ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢህአዴግ አገሪቱን እንደተቆጣጠረ ተሀድሶ አልወሰዱም በሚሉና በተለያዩ ሰበቦች የጡረታ መብታቸው ላልተከበረላቸው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት አባላት፣ የጡረታ መብታቸውን ለማስከበር መንግስት ጥሪ ማቅረቡ ታውቋል። የመንግስት ሹሞች የቀድሞ ወተዳሮቹን ፎርም እንዲሞሉ እያደረጉዋቸው መሆኑን አንዳንድ ወታደሮች ለኢሳት ገልጸዋል። መንግስት በአሁኑ ጊዜ ይህን እርምጃ ለምን ለመውሰድ እንደፈለገ አልታወቀም። ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች በኤርትራ የሚንቀሳቀሱ የተቃዋሚ ሀይሎች የፈጠሩት ...
Read More »በላይ አርማጭሆ ትክል ድንጋይ ወረዳ አንድ አውቶቡስ ተገልብጦ የ6 ሰዎች ህይወት አለፈ
ህዳር ፳፮(ሃያ ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ምንጮች እንደገለጹት በአደጋው 40 ሰዎች የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸዋል። የአደጋው መንስኤም ከአቅም በላይ ጭነት መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። በጭልጋ ወረዳ ደግሞ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ መኪና ተገልብጦ ተሽከርካሪዎች ለመተላላፍ ባለማቻላቸው መቸገራቸውን ለማወቅ ተችሎአል። መኪናው ነዳጅ እንደጫነ በመገልበጡ እሳት ይፈጠራል የሚል ስጋት ማሳደሩን የአካባቢው ሰዎች ግልጸዋል።
Read More »ሳውድ አረቢያ የውጭ ዜጎችን ማስወጣቱዋን እንደምትቀጥል አስታወቀች
ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ካለፈው ወር ጀምሮ ህጋዊ ወረቀት የላቸውም በሚል የውጭ ዜጎችን ማባረር የቀጠለችው ሳውድ አረቢያ፣ ከአለማቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድርጅት ትችት ቢደርስባትም፣ ዜጎችን ማስወጣት እንደምትቀጥል አስታውቃለች። አረብ ኒውስ እስካሁን በተወሰደው እርምጃ 126 ሺ ሰዎች ከአገሪቱ መውጣታቸውን ገልጿል። የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ 90 ሺ ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው መግባታቸውን ገልጸዋል። አረብ ኒውስ አንድ ባለስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ውጭ ዜጎችን የማስወጣት ...
Read More »በኢትዮጵያ የሚታየው የግብር አሰባሰብና ሙስና ህዝቡን እያስመረረ ነው
ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ በደብረማርቆስ ከተማ ተደርጎ በነበረው የህዝብ ስብሰባ ላይ ነርካታ ነጋዴዎች በታክስ መማረራቸውን ገልጸዋል። መቶ አለቃ ስመኝ መኩሪያው እንዳሉት መንግስትን አክብረን በቫት ብንገባም በአንድ አነስተኛ የንግድ ሱቅ በየወሩ እስከ 73 ሺ ብር ተጠይቀን ፤ መንቀሳቀስ አልቻልንም የምንነግደውን ሊወርሰን የሚሽከረከረው መንግስት ሚዛኑ የሚጥልብን ግብር አስመርሮናል ሲሉ ተናግረዋል፡፡ “የምንሰራውን ስራ በማቋረጥ አሰረክበን እንድንቀመጥ አሰገድዶናል ፣ ሃገራችንን ...
Read More »በመርካቶ በደረሰ ቃጠሎ መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ወደመ
ህዳር ፳፭(ሃያ አምስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቦንብ ተራና እና ጆንያ ተራ የሚባሉት አካባቢዎች ዛሬ ቀን ላይ በከፍተኛ የእሳት አደጋ የተጠቁ ሲሆን የከተማዋ የእሳት አደጋ በጊዜው ባለመድረሱም በነዋሪዎች ከፍኛ ተወቅሷል። የመስተዳድሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ሰራተኛ አቶ ንጋቱ ማሞ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረው ጥሪው የደረሳቸው አደጋው ከደረሰ ከ45 ደቂቃ በሁዋላ መሆኑን ተናግረዋል። አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ግን ...
