ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰንደቅ እንደዘገበው በ2004 በጀት ዓመት ባልተሟላ ሰነድ ከ3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ባላይ ወጪ በማድረጉ በፌዴራል ዋና ኦዲተር መ/ቤት ጠንካራ ትችት የቀረበበት የመከላከያ ሚኒስቴር የሒሳብ መዛግብቱን ዋናው ኦዲተርን ጨምሮ ለማንኛውም አካል ሚስጢር ማድረግ የሚያስችለውን ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጅቷል። አዲሱ የመከላከያ ሠራዊት ረቂቅ አዋጅ ሰነድ በአንቀጽ 72 ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት አገራዊ ጥቅምንና ደህንነትን ...
Read More »ኢትዩጵያ በምግብ እጥረት የተነሳ ከልጆቹዋ በየዓመቱ 144 ቢሊዮን ብር ታጣለች ተባለ
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወጣት እስከ አዋቂ ያለው ከግማሽ በላይ የሚሆነው ኢትዮጵያ በልጅነቱ በቂ ምግብ ሳያገኝ ተጎድቶ እንደሚያድግ የተመለከተው በኢትዮጵያ ይፋ በሆነው the cost of hunger in Ethiopia ጥናት ውስጥ ነው። 67 ከመቶ የሚሆነውና ከ15 አስከ 64 የእድሜ ክልል ውስጥ ያለው ኢትዮጵያዊ ጠንካራ ሰራተኛ ቢመስልም በልጅነቱ ያጣው የተመጣጠነ ምግብ አቀንጭሮትና አቀጭጮት አቅም አሳጥቶት በስራው ውጤታማ እንዳይሆን ...
Read More »በአፋር ሚሌ በሚደረገው ፍተሻ ሾፌሮች መማረራቸውን ገለጹ
ጥቅምት ፳፯(ሃያ ሰባት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሾፈሮቹ ለኢሳት እንደገለጹት ከኢትዮጵያ ወደ ጅቡቲ የሚሄዱና ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ እቃዎችን የጫኑ ተሽከርካሪዎች ተፈትሸው ለማለፍ ረጅም ጊዜ እንደሚወስዱባቸው ተናግረዋል። ከ10 እስከ 15 ኪሎ ሜትር የሚደርስ የመኪኖች ሰልፍ መኖሩን የሚናገሩት ሾፌሮች፣ በጸሀይ ላይ በሚያደርጉት ጥበቃ በርካታ ሾፌሮች እየተጎዱ መሆኑንም ይገልጻሉ። ፍተሻው የተጀመረው ዛሬ አራት አመት ገደማ ቢሆንም፣ ሰሞኑን የሚታየው ፍተሻ ከወትሮው በከፋ ...
Read More »የጅጅጋ ነዋሪዎች በብሄር ብሄረሰቦች በአል ስም የሚደርስብን እንግልት ከፍቷል ይላሉ
ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ገዢው ፓርቲ መጪውን የብሄር ብሄረሰቦች ቀን ለማክበር በጅጅጋ ከተማ ዝግጅት በማድረግ ላይ መሆኑ ይታወቃል። ለገዢው ፓርቲ ታማኞች ናቸው የተባሉና ” በተለምዶ ልማታዊ አርቲስትና ጋዜጠኞች እየተባሉ የሚጠሩ ታዋቂ ሰዎች አካባቢውን በመጎብኘት አድናቆታቸውን ሰጥተዋል። ኢሳት በክልሉ ያለውን ሁኔታ ከዘገበ በሁዋላ የተለያዩ ነዋሪዎች እና ጎብኝዎች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል። ክልሉን በቅርቡ አይታ የተመለሰች የመሀል አገር ወጣት፣ ዘመዶቿን ...
Read More »በአዋሳ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ተወግቶ ተገድሎአል
ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከምሽቱ 7 አካባቢ አንድ የውጭ አገር ዜጋ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ጀርባው አካባቢ በጩቤ ተወግቶ መገደሉን ለማወቅ ተችሎአል። ግለሰቡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰራተኛ ሳይሆን አይቀርም። ግድያውን ማን እንደፈጸመውና ለምን እንደተፈጸመ የታወቀ ነገር የለም። የክልሉን ፖሊስ ለማነጋገር ሙከራ ብናደርግም አልተሳካልንም። ተጨማሪ መረጃዎች እንደደረሱን የምናቀርብ መሆናችንን እንገልጻለን።
Read More »የጋዜጠኛ ኤፍሬምን ህይወት ለማትረፍ የሚደረገው መዋጮ አርኪ አይደለም ተባለ
ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጥቅምት 20 ቀን 2006 ዓ.ም በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ የቀረበባቸውን የስም ማጥፋት ክስ ፍ/ቤት ቀርበው ምላሽ ለመስጠት ወደ ሐዋሳ ያመሩት የኢትዮ ምህዳር ጋዜጣ ባልደረቦች ከደረሰባቸው የባጃጅ ተሸከርካሪ አደጋ ጋር በተያያዘ በተለይ ኤፍሬም በየነ ላይ የከፋ ጉዳት መድረሱን ተከትሎ በመዋጮ ህይወቱን ለማትረፍ እየተደረገ ያለው ጥረት እስካሁን ውጤቱ አመርቂ አለመሆኑን አንድ የዕርዳታ አሰባሳቢ ኮምቴ አባል አስታወቀ፡፡ ጋዜጠኛ ኤፍሬም ...
