በፓኪስታን-ፔሽዋር  ውስጥ በሚገኝ ትምህርት ቤት በተከፈተ የአሸባሪዎች ጥቃት በትንሹ 126 ስዎች መገደላቸው ተሰገበ።

ታኀሳስ ፯(ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ቢቢሲ ባለስልጣናትን ጠቅሶ እንደሰገበው በታሊባን የተፈጸመ ነው በተባለው በሲህ ጥቃት ከሞቱት መካከል በርካታዎቹ ህጻናት ናቸው። ወታደራዊ ዩኒፎርም የለበሱ አምስት ወይም ስድስት የሚሆኑ ታጣቂዎች ወደ ትምህርት ቤቱ መግባታቸውን የትናገሩት ባለስልጣናቱ፤ ወዲያውኑ አካባቢው በደህንነቶች እንዲከበብ መደረጉን ተከትሎ የተኩስና የፍንዳታ ድምጽ መሰማቱን ተናግረዋል። ወደ 500 ከሚጠጉ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች በርካቶቹ ማምለጣቸውን የጠቀሱት ባለስልጣናቱ፤ይሁንና  ምን ያህል ተማሪዎች ...

Read More »

መድረክ በአዲስ አበባ የተሳካ የተቃውሞ ሰልፍ አካሄደ

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመድረክ የህዝብ ግንኙነት ሃለፊ አቶ ጥላሁን እንዳሻው የገዢው ፓርቲ የጸጥታ ሃይሎች ሲያደርሱት ከነበረው ጫና አንጻር ሲታይ የተሳካ የሚባል ሰላማዊ ሰልፍ መደረጉን ገልጸዋል። መጪው ምርጫ ነጻና ፍትሃዊ እንዲሆን፣ የሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶች እረገጣ እንዲቆም፣ የተለያዩ የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች፣ ጋዜጠኞች፣ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት እንዲፈቱ በመፈክሮች መጠየቃቸውን ገልጸዋል። በሰልፉ ላይ የተወሰኑ የመድረክ መፈክሮች ብቻ እንዲሰሙ ...

Read More »

አየር መንገድ የሰማያዊ ፓርቲ የፋይናንስ ክፍል ሃላፊን ከስራ አባረረ

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአየር መንገድ ውስጥ ሱፐርቫይዘር አፒራንስ በሚል የሃላፊነት ቦታ ላይ ሲሰሩ የነበሩት አቶ ወረታው ዋሴ ሃላፊነታቸውን በአግባቡ አልተወጡም በሚል በፈረንጆች አቆጣጠር ከዲሰምበር 8፣ 2014 ጀምሮ ከስራቸው እንደተባረሩ የሚገልጽ ደብዳቤ ደርሶአቸዋል። አቶ ወረታው በበኩላቸው ውዝግቡ የቆየ መሆኑን በማንሳት ፣ አየር መንገዱ የወሰደው እርምጃ ከፖለቲካ አቋማቸው ጋር የተያያዘ መሆኑን ገልጸዋል። የኢትዮጵያ አየር መንገድ የወሰደውን እርምጃና የአየር ...

Read More »

አቶ ሽመልስ ከማል  ከአቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር  በመጋጨታቸው አኩርፈው ቤት መቀመጣቸው ተሰማ

ታኀሳስ ፮(ስድት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የመንግስት ኮምኒኬሽን ጽ/ቤት ሚኒስትር ዴኤታ የሆኑት አቶ ሽመልስ ከማል ከ ሚኒስትሩ ሬድዋን ሁሴን ጋር መግባባት ባለመቻላቸው አኩርፈው ቤት በመቀመጥ መደበኛ ሥራቸውን እያከናወኑ አለመሆኑን  ምንጮች ገልጸዋል። አቶ ሽመልስ ከደባል ሱስ  ጋር በተያያዘ በመደበኛ የስራ ሰዓታቸው ሊገኙ ባለመቻላቸው ሚኒስትሩ ይህን ባህሪያቸውን እንዲያስተካክሉ ቢነግሩዋቸውም ሊያስተካክሉ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው የተፈጠረ መሆኑን ምንጮች ይገልጻሉ። የአቶ ሽመልስን   ሃላፊነት ደርበው እየሰሩ ...

Read More »

የስዊድን ከፍተኛ አቃቢ ህግ በ13 የኢትዮጵያ ባለስልጣናት ላይ ምርምራ በማድረግ ላይ ነው

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አንድ ከፍተኛ አቃቢ ህግ ለስዊድን ሬዲዮ እንደገለጹት ምርጫ 97ትን ተከትሎ በህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ ጦር ለተገደሉ ንጹህ ዜጎች ተጠያቂዎች ናቸው የተባሉ 12 ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናትና አንድ ስዊድን አገር በሚገኝ ሌላ ወታደራዊ አዛዥ ላይ ምርመራ  እየተካሄደ ነው። ማስረጃዎች ተሰባስበው እንዳለቁ ክስ ሊመሰረት እንደሚችል የገለጹት አቃቢ ህጓ ፣ባለስልጣናቱ በየትኛውም አገራት ቢዘዋወሩ ተይዘው ለፍርድ እንደሚቀርቡ ገልጸዋል። ጉዳዩን በቅርብ ...

