የካቲት ፳፫(ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን በባህርዳር ዩኒቨርስቲ ዘንዘልማ ግቢ ውስጥ በተካሄደው ስልጠና ለመሳተፍ ከአማራ ክልል ከሚገኙ ከተሞች ለመጡ 450 የከተማ ልማት ዘርፍ ባለሙያዎችና ሃላፊዎች በተሰጠው ግምገማ አስር ባለሙያዎች ብቻ የተሰጣቸውን የብቃት መመዘኛ ማለፋቸው የክልሉንና የፌዴራል ሃላፊዎችን ክፉኛ ማስደንገጡን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ ባለሙያዎቹና ሃላፊዎች በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ የሙያ ሁኔታ የተሰማሩ የከተማ ፕላን ሰራተኞች፣በመሬት ባንክ አገልግሎት የተሰማሩ እና ...
Read More »በአዋሳ በደረሰው የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር ከ20 በላይ ነው ሲሉ የቃጠለው ሰለባ የሆኑ ሰዎች ገለጹ
የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በደቡብ ክልል ዋና ከተማ በአዋሳ የካቲት 14 ቀን 2007 ዓም በደረሰው ከፍተኛ የእሳት ቃጠሎ የሟቾች ቁጥር በመንግስት እንደተገለጸው አንድ ሳይሆን ከ20 በላይ መሆኑን ተገጂዎች ለኢሳት ገልጸዋል። ከፍተኛ ንብረት ከወደመባቸውና እሳቱ ሲነሳ በስፍራው ከነበሩት መካከል አንዱ ለኢሳት ሲናገር፣ እርሱ የ6 ሰዎችን የተቃጠለ አስከሬን ማየቱን፣ በስፍራው የሚገኙ ጓደኞቹ ደግሞ በአጠቃላይ እስካሁን 27 አስከሬን ተፈልጎ መቀበሩን ...
Read More »ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሰቆጣ አርሶደአሮች በረሃብ ምክንያት ተሰደዱ
የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ወኪላችን እንደዘገበው በሰቆታ አካባቢ የተከሰተውን ከፍተኛ ድርቅ ተከትሎ አርሶደአሮቹ ወደ ምእራብ ጎጃምና ሌሎች የአማራ ክልል አካባቢዎች በመሰደድ ላይ ናቸው። ተፈናቃዮቹ ከክልሉ ባለስልጣናትም ይሁን ከፌደራል መንግስቱ ምንም አይነት እርዳታ አለማግኘታቸውን ገልጸዋል። ብዙዎቹ ተፋናቃዮች ወጣት ወንዶችና ሴቶች ሲሆኑ፣ በሰፈሩባቸው አካባቢዎች ስራ ሰርተው ራሳቸውን እንዲያስተዳድሩ እየጠየቁ ነው። ተፈናቃዮቹ በዝናብ እጥረት ምክንያት ሰብላቸው ሙሉ በሙሉ መውደሙን ገልጸዋል። ...
Read More »ሙስሊሞችና ክርስቲያኖች የተሳተፉበት የስልክ ጥሪ ማቆም አድማ ተካሄደ
የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ሰሞኑን እንዳዲስ ተጠናክሮ በቀጠለው ሙስሊም ኢትዮጵያውያንን የማሰር ዘመቻውን በመቃወም ድምጻችን ይሰማ የጠራው ስልክን ለ12 ሰአታት የማጥፋት ዘመቻ በተሳካ ሁኔታ መካሄዱን ዘጋቢያችን ገልጿል፡፡ በርካታ ሙስሊሞች ስልኮቻቸውን አጥፍተው የዋሉ ሲሆን፣ በማህበራዊ የመገናኛ ብዙሃን የሚያደርጉትን እንቅስቃሴም አቁመው ውለዋል። በርካታ ክርስቲያኖችም ጥሪውን ደግፈው ስልካቸውን ዘግተው ውለዋል። እርምጃ የመንግስት ዋነኛ የገቢ ምንጭ በሆነው ቴሌ ላይ የኢኮኖሚ ጉዳት ለማድረስ ...
Read More »በአማራ ክልል ነዋሪዎች በአገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች መማረራቸውን ተናገሩ
የካቲት ፳(ሃያ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በክልሉ ኢንዱስትሪና ከተማ ልማት ቢሮ እና የተለያዩ ቢሮዎች በየእለቱ ጉዳያቸውን ለማስፈጸም የሚመላለሱ ባለጉዳዮች በተለያየ ሰበብ ፈጻሚ በማጣት መቸገራቸውን ድርጅቱ ባዘጋጀው የአስተያየት መስጫ መዝገብ ላይ ማስፈራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ ያሳያል። ከተለያዩ አካባቢዎች ጉዳይ ለማስፈጸም እንደመጡ የገለጹት ቅሬታ አቅራቢዎች በተለይ በስብሰባ ሰበብ ለረዢም ጊዜ መጉላላታቸውን ባሰፈሩት የሃሳብ መስጫ ደብተር ላይ ለማንበብ ይቻላል። አስተያየት ሰጪዎች በዋነኝነት ያነሱት ችግር ባለስልጣኖች በስብሰባ ...