Read More »ህወሀት በእነ አቶ ስየ ላይ የጀመረውን ዘመቻ ቀጥሎበታል
ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህወሀት በውስጡ የተነሳበትን መከፋፈል ለማስቀረት በእነ አቶ ስብሀት ነጋ የሚመራው ቡድን የቀድሞ ታጋዮችን በማሰባሰብ ህወሀትን ለማዳን በሚረባረብበት ጊዜ፣ በአቶ ስየ አብርሀ እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የተጀመረው ዘመቻ ግን እንደቀጠለ መሆኑ ታውቋል። አቶ ስየ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴያቸው በእጅጉ የተገታ ቢሆንም፣ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ( ኢቲቪ) ” የነቀዙ ሀይሎች” በሚል በእርሳቸውና በአቶ ታምራት ላይኔ ላይ የዶክመንታሪ ፊልም ...
Read More »ኢትዮጵያ እና ግብጽ በአባይ ጉዳይ ሳይስማሙ ቀሩ
ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሱዳን፣ ኢትዮጵያ እና ግብጽ መካከል በካርቱም የተካሄደው የአንድ ቀን ስብሰባ ያለውጤት ተጠናቋል። በኢትዮጵያና ግብጽ መካከል ልዩነቶች የተፈጠሩ ሲሆን፣ ልዩነቶችን ለማጥበብ ስለሚወሰደው እርምጃም አልተስማሙም። ብዙ ክብደት ተሰጥቶት የነበረው ስብሰባ በአንድ ቀን መጠናቀቁ በሁለቱ አገራት መካካል ያለው ልዩነት እየሰፋ መሄዱን የሚያሳይ ነው ተብሎአል። ምንም እንኳ ከአንድ ወር በሁዋላ አገራቱ ተመልሰው እንደሚገናኙ ቢገለጽም፣ ግብጽ ዬያዘችው ...
Read More »መሀመድ ሙርሲ የግብጽ ፕሬዳንት ነኝ ሲሉ ተናገሩ
ጥቅምት ፳፮(ሃያ ስድስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በግብጽ የተቀሰቀሰን አመጽ ተከትሎ በወታደራዊ ሀይሉ ጣልቃ ገብነት ከስልጣን የተወገዱትና በእስር ላይ የሚገኙት መሀመድ ሙርሲ በካይሮ ጉዳያቸውን እንዲያስችል በተሰየመው ፍርድ ቤት ቀርበው የግብጽ ፕሬዳንት መሆናቸውን ተናገሩ። ሙርሲ፦የተከሰሱበት መንገድ ህገወጥ መሆኑንና እርሳቸው የግብጽ ህጋዊ ፕሬዳንት ሆነው መቀጠል እንዳለባቸው ነው ለዳኞች የተናገሩት። እንደ ቢቢሲ ሪፖርት ሙርሲና ሌሎች 14 የሙስሊም ብራ ዘር ሁድ ...
Read More »አዲሱ የመከላከያ አዋጅ በአንድ ብሄር የበላይነት ላይ የተመሰረተውን አደረጃጀት አይቀይረውም ተባለ
ጥቅምት ፳፭(ሃያ አምስት )ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የህዝብ ተወካዩች ምክር ቤት የውጭ መከላከያ ደህንነት እንዲሁም የህግ፣ ፍትህ እና የአስተዳደር ጉዳዩች ቋሚ ኮሜቴዎች አባላት ሰሞኑን እንዲወያዩበት በተደረገው የመከላከያ አዋጅ 98 በመቶ የሚሆኑት ወታደራዊ አዛዦች ከአንድ ብሄር የሆኑበትን አወቃቀር እንደማይለውጠው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው መኮንኖች ተናግረዋል: የመከላከያ ሚኒስቴር ሹሞች በበኩላቸው አዋጁ እስከ ዛሬ የነበሩትን ህጎች ሁሉ የሚለውጥና መከላከያን የሚያሳድግ ነው ይላሉ። ከማእረግ ...
Read More »