ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፓርቲው ይህን የገለጸው ጠ/ሚ ሀይለማርያም ደሳለኝ ” በቂ ጥበቃ የለንም በሚል ሰላማዊ ሰልፍን እንደሚከለክሉ” መናገራቸውን ተከትሎ በሰጠው መልስ ነው። ” በቂ ጥበቃ ማድረግ ያልቻለ መንግስት ስልጣኑን ለህዝብ በማስረከብ ይቅርታ ጠይቆ መሄድ እንጅ ከአሁን በኋላ መብታችሁን አታገኟትም ” በማለት መዛት ትዝብት ውስጥ የሚጥል ድርጊት ነው ብሎአል አንድነት በመግለጫው፡፡ አንድነት ” ተገዥነቱን ለህዝቡና ለህግ አድርጎ በአምባገነኖች ...
Read More »በሰሜን ጎንደር ስር የነበሩ ሁለት ወረዳዎችን በትግራይ ክልል ውስጥ ለማካተት እንቅስቃሴ መጀመሩን ፍኖተ-ነፃነት ዘገበ።
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአንድነት ለፍትህና ለዲሞክራሲ ፓርቲ ልሳን የሆነው ፍኖተ-ነፃነት እንደዘገበው፦አብረሃ ጅራ እና አብደራጊ የተባሉ ሁለት ወረዳዎች ከዚህ በፊት በአማራ ክልል በሰሜን ጎንደር ዞን ስር የነበሩ ቢሆንም፤ መሬቱ ግን ባብዛኛው በቅርብ ጊዜ ከትግራይ ክልል በመጡ ገበሬዎች ተይዟል፡፡ ቦታዎቹ በብዛትና በስፋት የሰፈሩት ገበሬዎቹች አስተዳደራዊ የበላይነትን በመጠቀም ወረዳዎቹን ወደ ትግራይ ለማካለል እንቅስቃሴ መጀመራቸው ተጠቁሟል፡፡ ይህንኑ ጉዳይ በተመለከተ ጥቅምት 5 ...
Read More »ሙሉ ክፍያ የከፈሉ የ40/60 መኖሪያ ቤት ተመዝጋቢዎች ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መንግስት ማግባባት ጀመረ።
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት ራሱ የ 40 በ 60 መኖሪያ ቤት ሠርቶ ለመስጠት የሰጠውን መግለጫ አምነው ከ81 ሺህ ሰዎች በላይ ሙሉ ክፍያ ከፈፀሙ በሁዋላ፤ ሀሳቡን በመቀየር ከፋዮቹ በማህበር ተደራጅተው ቤቱን ራሳቸው እንዲሠሩ መወሰኑ ተመዝጋቢዎችን አሳዝኗል። እንደ ሪፖርተር ዘገባ በአሁኑ ጊዜ መቶ በመቶ የከፈሉ የ40/60 ተመዝጋቢዎች በመኖርያ ቤት ኅብረት ሥራ ማኅበር ወደ ተነደፈው ፕሮግራም እንዲዛወሩ የአዲስ አበባ አስተዳደር ...
Read More »መለስ የሚባል ራእይ የለም ሲሉ አቶ ስብሀት ነጋ ተናገሩ
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህዝባዊ ወያነ ሀርነት ትግራይ(ህወሀት) ውስጥ የተካረረ አለመግባባት እንደተፈጠረ በስፋት በሚነገርበት በዚህ ወቅት አቶ ስብሀት ነጋ ፣ የኢህአዴግ እንጂ የመለስ የሚባል ራእይ የለም ብለዋል። የህወሀት መስራች የሆኑት አቶ ስብሀት ነጋ ይህን ያሉት ከጋዜጠኛ ደረጀ ደስታ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ ነው። አቶ ስብሀት ፦” መለስ የ ኢህአዴግን ራዕይ ለማስፈፀም ከፊት ሆኖ ብዙ ሥራ ሠራ እንጂ ራዕዩ የመለስ ...
Read More »የኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ከፍተኛ ድክመት እየታየበት ነው
ጥቅምት ፲(አስር)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የንግድ ሚኒስቴርና የክልሉ ቢሮዎች የ2006 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ያተኮረ የውይይት መድረክ በጊዎን ሆቴል ባደረጉበት ወቅት ሚኒስቴሩ አቶ ከበደ ጫኔ ” በ2005 የበጀት ዓመት የስራ አፈፃፀም የታሰበውን ያክል ትርፋማ መሆን አልተቻለም፡፡” ብለዋል። ችግሮቹ ሐገራዊ ፣ አለማቀፋዊና አህጉራዊ ይዘት እንዳላቸውም ሚኒስትሩ አክለዋል። በ2005 በጀት አመት 4 ቢሊዮን 600 ሚሊዮን ዶላር ለመሰብሰብ ታቅዶ 68 ነጥብ ስድሰት ...