Read More »አብዛኞቹ የመንግሰት ጋዜጠኞች የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን መረጃዎች አመለከቱ
የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመንግስት የመገናኛ ብዙሃን ውስጥ ተቀጥረው የሚሰሩ ጋዜጠኞች አብዛኞቹ የኢህአዴግ አባላት መሆናቸውን ኢሳት በደረሰው የአባላት ስም ዝርዝርና የስራ ድርሻ ሰነድ ለማረጋገጥ ችሎአል። በቀድሞው ኢቲቪ በአዲሱ አጠራሩ ኢቢሲ እና በኢትዮጵያ ሬዲዮ ስር የሚሰሩ ዳይሬክተሮች፣ የዜና አዘጋጆች፣ የወቅታዊ ዘገባ አቀናባሪዎች፣ የስፖርት ጋዜጠኞች ፣ የካሜራ ባለሙያዎች፣ ቴክኒሻኖችና የተለያዩ የድጋፍ ሰራተኞች የህወሃት፣ የብአዴን፣ ኢህዴድ ወይም የደህዴግ አባላት ...
Read More »ሼክ አላሙዲን የህወሃትን 40 ኛ አመት በአል በአዲስ አበባ ስፖንሰር አደረጉ
የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) በትግራይ ክልል በብዙ መቶ ሚሊዮኖች የሚቆጠር ብር በማውጣት ከአንድ ወር በላይ ሲያከብር የቆየውን የ40ኛ ኣመት የምስረታ በዓሉን የፊታችን እሁድ በአዲስአበባ ሚሌኒየም አዳራሽ በሚያካሂደው ድግስ ለማጠቃለል መዘጋጀቱ ታውቋል፡፡ በዚህ ዝግጅት ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ አምባሳደሮችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች የሚገኙ ሲሆን የዕለቱን የፌሽታ በዓል ወጪ ሚሊየነሩ ሼህ አልአሙዲ እንደሚሸፍኑት ...
Read More »በኣማራ ክልል 31 እስር ቤቶች አደገኛ እስር ቤቶች ተባሉ
የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጃፓን መንግስት የሚደገፈው የግልግል ዳኝነት ይፋ ባደረገው ጥናታዊ ጽሁፍ በአማራ ክልል የማረሚያ ቤቶች በህግ ታራሚዎች አያያዝ እና አስተዳዳር ከፍተኛ ችግሮች አሉባቸው ብሎአል። 31 እስር ቤቶች በእስረኞች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትሉም ተገልጿል። ለሰው ልጆች አደገኛ ተብለው ከተለዩት እስር ቤቶች መካከል ደብረ ታቦር፣ ጋይንት፣ አዲስ ዘመን፣ ሃይቅ፣ ደብረ-ብርሃን፣ መሃል ሜዳ አዲስ ከተማ፣ አጣየ፣ ወልድያ፣ ...
Read More »በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት የድጋፍ ኮሚቴ አባላት በጋራ ለመስራት ተስማሙ
የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሁለቱ ፓርቲዎች የድጋፍ ኮሚቴ አስተባባሪዎች በጋራ በመስራት ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሳኔ ማሳለፋቸውን ያስታወቁት፣ አንድነት ፓርቲ መንግስት በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ አማካኝነት እንዲፈርስ ከተደረገና አባሎቹም ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው። በሌላ ዜና ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ቀድሞ የአንድነት አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ...
Read More »በኬንያ የተያዙት ኢትዮጵያውያን በገንዘብ ተቀጡ
የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በህገወጥ መንገድ ወደ ደቡብ ሱዳን ሊሄዱ ሲሉ ተያዙ የተባሉት 101 ኢትዮጵያውያን ኬንያ ፍርድ ቤት ቀርበው 50 ሺ የኬንያ ሸልንግ መቀጣታቸውን፣ ቅጣታቸውን ካልከፈሉ ደግሞ በአንድ አመት እስር ተቀጠው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ተወስኖባቸዋል። ኢትዮጵያውያኑ በምግብ እጥረት የተነሳ በከፍተኛ ሁኔታ ተጎሳቁለው ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተዘግቧል። መንግስት ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት ማግኘቱን በመገናኛ ብዙሃን በተደጋጋሚ ቢገልጽም አገሪቱን ...
Read More »