ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢትዮጵያና ኬንያ በግልገል ጊቤ ሶስተኛ የሀይል ማመንጫ ግድብ ላይ ያላቸውን አለመግባባት እልባት ለመስጠት የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ፕሮግራም ሁለቱንም ሀገራት በማግባባት ላይ እንደሆኑ ገለጹ፡፡ ኢትዮጵያ በኦሞ ወንዝ ላይ በመገንባት ላይ ያለችው የሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት በቅርብ የሚገኘውን የኬንያን ቱርካና ሀይቅ ይጎዳል በሚል የኬንያ መንግስት የአካባቢ ተቆርቋሪ ድርጅቶች ቅሬታቸውን ሲያሰሙ ቆይተዋል፡፡ የኦሞ ወንዝ ለቱርካና ሀይቅ ብቸኛ ...
Read More »ኢትዮጵያዊው ሳይንቲስት ሹመት አገኙ
ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ኢትዮጵያዊውን የእርሻ ሳይንቲስት አዲስ ለተቋቋመ የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ አባልነት መረጠው፡፡ ሳይንቲስቱ ፕሮፌሰር ገቢሳ ኢጀታ 26 አባላትን ላካተተው የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ ሲመርጥ ብቸኛ የእርሻ ሳይንቲስት እንደሆነ ኢሶሼትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡ አዲሱ የተባበሩት መንግስታት የሳይንቲስቶች አማካሪ ቦርድ በአለም አቀፍ በተለያዩ ዘርፍ የታወቁ ሳይንስቶችን በአባልነት ይዞ ይገኛል፡፡ አዲሱ ቦርድ በሳይንስና ቴክኖሎጂ እንዲሁም ...
Read More »የንዌር ዞን ግጭት ተባብሶ ቀጠለ
ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በጋምቤላ ክልል ንዌር ዞን ዋና ከተማ በሆነችው ሚኒኛንግ ከተማ የተፈጠረው ግጭት ተባብሶ የሞቱ የመከላከያ ሰራዊት ቁጥር መጨመሩና በርካታ መሳሪያዎች ከመከላከያ ካምፕ መወሰዳቸው ተገለጸ፡፡ ባለፋው እሁድ አንድ መሳሪያ የታጠቀ ሰው እግር ኳሱን ሲመለከቱ በነበሩ ሰዎች መካከል ባስነሳው አለመግባባት የመከላከያ ሰራዊት አባላት እና ነዋሪዎች ግጭት ውስጥ ገብተው ሰንብተዋል፡፡ ግጭቱ ተባብሶ በመቀጠሉ ሰሞኑን ከሞቱት ሶስት ...
Read More »በዳውሮ ዞን አዲስ ውጥረት ተቀሰቀሰ
ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ዳውሮ ዞን ከሁለት ዓመት በፊት ተቀስቅሶ የነበረው የመልካም አስተዳደር እጦት ጥያቄ በአዲስ መልክ መቅረብ በመጀመሩ በዞኑ ውጥረት መንገሱን ተገለጸ፡፡ በዞኑ የሚኖሩ ማህበረሰብ ከፍተኛ የሆን የመልካም አስተዳደር ችግር እንዳለባቸው በመግለጽ ላይ መሆናቸውን የዳውሮ ዞን አካባቢ ተወላጅ የሆኑት አቶ ፍሰሀ ተስፋዬ ከኢሳት ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ አመልክተዋል፡፡ አዲስ መነሳት የጀመረውን የህዝብ ጥያቄ ተከትሎም ...
Read More »ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የጨንጫ ወረዳ መምህራን የስራ ማቆም አድማ ላይ ናቸው
ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል በጋሞጎፋ ዞን በጨንጫ ወረዳ የሚገኙ የተለያዩ ትምህርት ቤት መምህራን ለአባይ ግድብ ማሰሪያ በሚል ከደሞዛቸው ላይ ገንዘብ መቆረጡን ተከትሎ ካለፉት 3 ቀናት ጀምሮ የስራ ማቆም አድማ እያደረጉ ነው፡፡ የጨንጫ ፣ ጭነቶ፣ ጦሎላ፣ ጨፌ፣ ጺዳ እና ቱክሻ ትምህርት ቤቶች መምህራን በአድማ ላይ መሆናቸውን ተከትሎ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ተማሪዎች ቤታቸው ለመቀመጥ ተገደዋል። የወረዳው እና የዞን ...
