገልጸዋል። በፓዊ የኤሊክትሪክ ሐይል መቆጣጠሪያ እና ማከፋፋያ ዲስትሪክት ስር የሚገኙት እና የቢኒሻንጉል ጉምዝ ክልል መተከል ዞን ወረዳዎች፤ወንበራ ፤ ጉባ ፤ድባጢ ፤ ግልገል በለስ ፤ፓዊ ፤ ዳንጉር ፤ ማንኩሺ ፤ማንዱራ ፤ ማንቡክ፤ ቡለን፤ ሞራ ከ500 ሺ ባለይ ...
Read More »የቀድሞው ፕሬዚዳንት የአንድነት ፓርቲ ሊቀመንበር ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ከእስር ተፈቱ
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዶ/ር ነጋሶ ዛሬ ከቀኑ 9 ሰአት ላይ ሽሮ ሜዳ በሚገኝ እስር ቤት ውስጥ እንዲታሰሩ መደረጉን የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳንኤል ተፈራ ከገለጹ ከሰአታት በሁዋላ ፣ ሊቀመንበሩ ማምሻውን ተፈትተዋል። አንድ ግለሰብ “የፓርቲው የሰላማዊ ሰልፍ የቅስቀሳ ግብረሀይል አባላት ያለፍላጎቴ ፎቶግራፍ አንስተውኛል” በሚል ክስ መመስረቱን ተከትሎ ፣ የቅስቀሳ አባላቱ መያዛቸውንና እነሱን ለማስፈታት ወደ ስፍራው ያቀኑት ...
Read More »ወታደራዊ መኮንኖች የደሞዝ ይጨመርልን ጥያቄ አቀረቡ
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ካለፉት 8 ቀናት ጀምሮ ስብሰባ ላይ ሲሆኑ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ዋነኛው የመነጋገሪያ አጀንዳ መሆኑ ታውቋል። ከመቶ አለቃ በላይ ማእረግ ያላቸው ወታደራዊ መኮንኖች ስብሰባዎችን እያካሄዱ ያሉት የጄኔራሎች ስብሰባ ከወር በፊት መጠናቀቁን ተከትሎ ነው። በጄኔራሎቹ ስብሰባ ላይ ለሰራዊቱ የደሞዝ ጭማሪ ጥያቄ ተነስቶ የነበረ ቢሆንም፣ “ሰራዊቱ አሁን የሚያገኘው ደሞዝ ለኑሮው ...
Read More »የሀይማኖት አቋም የእድገት መመዘኛ መስፈርት እንዲሆን ተወሰነ
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአቶ በረከት ስምኦን በተመራው የኢህአዴግ ማእከላዊ ኮሚቴ ውይይት ላይ ፣ የሀይማኖት አክራሪነት ከምርጫ 97 ቀጥሎ ከፍተኛ ፈታኝ አደጋ እንደሆነ ከተገለጸና ውይይት ከተካሄደ በሁዋላ የአገሪቱ ሲቪል ሰርቪስ የሀይማኖት ጉዳይን እንደ አንድ የእድገት መመዘኛ መስፈረት እንዲተገብር ስምምነት ላይ ተደርሷል። በጉባኤው ላይ የሐይማኖት አክራሪነት የመንግስትን ተቋም በማፈራረስ እና ተከታዮቹ ነፍጥ አንስተው መስዋእት እንዲሆኑ በማነሳሳት ከፍተኛ የሆነ ...
Read More »እነወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ ፕሬስ ካውንሰል መመስረት አልቻሉም
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ የመገናኛ ብዙሃን ምክርቤት ወይንም ፕሬስ ካውንሰል ለማቋቋም ኃላፊነቱን የተረከበው ጊዜያዊ ኮምቴ የካውንስሉን መስራች ጉባዔ መጥራት እንዳልቻለ ተጠቆመ፡፡ በኢህአዴግ ደጋፊነት በሚታወቁት ወ/ሮ ሚሚ ስብሃቱ የሚመራው ጊዜያዊ መስራች ኮምቴ ፕሬስ ካውንስሉን እንዲመሰረት ኃላፊነት ቢሰጠውም አመራሩ እርስበርስ ባለመግባባቱና ከብዙሃኑ ጋዜጠኞች አዎንታዊ ምላሽ ባለማግኘቱ የምስረታውን ጉዳይ ጥያቄ ምልክት ውስጥ ጥሎታል፡፡ ይህ ኮምቴ በወ/ሮ ሚሚ ሊቀመንበርነት፣ በአቶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ 3ተኛ ዓመት በጀርመን-ሙኒክ በደማቅ ሁኔታ ተከበረ።
መስከረም ፲፭(አስራ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቅዳሜ ከቀኑ 14 ሰዓት ጀምሮ ሙሉ ሌሊቱን ጭምር በደማቅ ሁኔታ በተከበረው የኢሳት 3ኛ ዓመት በዓል ላይ ‘ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች በርካታ ኢትዮጵያውያን ተገኝተዋል። በዝግጅቱ ኢሳት ከየት ተነስቶ የት ላይ እንደደረሰ በስፋት ያብራሩት የድርጅቱ ማኔጅንግ ዳይሬክተር አቶ ነዓምን ዘለቀ፤ኢሳት ለወደፊቱ መድረስ ያለበትን ደረጃ አስመልክቶ የተሰነቀውን ራዕይ ጠቁመዋል። ከፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች መካከል የኢህአፓው አመራር ዶክተር ዘነበ ...
Read More »የኢትዮጵያ አየር ሀይል መዳከሙን ካፒቴን አክሊሉ ተናገሩ
መስከረም ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ አየር ሃይል በመተው ሰሞኑን ግንቦት 7ትን ከተቀላቀሉት አብራሪዎች እና የበረራ አስተማሪዎች መካከል የተዋጊ ሄሊኮፕተር ተዋጊና አዛዥ የሆኑት ካፒቴን አክሊሉ መዘነ ዛሬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለምልልስ በአንድ ወቅት በገናናነቱ የሚታወቀው የኢትዮጵያ አየር ሐይል አሁን ያለበት ደረጃ የሚያሳፍር መሆኑን ተናግረዋል። በኢትዮጵያ ውስጥ ፍትህ ሰፍኖ አየር ሀይሉ ተመልሶ የሚገነባበት ጊዜ እንደሚመጣ የገለጹት ካፒቴን አክሊሉ፣ እስከ ዛሬ ...
Read More »