ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውሃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚኒስትር አለማየሁ ተገኑ ህዳር 26 ቀን 2007፣ በቁጥር ውመአሚ 1/01/67 በጻፉት ደብዳቤ ” በክልሎችና በከተማ አስተዳደሮች በከፍተኛ ወጪ ተገንብተው ለበርካታ ኢንተርፕራይዞች የመስሪያና መሸጫ አገልግሎት የሚውሉ ህንጻዎችና ሼዶች በኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ችግር ምክንያት ለታለመላቸው አላማ ለማዋል ” አልተቻለም ብለዋል። “በእነዚህ ማእከላት ውስጥም በከፍተኛ የውጪ ምንዛሬ የገቡና ሊገቡ የተሳቡ የማምረቻ ማሽነሪዎች ምርትን ...
Read More »በሽብር ወንጀል ተጠርጥረው የተከሰሱት በድጋሜ ተቀጠሩ
ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእነ ዘላለም ወርቃገኘሁ የክስ መዝገብ የሽብር ክስ የተመሰረተባቸው የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሮችን ጨምሮ 10ሩም ተከሳሾች የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ልደታ 19ኛው ወንጀል ምድብ ችሎት ቤት ቢቀርቡም ሌላ ቀጠሮ እንደተሰጣቸው ነገረ ኢትዮጵያ ዘግቧል። የሰማያዊ፣ የአንድነትና የአረና ፓርቲዎች አመራሮች የሆኑት አቶ የሺዋስ አሰፋ፣ አቶ ሀብታሙ አያሌው፣ አቶ ዳንኤል ሺበሺ እና አቶ አብርሃ ደስታ እንዲሁም አንደኛ ተከሳሽን ...
Read More »ንግድ ባንክ ከባንክ ውጭ የሚደረግ የገንዘብ ሽግግርን ለማስቀረት በውጭ አገራት ቅርንጫፍ ባንኮችን ሊከፍት መሆኑን አስታወቀ
ታኀሳስ ፱(ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባንኩ እንደሚለው በርካታ ኢትዮጵያውያን በሚኖሩባቸው አገሮች ቅርንጫፎችን በመክፈት በአመት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን፣ ከባንክ ውጭ የሚደረገውን ገንዘብ የማስተላለፍ ዘዴ ለመቆጣጠር አስቧል። አሜሪካ፣ ደቡብ አፍሪካ፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስና ሳውድ አረቢያ በመጀመሪያው ዙር የንግድ ባንኮች ቅርንጫፎች ከሚከፈትባቸው አገራት ተርታ ተመድበዋል። ባንኮቹ መከፈታቸው ኢትዮጵያውያን ወደ አገራቸው የሚልኩትን ገንዘብ ለመጨመር እንደሚረዳም ጠቅሷል። ኢትዮጵያ ምርት ወደ ውጭ ...
Read More »ህወሃት በመንግስት ወጪ 40ኛ አመቱን ለማክበር ሸርጉድ እያለ ነው
ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በከፍተኛ ዝግጅት ይከበራል የተባለው የህወሃት 40ኛ አመት በአል ወጪ የሚሸፈነው ከመንግስት ካዝና መሆኑ በአባል ድርጅቶች መካከል መነጋገሪያ አጀንዳ እየሆነ መምጣቱን የሚናገሩት የኢህአዴግ ምንጮች፣ ከመንግስት ካዝና ለሚወጣው ገንዘብ የተሰጠው ሰበብ ገጽታ ግንባታ የሚል መሆኑን ገልጸዋል። ህወሃት በአሉን ከድርጅቱ ካዝና በተለይም የአገሪቱን ሲሶ ሃብት ከተቆጣጠረው ኢፈርት ካዝና መጠቀም እየቻለ፣ ወጪውን መንግስት እንዲሸፍነው ማስደረጉ ለብዙዎቹ አልተዋጠላቸውም። ...
Read More »በሃረር ከ10 ሺ በላይ ህገወጥ ቤቶች ይፈርሳሉ
ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የክልሉ መንግስት የሃማኖት፣ የእድር፣ የአፎቻ መሪዎችን፣ የአገር ሽማግሌዎችንና ታዋቂ ግለሰቦችን በራስ መኮንን የህዝብ አዳራሽ ታህሳስ 5 ቀን 2007 ዓም ሰብስቦ ባወያየበት ወቅት ፣ ከ1990-2004 ዓም ባለው ጊዜ ውስጥ የተሰሩ ቤቶች በሰነድ አልባ ቤትነት የተመዘገቡ እና ከከተማው ማስተር ፕላን ጋር የማይጋጩ ከሆነ ህጋዊ ይደረጋሉ፣ ከ2004 ዓም እስካሁን ካርታና ፕላን ለሌላቸው ከሊዝ ውጪ የተገነቡት ግን ...