Read More »ጠ/ሚኒስትሩ ተቃዋሚዎችን “ይሄ መንግስት ፈርቷል እያላችሁ ራሳችሁን አታሞኙ” አሉ
ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ዛሬ በተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው ከፓርላማ አባላት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ መንግስት የጎዳና ላይ ነውጥ ከሚያሰቡት ሀይሎች ጋር ለመነጋገር የማይችልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረዋል። አቶ ሀይለማርያም በተቃዋሚዎች በኩል የሚቀርበው ቅጥ ያጣ ፍረጃ እና የጥላቻ ፖለቲካ እንዲቆም እንዲሁም የጎዳና ላይ ነውጥ እናደርጋለን በማለት የሚያስቡ ሀይሎችም ሀሳባቸውን እንዲያቆሙ ጠይቀዋል። “የጎዳና ላይ ነውጥ ለማስነሳት በቂ መረጃ ...
Read More »32ኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ጉባኤ በጥሩ መንፈስ እየተካሄ ነው ተባለ
ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባቶች ለኢሳት እንደገለጹት በዛሬው ስብሰባ የልማት ኮሚሽኑ ሪፖርት ሰፊ ሽፋን የተሰጠው ሲሆን፣ መንግስት በቤተክርስቲያኑዋ ገቢ ላይ እየተጠቀመ መሆኑ ተነግሯል። የኮሚሽኑ መሪ ” በጭንቅ ውስጥ ነው እየሰራን ያለነው ፣ በመኖርና ባለመኖር ውስጥ እንገኛለን ያሉ” ሲሆን፣ ስሜታቸውን በድፍረት ሲናገሩ ከዋሉት ጳጳሳት መካከል ብጹዕ አቡነ ቄርሊዎስ ” ዛሬ ጀመርነው፣ እስካሁን የለንም ነበር፣ ዛሬ ስለቤተክርስቲያን ...
Read More »አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከገቢዎችና ጉምሩክ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት የሙስና ክስ ጋር በተያያዘ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ከባለሃብቶች ጋር የነበራቸው ቁርኝት የልማታችን ጸር ነበር አሉ፡፡
ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አቶ ኃ/ማርያም ዛሬ ጠዋት የአገር አቀፍ የጸረ ሙስና ጥምረት 2ኛ መደበኛ ስብሰባ በሸራተን አዲስ በተካሄደበት ስነስርኣት ላይ ተገኝተው ባደረጉት ንግግር አንዳንዶቹ ባለሃብቶች ከከፍተኛ መንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ሳይቀር የጠበቀ ቁርኝት ፈጥረው እንደነበር አምነው በዚህም ምክንያት ሰዎቹን መንግስት አይደፍራቸውም ተብሎ በህብረተሰቡ ዘንድ እስከመገመት ደርሶ ነበር ሲሉ ተናግረዋል፡፡ እንደዚህ ዓይነት የመንግስት ባለስልጣናትና ኪራይ ሰብሳቢ ባለሃብቶች ቁርኝታቸውን ...
Read More »በአፍሪካ ዋና ከተማ 24 ሰዓት ውሀ የሚያገኘው 65 በመቶው ህዝብ ብቻ ነው
ጥቅምት ፯(ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ በአዲስ አበባ የውሀ ቀለም አይቶ የማያውቅ ህዝብ አለ በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ 65 በመቶ የሚሆነው የአዲስ አበባ ህዝብ ውሀ 24 ሰአት እንደሚያገኝ ገልጸው፣ 20 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት 5 ቀናት፣ ከ10-15 በመቶ የሚሆነው ደግሞ በሳምንት አንድ ቀን ውሀ ያገኛል ብለዋል። በአብዛኛው የአፍሪካ ዋና ዋና ከተሞች የውሀ አቅርቦት ከ75 እስከ 99 በመቶ ...
Read More »የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ በመንግስት ላይ ተቃውሞ አሰማች
ጥቅምት ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአዲስ አበባ አራት ኪሎ በሚገኘው መንበረ ፓትሪያርክ ስብሰባ አዳራሽ በመካሄድ ላይ ባለው 32ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ በቤተክርስቲያኑዋ ታሪክ ተሰምቶ የማያውቅ ተቃውሞ ተከስቷል። አንድ በስብሰባው ላይ የተሳተፉ አባት እንደገለጹት በስብሰባው ላይ ” ይህ መንግስት የኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንን ለማፍረስ እንደተነሳ በስፋት ተነግሯል። የፌደራል ጉዳዮች የሀይማኖት ክፍል ሃላፊዎች ዛሬ ስለ አክራሪነትና ጽንፈኝነት ገለጻ ለመስጠት በተገኙበት ወቅት ነው ...
Read More »