Read More »

መድረክ ታህሳስ 5 የጠራውን የተቃውሞ ሰልፍ ቅስቀሳ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች እያደናቀፉት ነው

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በኢትዮጵያ ውስጥ ነጻና ፍትሃዊ ምርጫ ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች እንዲመቻቹ ለመጠየቅ መድረክ የፊታችን እሁድ የጠራው ሰልፍ እንዲደናቀፍ የገዢው ፓርቲ ካድሬዎች ተጽእኖ ቢያሳርፉም፣ ተጽኖውን ሁሉ ተቋቁሞ የሰፈር ለሰፈር ቅስቀሳውን እያካሄደ መሆኑን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው አቶ ጥላሁን እንዳሻው ተናግረዋል። አዲስ አበባ መስተዳድር ሰላማዊ ሰልፉ እንዲካሄድ እውቅና ቢሰጥም፣ ቅስቀሳ ለማድረግ ሌላ እውቅና ያስፈልጋል በሚል በድምጽ ማጉያ ቅስቀሳ ...

Read More »

ታዋቂው ጠበቃ ተማም አባቡልጉ የዲሲፒሊን ክስ ቀረበባቸው

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስር ላይ የሚገኙ የሙስሊም የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላትን እንዲሁም የህሊና እሰረኞችን ጉዳይ የሚከታተሉት ጠበቃ ተማም አባቡልጉ ከዚህ በፊት ለሎሚ መጽሄት በሰጡት አስተያየት ነው። ሰማያዊ ፓርቲ የሽብረተኞች መጠቀሚያ ሆኗል በሚል በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የቀረበውን ዘገባ በመተቸታቸው እንዲሁም በኢትዮጵያ የጸረ ሽብር ህግ ላይ አስተያየት በመስጠታቸው የዲሲፕሊን ክስ ቀርቦባቸዋል። አቶ ተማም የኢትዮጵያ ቴሌቪዥንንና  የጸረ ሽብር ህጉን ታዓማኒነት ...

Read More »

በ2006 በደሴ የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ የታሰሩ ሙስሊም ኢትዮጵያውያን ጉዳይ ውዝግብ አስነሳ

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፊደራል ፍ/ቤት ከወንጀል ነፃ ናቸው በሚል ያሰናበታቸወን ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን በተመለከተ  የክልሉ አስተዳደር እና ፀጥታ ነፃ አይደሉም በሚል ባቀረበው አቤቱታ ጉዳያቸው በክልሉ ካቢኔ መታየት ጀምሯል፡፡ የክልሉ ካቢኔ ባደረገው ውይይት ለሁለት የተከፈለ ሲሆን አንደኛው ወገን እንፍታቸው ሲል ሌላው ወገን ደግሞ በምርጫው  ላይ አሉታዊ ተጽኖ ስለሚያሳርፉ መፈታት የለባቸውም በሚል ሲከራከሩ ከቆዩ በሁዋላ ምርጫው ሳይጠናቀቅ መፈታት የለባቸውም ...

Read More »

ኢትዮጵያዊው የእርሻ ሳይንቲስት ዶ/ር የሺጥላ ደገፉ  በምርምር ስራቸው ፊንላንድ ውስጥ ሜዳልያ ተሸለሙ።

ታኀሳስ ፫(ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በትውልድ ኢትዮጵያዊ እና በዜግነት ፊላንዳዊ የሆኑት ከፍተኛ የእርሻ ሳይንቲስት  ዶ/ር የሺጥላ ደገፉ የክብር ሜዳልያውን የተሸለሙት ባለፈው ቅዳሜ ፣ ፊንላንድ 97ኛ አመት የነጻነት በአሉዋን ባከበረችበት ወቅት ነው። ዶ/ር የሺጥላ  ዕጽዋት ከየትና እንዴት በሽታ እንደሚይዛቸው፤ እንዴትስ በውስጣቸው እንደሚተላለፍና በራሳቸውም እንዴት እንደሚከላከሉ ከ23 ዓመታት ምርምር በሁዋላ  ሂደቱን ለመጀመሪያ ጊዜ በማግኝታችው ነው። ፊንላንድ መሠረታቸው ወይንም ዘራቸው ሳያግዳት  ...

Read More »

የተቃውሞ ሰልፍ በማድረጋቸው ብቻ ታስረው የነበሩ 9 ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ተፈቱ

ታኀሳስ ፪(ሁለት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው ህዳር 27 በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ ሲዘጋጁ በፖሊስና በደህንነቶች ቁጥጥር ስር ውለው የነበሩት የ9 ፓርቲዎች አመራሮችና አባላት ከእስር የተለቀቁ ሲሆን፣ ብዙዎቹ በእለቱ በደረሰባቸው ድብደባ ከመጎዳታቸውም በተጨማሪ በእስር ቤት ውስጥ የነበራቸው አያያዝ አስከፊ እንደነበር ታውቋል። የሰማያዊ ፓርቲ የአመራር አባል የሆነው ይድነቃቸው ከበደ  ደህንነቶች ወደ እስር ቤት በተደጋጋሚ እየሄዱ ከማን ጋር ግንኙነት እንዳላቸው ...

Read More »