Read More »የስዊድን የጦር ኮሚሽን በኦጋዴን ስለተፈጸመው ወንጀል አፋጣኝ መልስ እንደሚሰጥ አስታወቀ
ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኦጋዴን የሚፈጸመውን የሰብአዊ መብት ጥሰትና የጦር ወንጀል የሚያሳየው ዘጋቢ ፊልም በቅርቡ በስዊድን ቴሌቪዥን መለቀቁን ተከትሎ ዛሬ አርብ፣ የስዊድን የጦር ኮሚሽን ማስረጃዎችን ተረክቧል። ማስረጃዎችን ለኮሚሽኑ ያስረከቡት ሂደቱ ዋና ተወናይ የሆነው ወጣት አብዱላሂ የሱፍና የአለማቀፍ የህግ ባለሙያዎች ኮሚሽን ኮሚሽነር የሆኑት ስቴላ ጋርደ ናቸው። የጦር ኮሚሽኑ የቀረበለትን ማስረጃ በማየት አፋጣኝ ውሳኔ እንደሚሰጥ መግለጹን ወጣት አብዱላሂ ለኢሳት ተናግሯል። ...
Read More »በኢትዮጵያ የማእከላዊ እስር ቤት ውስጥ በእስረኞች ስቃይ ይፈጸማል ሲል ሁማን ራይትስ ወች አስታወቀ
ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰብአዊ መብት ድርጅቱ ” በማዕከላዊ የሚገኙት መርማሪ ፖሊሶች ታሳሪዎች ጥፋታቸውን እንዲያምኑ፣ እንዲናገሩ ወይም ሌላ መረጃ እንዲያወጡ የሚያደርጉት በሃይል የማስፈራራት መንገድን በመጠቀም ሲሆን ይህም እስከ ማሰቃየት እና ሌላ ጎጂ አያያዝ እስከ መፈጸም ይደርሳል፡፡ ” ብሎአል። ከ2002 ዓም እስከ 2005 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ በማእከላዊ እስር ቤት የተፈጸሙ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችን በሚዘረዝረው መግለጫ ፣ በእስር ቤቱ ...
Read More »ከሙስና ጋር በተያያዘ ኢህአዴግ ችግር ውስጥ መሆኑን አቶ ሰብሃት ተናገሩ
ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ ከሙስና መንሰራፋት ጋር በተያያዘ የገጠመውን ፈተና በድል ለመወጣት ሕዝቡን ማሳተፍ እንዳለበትና ያለሕዝቡ ተሳትፎ የሚደረጉ ነገሮች ሁሉ የማይመለስ ጥፋትን ያስከትላሉ ሲሉ አቶ ስብሃት ነጋ ለኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችን ምክር ለግሰዋል። የጸረ ሙስና ኮምሽን በሸራተን ሆቴል ያዘጋጀውና በምክትል ጠ/ሚኒስትር ማዕረግ የሲቪል ሰርቪስ ሚኒስትር የሆኑት አቶ ሙክታር ከድር እና የፓርላማው አፈጉባዔ አቶ አባዱላ ገመዳ በመሩትና ዛሬ በተጠናቀቀው ...
Read More »የዋግ ህምራ ህዝብ ከመንገድ ጋር በተያያዘ ጩኸት ማሰማቱን ቀጥሎአል
ጥቅምት ፰(ስምንት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከመንገድ ጋር በተያያዘ ከዋግ ህምራ ዞን ርዕሰ ከተማ ሰቆጣ የሚሰማው የተቃውሞ ድምጽ በሁሉም የዞኑ ወርዳዎች መዳረሱን በስፍራው ያሉ ወኪሎች ገልጸዋል፡፡ ” የልማት ጥያቄያችን አልተመለሰም ፤ መንግስት ሰቆጣን እረሰቱዋል ፤ አገልግሎት ለማግኘት ወደ ትግራይ መሄድ ግድ ብሎናል” ሲሉ ነዋሪዎች ለመንግስት ባለስልጣናት ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በቅርቡ ከሰቆጣ ፤ አበርገሌ ፤ ዝቋላ፤ ስሃላ ሰየምት ፤ድሃና ፤ ጋዝ ጊብላ ...
Read More »ኢትዮጵያ እስረኞችን በማሰቃየት ምርመራ እንደምታካሂድ ተገለጸ
ጥቅምት ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ባለስልጣናት የፓለቲካ እስረኞች ላይ ምርመራ ሲያካሂዱ ስቃይ እንደሚፈጽሙ ተቀማጭነቱን በአሜሪካ ያደረገው ሂዩማን ራይትስ ዎች ዛሬ ይፋ አደረገ፡፡ መንግስት በበኩሉ የቀረበውን ውንጀላ አስተባብሎ ሪፖርቱ ከእውነት የራቀና ተአማኝነት የሌለው ነው ብሏል፡፡ ድርጅቱ ታስረው የነበሩ እማኞች ዋቢ በማድረግ ባወጣው ሪፖርት ባለስልጣናት ከእስረኞች ቃል ለመቀበል ሲሉና ምርመራ ሲያካሂዱ ድብደባ እንደሚፈጽሙ አመልክቷል፡፡ በተለይ የጸጥታ አካላትና ፓሊሶች በማዕከላዊ ...
Read More »