Read More »ኢህአዴግ ለግንቦት7 ያቀረበው የእንደራደር ጥያቄ የተለያዩ አስተያየቶችን እያስተናገደ ነው
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በተለያዩ የኢትዮጵያ ክፍሎች የሚኖሩ ዜጎች በስልክ እየሰጡ ባለው አስተያየት ግንቦት7 ከኢህአዴግ ጋር መነጋገሩን አይደግፉም። አብዛኞቹ የሚሰጡት ምክንያት ደግሞ “ኢህአዴግ ተዳክሟል፣ ኢህአዴግ የሚታመን ድርጅት አይደለም” የሚሉ ናቸው። በዚህ ዙሪያ ኢትዮጵያውያን የሰጡት አስተያየት የሚከተለውን ይመስላል በሌላ በኩል ደግሞ የተወሰኑ ኢትዮጵያውያን የድርድሩ ዜና መልካም ወሬ መሆኑን ለኢሳት በላኩት የኢሜል መልክት አስታውቀዋል። ኢትዮጵያ ውስጥ ሁሉም ፓርቲዎች በሰላም ...
Read More »በጅጅጋ የሚታየው ስረአት አልባነት ተባብሷል
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጅጅጋ በማንኛውም ሰአት ዜጎች ቤታቸው በጸጥታ ሀይሎች ይፈታሻል። የጸጥታ ሀይሎችም ከሞባይል ስልክ ጀምሮ እስከ ላፕቶፕ እንዲሁም ገንዘብ ይወስዳሉ። የቀበሌ መታወቂያዎችን ሳይዙ ከሄዱ ደግሞ ተጠርጥረው ይያዛሉ። የከተማዋ ነዋሪዎች እንደሚሉት ጅጅጋ ለኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ በላይ የስቃይ መሬት ሆናለች ። አንድንድ ምንጮች እንደሚሉት ችግሩን የተወሳሰበ ያደረገው አልሸባብ በጅጅጋው ፕሬዝዳንት የግል ሞባይል ላይ የብሄር ብሄረሰቦች በአል በከተማዋ ...
Read More »በዱራሜ ከተማ በተነሳ ግጭት በርካታ ሰዎች ተጎዱ
ህዳር ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ቅዳሜ በከንባታ ጠንባሮ ዞን በዱራሜ ከተማ ገበያ ላይ በተነሳው ተቃውሞ አንድ ታዳጊ ሲገደል ሁለት ፖሊሶች ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ገበያተኞችም ጉዳት ደርሶባቸዋል። ግጭቱ የደረሰው የከተማው ግብር ሰብሳቢዎች አነስተኛ ነጋዴዎች ቡና መሸጥ እንዲያቆሙ ማስገደዳቸውን ተከትሎ ነው። አርሶአደሮች የተወሰኑ ኪሎ ቡናዎችን ወደ ገበያ በመውሰድ የመሸጥ የዘመናት ልማድ ያላቸው ሲሆን፣ የከተማው ግብር ሰብሳቢዎች ደግሞ ” ንግድ ...
Read More »ኢህአዴግ ለግንቦት7 የድርድር ጥያቄ አቀረበ
ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ሰዎች እንደገለጹት ኢህአዴግ የእንደራደር ጥያቄውን በሁሉት ወር ጊዜ ውስጥ ለ3ኛ ጊዜ ማቅረቡ ነው። ግንቦት 7 የፍትህ፣ የነፃነትና የዲሞክራሲ ንቅናቄ ኢሳት ላቀረበው ጥያቄ በሰጠው የጽሁፍ መልስ “የእንደራደር” ጥያቄ እንደቀረበለት አምኖ፣ “ይሁን እንጅ ንቅናቄው በዋናነት ወያኔ እንደለመደው ድርድርን ለውጥረት ማስተንፈሻነት ለመጠቀም” ያደረገው ነው ብሎአል። የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚመኘውም ሆነ ግንቦት 7 የሚፈልገው ዲሞክራሲያዊ ...
Read More »አለማቀፉ የሰብአዊ መብቶች ተቆርቋሪ ድርጅት የሳውድ አረቢያ መንግስት በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት ምርመራ እንዲያደርግና እርምጃ እንዲወስድ አሳሰበ
ህዳር ፳፫(ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሂውማን ራይትስ ወች ባወጣው መግለጫ የሳውዲ የጸጥታ ሀይሎችና የሳውዲ ዜጎች በኢትዮጵያውያን ስደተኞች ላይ የሀይል እርምጃ በመውስድ ጉዳት አድርሰዋል። በኢትዮጵያውያን ሰራተኞች ላይ ለተፈጸመው ጥቃት የሳውድ አረቢያ መንግስት አስፈላጊውን ምርመራ በማድረግ በአጥፊዎቹ ላይ ተገቢውን እርምጃ ሊወስድ ይገባል ያለው ድርጅቱ በአሁኑ ሰአት በማጎሪያ ካምፖች ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያውያን በቶሎ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ እስከዚያው በቂ ምግብ፣ መጠለያና የህክምና ...
Read More »