Read More »በበባህር ዳር ከተማ የሚታው የነዳጅ ችግር ተባብሶ ቀጥሏል፡፡
ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን እንደ ሌሎች የሃገሪቱ ክፍሎች በነዳጅ አቅርቦት ሲቸገሩ የቆዩት የባህርዳር የታክሲና ባጃጅ አሽከርካሪዎች ዛሬም ድረስ ችግሩ ተባብሶ መቀጠሉን ለዘጋቢያችን ተናግረዋል። በትናንትናውና በዛሬው እለት በከተማዋ ካሉት ከአስር በላይ ማደያዎች በአንዱ ብቻ ነዳጅ የሚገኝ መሆኑን የተናገሩት አሽከርካሪዎች ፣ በዚህ ነዳጅ ማደያ ለመቅዳት እስከ ሁለት መቶ ሜትር ተሰልፈው ለሰዕታት እንደሚቆዩ ተናግረዋል፡፡ ሁል ጊዜ በወሩ መጨረሻ የነዳጅ ...
Read More »የደቡብ ሱዳን የሰላም ድርድር እንደገና ለማስጀመር ጥረት እየተካሄደ ነው
ታኀሳስ ፰(ስምንት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለአንድ አመት ያክል ተቋርጦ የነበረው የደቡብ ሱዳንን የሰላም ስምምነት እንደገና ለማስጀመር እንቅስቃሴ መጀመሩን የቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ስዩም መስፍን አስታውቀዋል። ድርድሩ የተጀመረው በአዲስ አበባ ነው። ሁለቱ ተፋላሚ ሃይሎች በተለያዩ ጊዜያት ለድርድር ቢቀመጡም እስካሁን ይህ ነው የሚባል መፍትሄ ሊያመጡ አልቻሉም። የኢሳት የዲፕሎማቲክ ምንጮች እንደሚሉት በደቡብ ሱዳንና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ግንኙነት እየሻከረ ሲሆን፣ ደቡብ ሱዳንም ...
Read More »በማህበረ ቅዱሳን ውስጥ ኢሳትና የግንቦት 7 ፣ በፕሮቴስታንት ደግሞ የኦነግ ሰዎች አሉ ሲሉ ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ተናግሩ
ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቅርቡ የፌደራልና የክልል የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊዎች በባህርዳር በተሰባሰቡበት ወቅት የፌደራል ጉዳዮች ሚኒስትር የሆኑት ዶ/ር ሽፈራው ተ/ማርያም ፣ ይህን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋም የፖለቲካ ፍላጎት ማራመጃ መሆኑን ለማስረዳት ነው። ዶ/ር ሽፈራው ከአፋር የጸጥታ ዘርፍ ሃላፊ ” መንግስት ለምን በሃይማኖት ጉዳይ ጣልቃ ይገባል? ለምንስ በአገራችን የሌለ ችግር ያመጣብናል?” በሚል ጥያቄ ቀርቦላቸዋል። ዶ/ር ሽፈራው ይህንን ለማስረዳት ይጠቅማል ...
Read More »በሽንሌ ዞን 7 ሰዎች በፌደራል ፖሊሶች ተገደሉ
ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የአካባቢው ሰዎች እንደገለጹት በአፋርና በኢሳ መካካል ያለውን የቆየ የድንበር ውዝግብ ተከትሎ መንግስት የተወሰኑ ቦታዎች ወደ አፋር ክልል እንዲካተቱ መወሰኑን ተከትሎ በተነሳ ተቃውሞ 7 ሰዎች በጸጥታ ሃይሎች ሲገደሉ ከ30 በላይ የሚሆኑ ደግሞ ቆስለዋል። በርካታ ሰዎችም ተይዘው ወደ አልታወቀ ስፍራ ተወስደዋል። አሁንም በአካባቢው ከፍተኛ ውጥረት የሰፈነ ሲሆን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች መንግስትን የሚያወግዙ የተቃውሞ ሰልፎችንም እያደረጉ ነው። ...
Read More »ከህዳር 30 ቀን 2007 ዓ.ም ጀምሮ በነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ ዋጋ ላይ ቅናሽ መደረጉን ተከትሎ በአዲስአበባ የነዳጅ ማደያዎች ባለፈው አንድ ሳምንት የታየው የነዳጅ ሰልፍ አሁንም ድረስ መቀጠሉ ታወቀ፡፡
ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ንግድ ሚኒስቴር የዋጋ ቅናሹን ካደረገ በሃላ ማደያዎች አዲሱ ታሪፍ አያወዋጣንም በሚል መናገራቸውን ተከትሎ የአቅርቦት እጥረት የተፈጠረ ሲሆን ሚኒስቴሩ የተወሰኑ ማደያዎችን በማሸግና በማስፈራራት ነገሩን ለማርገብ ቢሞክርም ችግሩ ሳይቀረፍ 8ኛ ቀኑን ይዞአል፡፡ በቦሌ፣ በካዛንቺስ፣ በንፋስስልክ በሌሎችም የከተማዋ አካባቢዎች በየማደያው ረጃጅም ሰልፎች የሚታዩ ሲሆን የችግሩ ትክክለኛ መንስኤ ምን እንደሆነ እንዳላወቁያ ያነጋገርናቸው አሽከርካሪዎች ገልጸው፣ ነዳጅ ለመቅዳት ከማደያ ...
Read More »