በመርካቶ በደረሰ ቃጠሎ መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ወደመ

ህዳር (ሃያ አምስ)ቀን ፳፻፮ / ኢሳት ዜና :-ቦንብ ተራና እና ጆንያ ተራ የሚባሉት አካባቢዎች ዛሬ ቀን ላይ በከፍተኛ የእሳት አደጋ የተጠቁ ሲሆን የከተማዋ የእሳት አደጋ በጊዜው ባለመድረሱም በነዋሪዎች ከፍኛ ተወቅሷል።

የመስተዳድሩ የእሳትና ድንገተኛ አደጋ የህዝብ ግኑኝነት ሰራተኛ አቶ ንጋቱ ማሞ በ10 ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ተናግረው ጥሪው የደረሳቸው አደጋው ከደረሰ ከ45 ደቂቃ በሁዋላ መሆኑን ተናግረዋል።

አንዳንድ አስተያየት ሰጪዎች እንደሚሉት ግን መንግስት አካባቢውን ለልማት በሚል ሰበብ እሳቱ ሆን ብሎ እንዲነሳ አድርጓል። ኢሳት የመንግስትን አስተያየት ለማግኘት ለመንግስት ቃል አቀባይ ስልክ ቢደውልም ቃል አቀባዩን ለማግኘት አልቻለም።