በሰሜን አሜሪካ የሚገኙ የሰማያዊና የአንድነት የድጋፍ ኮሚቴ አባላት በጋራ ለመስራት ተስማሙ

የካቲት ፲፱(አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሁለቱ ፓርቲዎች የድጋፍ ኮሚቴ አስተባባሪዎች በጋራ በመስራት ሰማያዊ ፓርቲና ሌሎች በሃገር ውስጥ የሚንቀሳቀሱ ሃይሎችን በጋራ ድጋፍ ለመስጠት ውሳኔ ማሳለፋቸውን ያስታወቁት፣ አንድነት ፓርቲ መንግስት በሚቆጣጠረው ምርጫ ቦርድ አማካኝነት እንዲፈርስ ከተደረገና አባሎቹም ሰማያዊ ፓርቲን ከተቀላቀሉ በሁዋላ ነው።

በሌላ ዜና ደግሞ በተለያዩ ክልሎች ቀድሞ የአንድነት አሁን የሰማያዊ ፓርቲ አባላት የሆኑ ሰዎች እየታሰሩ መሆኑን የሚደርሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።